Ethiopian Kids

Ethiopian Kids ልጆቻችሁን ለምትወዱ ኢትዮጵያውያን Hello and Welcome to Ethiopian KIDS. We provide information everything about
children.
(4)

The articles, tips, and quotes on children and family

DISCLAIMER:
The pictures/images that are used as the background on quotations and displayed on this page are taken from the internet (google images). If origin of the picture/image is known, it will be acknowledged. ..However if the origin of the picture/image is unknown cannot be given credit. If there are pictures displaying on this page

which belong to specific entity,
please send a message via e-mail to [email protected] to receive proper acknowledgment or request to be taken off the wall. PRIVACY NOTICE: Warning - any person and/or institution and/or Agent and/or Agency of any governmental structure including but not limited to the United States Federal Government also using or monitoring/using this website or any of its associated websites, you do NOT have my permission to utilize any of my profile information nor any of the content contained herein including, but not limited to my photos, and/or the comments made about my photos or any other "picture" art posted on my profile. You are hereby notified that you are strictly prohibited from disclosing, copying, distributing, disseminating, or taking any other action against me with regard to this profile and the contents herein. The foregoing prohibitions also apply to your employee , agent , student or any personnel under your direction or control. The contents of this profile are private and legally privileged and confidential
information, and the violation of my personal privacy is punishable by law.

09/01/2026

ትንሳኤ አልአዛር ከአዲስ አበባ

09/01/2026
ልጄ ሆይ እነሆ የአያቶችሽ እና የቅድም አያቶችሽ አገር…ጉዞ ወደ ግንብቹ ወረዳ ጨፌ ዶንሳ ከተማ እና ግርሚ አቦ የገጠር መንደርከመጀመሪያ ልጄ ጋር ከአሜሪካ ተነስተን በልጅነት አይምሮዬ ምድራ...
08/30/2026

ልጄ ሆይ እነሆ የአያቶችሽ እና የቅድም አያቶችሽ አገር…
ጉዞ ወደ ግንብቹ ወረዳ ጨፌ ዶንሳ ከተማ እና ግርሚ አቦ የገጠር መንደር
ከመጀመሪያ ልጄ ጋር ከአሜሪካ ተነስተን በልጅነት አይምሮዬ ምድራዊ ገነት ብዬ ከሳልኳቸው ቦታዎች ውስጥ አንዷ ወሆነችው ጉዞ ጀምረናል።
በመጀመሪያ ያቀናነው ከቅድም አያቶቼ ጀምሮ አፅማቸው ወዳረፈበት እኔም ክርስትና ወደተነሳሁበት ግርሚ አቦ ደብር ነበር። እሁድ በማለዳ የነፍስ ይማር እንጀራ በመሶብ ፣ ጠላ እና ጠጅ በጀሪካን ፣ ወጥ እና ያቺን ነጭ ነገርም ሳትቀር ይዘን …ባጃጅ መግባት እስከሚችልበት በባጃጅ ከዛም በግራችን እየገሰገስን ነው። ጉዞአችን ላይ ሁለት ትላልቅ ሞጆ እና ሞጆ ጆሎ የተባሉ ወንዞችን አቋርጠን የፈጣሪን ጥበብ እያደነቅን የማይደረስ የለም ደረስን።
እንዴት ደስ ይላል አባቶች በቅዳሴ መሀል የአያቶቻችን ፣ የአክስቴን ፣ የአባቴን ፣ የባለቤቴን አባት እና የአክስቴን ባል የክርስትና ስም እያነሱ በፀሎት አሰቧቸው። ምዕመናኑም ይዘን የመጣነውን እየተቃመሱ ነፍስ ይማር ሲሉን ነበር። ፈጣሪ የእነዛን ቅን እና ደጋግ አያቶቼን ነፍስ ከፃድቃን አጠገብ እንደሚያስቀምጣት አልጠራጠርም። ስለነሱ ብሎ የኛንም ህይወት በምህረት ዓይን ይመልከተው።
እኔ ውልደቴ አዲስ አባባ ቢሆንም ለአቅመ ትምህርት እስክደርስ አያቶቼ ልጃችንን አንሰጥም በማለታቸው አብዛኛውና ጣፋጩ የልጅነት ትዝታዎቼ የገጠር ህይወት ነው።
ለአባቴ እሸቱ ሻረው ክብር ይግባውና ትምህርቴን በአዲስ አበባ ከጀመርኩ በኋላም ከአያቶቼ ጋር ያለው ፍቅር እንዳይቋረጥ እህቶቼን ሰላማዊት እና ያለምን…(እሙዶ) ጋር በየክረምቱ መስቀል እና አዲስ ዓመትን ጨምረን ከአያቶቻችን ጋር ነው የምናሳልፈው።
በደርግ ጊዜ አብዛኛው የአካባቢው ሰው "ሰፈራ" በሚል መርሀ ግብር ነባር ቀያቸውን እያፈረሱ ወደ አንድ አካባቢ ይሰበሰቡ ነበር።
የኛ ቤተሰብ እድሜ ለግሪካዊው ቅድም አያታችን መኖሌ ፓፓፓጵሎስ በሞጆ ወንዝ ላይ ብቻ 3 በውሀ ሀይል የሚሰሩ የወፍጮ ቤቶች በተለያዩ አካባቢዎች ስለነበሩን ወፍጮቤቱን ጥለን መሄድ ስለማንችል ቤታችን አልፈረሰም።
መኖሪያ ቤታችን ከትልቁ ሞጆ ወንዝ አናት ላይ በበርካታ ዛፎች የተከበበ ለአካባቢው የመጀመሪያው ውስጡም ውጪውም መጥርብ ድንጋይ እና በነጭ ኖራ የተገነባ ዘመናዊ እድሜ ጠገብ የቆርቆሮ ቤት ነው። በተለይ ግርሚ የሚገኘው ወፎጮ ቤት በተለያየ ዕፅዋት እና ፍራፍሬ እንደነ ሎሚ ኮምጣጤ ብርቱካን ፣ ዘይቶና እና በመሳሰሉት ስለተሞላ ምድራዊ ገነት ነው የሚመስለው።
ግሪካዊው ቅድም አያቴ የበርካታ የእጅ ሞያ ባለቤት ነበር። በኢትዮጵያ በተለያዪ ቦታዎች በውሀ የሚሰሩ የመኖሌ ወፍጮቤት ፣ አዲስ አበባ ዙሪያ ለገዲዲና በተለያዩ ቦታዎች የኖራ ማምረቻዎች ፣ በከተማ አሁን ሰሜን ሆቴል ህንፃ ከተገባበት አጠገብ የዳቦ ፋብሪካዎች ፣ በቤታቸውም አረቄን በዘመናዊ መልክ የሚያዘጋጁበት ማሽንም ነበራቸው። በአገራቸውም ግሪክ እጅግ የተከበሩ ባለጠጋና ባለብዙ ምያ ባለቤት ኢንጅነር ነበሩ።
መኖሌ ፓፓፓጵሎስ ቅድም አያቴን አመለወርቅ አርጋውን አግብተው ሲኖሩ በፈጣሪ ፍቃድ መሪያ(አየለች) መኖሌ የምንላት አያቴን ትወለዳለች። ልጄ ልያትም ከአያቴ ጋር ብዙ የሚያመሳስላቸው ነገሮች አላቸው።
መሪያ ለአቅመ አዳም ስትደርስ ከግሪክ ድረስ እጮኛ መጥቶ ያያት እና ይተወቃሉ። አባት እና እናቷ እንደልጃቸው ያሳድጉት ደሜ ሰኚ አብቹ የሚባል ጉብል ለካ መሪያን በጣም ይወዳት ነበር። ደሜ በጣም ጠንካራ ሰራተኛቸው ነበር በተለይ በጣሊያን እና በኢትዮጵያ ጦርነት ወቅትም ዘምቶ የነበረ እጅግ መልከመልካም ጎበዝ አዳኝ ስለነበረ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ ነበር።
ለመሪያ እጮኛ ከግሪክ አገር መጣላት ልታገባ ነው የሚለው ወሬ ወደ ጆሮው ሲደርስ ሳይቀድሙኝ ብሎ መሪያን እና መሳሪያውን ይዞ ዋሻ ይገባል። አንድም ወንድ የሆነ ሰው ዋሻ መጥቶ መሪያን ማስጣል የሚችል ኅይል አልተገኘም።
የመሪያ አባትም በንዴት ብዙ አረቄ ይጠጡና ይሞታሉ። አጅሬ ደሜ መሞታቸውን ሲሰማ ከዋሻ ወጥቶ እዛ አካባቢ ያለውን ሀብት ብቻ አስከብሮ ሌላውን ጉዳይ ሳይሰጥ ያን ሁሉ ንብረት ማንም ወረሰው ፣ ጥሩነቱ በዙሪያው ያሉትን ንብረቶች አስከብሮ ለቀጣዪ ትውልድ አስተላልፏል። በስህተት ፈረንጅ የሚባል እዛ አካባቢ ከታየ አለቀለት። መሳሪያ እየተኮሰ አዲስ አበባ ድረስ ነበር የሚያባርራቸው።

የእህል ውሀ ነገር ሆኖ አያቶቼ መሪያ እና ደሜ አምስት ልጆችን አፍርተው ብዙ ዓመት በፍቅር መኖር ችለዋል። በመጨረሻም እሱ በ83 ዓመቱ መሪያ በ78 ዓመቷ ተከታትለው ከዚህ ዓለም ድካም አረፍ። እግዚያብሔር ነፍሳቸውን ከደጋግ ፃድቃናት አጠገብ ያስቀምጥልን።
ቅድም አያቴ አመለወርቅ አርጋው የፈረንጁ ሚስት "ከጃርቲ" አሮጊት ከሚለው የኦሮምኛ ቃል በስተቀር ጆሮአቸው ቢቆረጥ ኦሮምኛ አይሰሙም። ትውልድ እና እድገታቸው ቡልጋ ምንጃር እና ሸንኮራ ነው።
እኔ እና እሳቸው የተለየ ፍቅር ነበረን። አቤት ጨዋታ ሲያቁ ሁሉ ነገራቸው በግጥም እና በዜማ ነበር። በህይወቴ በጣም የሚቆጨኝ የሚያወሩትን ሳልፅፍ ማለፋቸው ነው። ሁሌም እሳቸው ሳስታውስ በአምሮዬ ቀድሞ የሚመጣው እረጅሙ ዱላቸው ነበር። የበርበሬ ድልህ ፣ የጠላና የጠጅ ጋኖች የሚጠበቁት በሳቸው ነው። ያንን የበርበሬ ድልህ እና ጠላ ለመስረቅ ቀስ ብለን ስንመጣ በረጅሙ ዱላቸው አናታችን ይሉን ነበር። ማንንም አያስነኩም።
አያቴ መሪያ መኖሌን ከእናቴም በላይ ሳልወዳት አልቀርም…። በርካታ የልጅነት ጨዋታዎችን እንደ "መግላሊቴ" ቁንጥጫ ለቁንጥጫ ፣ እንቆቅልሽ እና ተረት ተረት የመሳሰሉትን ጨዋታዎች ሁሌ ማታ ማታ እሳት እየሞቅን ስንጫወትና ስንስቅ ነው የምናመሸው። ሁሉም ሴቶች በትልቁ ምጅጃ ዙሪያ ተሰብስበው ቡና አፍልተው ይጠጣሉ ፣ ግማሹ እራት ይሰራል ፣ ከማሳ የተለቀመ ጎመን ይቀቀላል ፣ አንዳንዴ ገንፎ በትልቅ ብረድስት ይገነፋል። ትልልቆቹ እናቶች የከሰል ምድጃ እየተቀባበሉ በቀሚሳቸው ሸፍነው የውስጥ ሰውነታቸውን ያሞቁታል።
አያቴ በተለይ እኔን እጅግ ሲበዛ አብዝታ ትወደኛለች። ስሜን ኤልያስ ብላ ያወጣችልኝም እሷ ነች። ከአዲስ አበባ ስመጣ የደስታ እንባ በአይኖቿ ሞልተው ይፈሳሉ። ወደ አዲስ አበባ ስሄድም እንደዛው ታነባለች።
ልትሞት ጥቂት ወራት ሲቀራት በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እኔ ነበርኩ የማስታምማት "ደም አስፈልጎን ስላላገኘን እኔ ቀይ መስቀል ሄጄ ደም መስጠት ነበረብኝ። እንደዛም ሆኖ የተቆረጠላትን ቀን ማለፍ አልተቻለም። መርቃኝ… መርቃኝ…መርቃኝ… አትጠግብም።
በኔ ህይወት "የእሷ ምርቃት" ፈጣሪ ጋር የደረሰ ይመስለኛል። እውነት ነው "የሚያድግ ልጅ አይጥላህ የሚሞትም ሽማግሌ አይርገምህ" አደል የሚባለው…የትልቅ ሰው ምርቃት ከመሬት አይቀርም።
ከወንድ አያቴ ደሜ የማረሳቸው ትዝታዎች እቤታችን ውስጥ በርካታ መሳሪያዎች ነበሩን ዲሞፍተር ፣ ቤልጅግ ፣ መንቱፍ ፣ እረሽ ፣ ሽጉጥ እና የት እንደሚቀመጥ የማናውቀው 30 ጎራሽም ነበረው። አቤት ሽጉጡን ስወዳት …
ብዙ ጊዜ አደን እኔን ፣ ልጁን ደረጄ ደሜን የአክስቴን ልጅ ነዋይን እና የተወሰኑ ገበሬዎችን አስከትሎ ትልቁን የረሽ እና ትንሹዋን ቤልጂግ ይዘን ነበር ለዓደን የምንወጣው… ሚዳቆ ፣ ቆቅ እና ጅግራ ተሸክመን እንመጣ ነበር። አቤት የቆቅ ስጋ ሲጣፍጥ።
ሁሌ ቅዳሜ… ቅዳሜ ከሰኞ እስከ አርብ የተሰበሰበውን ከወፋጮቤት ገንዘብ ይዞ ቤልጅጉን ታጥቆ እሱ በበቅሎ እኛ እህል የጫኑ አህዮችን እየነዳን በግራችን ጨፌዶንሳ ከተማ እቁብ ለመጣል እንሄዳለን።
ነፍሱዋን ይማረው እና ሁለተኛ ልጁ አክስቴ አልማዝ ደሜ ጨፌ ዶንሳ ከተማ ውስጥ ምግብ ቤት ነበራት …ለስላሳ የምእንጠጣው ፣ ምግብ ቁንጣን እስኪይዘን የምንመገበውን መቼም አረሳውም…
ገበያም ወርደን ጋዝ ለኩራዞቻችን ፣ ዘይት ፣ ቡና እና ስኳር ፣ ጨው ፣ ሸንኮራገዳና ከረሜላ ገዝተን በአህያ እንጭናለን። ስንመለስ አህያዎ ቹ ብዙ ጭነት ስለሌላቸው አህያ እየጋለብን ነበር ወደቤት የምንመለሰው። አይ ልጅነት…ቢያወሩት አያልልቅም…
ከመስከረም ጀምሮ እስከ መስቀል ያለው ወቅት ለእኔ አይምሮ በጣም የተለየ ነው። አገሩ በሙሉ በአደይ አበባ ይሞላል። ሳሩ አድጎ ግማሽ ሰውነታችን ይሸፍናል…ልጃገረዶች በአዲስ ዓመት ዋዜማ በቤታች በታች ካለው የሞጆ ወንዝ ባህር ዳርቻ መጥተው አረንጓዴ ቀጤማ(ቁኒ) ይለቅማሉ። ጎረምሳው ከንፈር ወዳጅ መያዝ የሚጀምረው ገና ከዋዜማው ነው። ማታላይ ችቦ ይበራል ወንድ አያቴ መሳሪያ ይተኩሳል። "የመስቀል ደመራ" ለየት የሚያደርገው የበራ ችቦ ይዘን ወደሌላ አካባቢ እንሮጥ ነበር።

የአዲስ ዓመት እለት ጠዋት ከብት ይታረዳል ሶስት እግር ያላቸው ትላልቅ የኬሻ ገበቶች (ጠረጴዛ) ከተሰቀሉበት ወርደው እንጀራ ይለብሳሉ።
እረፈድ ሲል ትላት በወንዙ ዳር ቀጤማ ሲለቅሙ የነበሩት ልጃገረዶች ቀጤማቸውን ይዘው በበርካታ ጎረምሶች ታጅበው አባቢሌ ሮቤ ጨዋታ ረገዳ (የአበባዮዎሽ ጨዋታ) የሚጀመረው ከኛ ቤት ነው።
ምግብ እስኪጠግቡ በላይ በላዩ እየተጨመረላቸው ይበላሉ። ጠላ እንደልባቸው ይጠጣሉ። በልተው እንደጨረሱ ጎረምሳው ባንድ አቅጣጫ ልጃገረዶቹ በሌላው አቅጣጫ ተሰልፈው ወገብ ወገባቸውን ተያይዘው እስኪደክማቸው (አሱ …እብሺው…አሱ …እብሺው ) (ክዋኬ… ክ ክዋኬ …ክ) እያሉ ቤቱ እስኪደበላለቅ ድረስይጨፍራሉ (ይረግዳሉ) ። አቤት አባራው …
በመጨረሻም ከአያቶቻችን የገንዘብ ሽልማት ይሰጣቸዋል። እነሱም በተራቸው መርቀውን ወደሌላ ቤት ጉዞ ያደርጋሉ።
እኔና አጎቴ ደረጄ ደሜ የሰባት ዓመት ልዩነት ቢኖረን ነው። የዛን ለት ቤተዘመድ ተሰብስቦ እነዛን ትንንሽ ልጆች ከንፈርወዳጅ መያዝ አለባችሁ ጎበዞች በርቱ እያሉ የልብ ልብ ሰጡን። እኛም ወንድነት ተሰምቶን ወንዙን ከመሻገራቸው በፊት ለመያዝ ሙከራ እንዳደረግን ወዲያው በያዙት ቀጤማ ፊት ፊታችን መትተው እሮጠው አመለጡን። ይመስለኛል እኛ በጣም ልጆች ስለሆን አልተሳካልንም…

… ዋና የምንዋኝባቸው ቦታዎች… ከብት የምንጠብቅበት አካባቢዎች እንደዱሮም ባይሆኑ ዛሬም አሉ ፣ የሞጆ ወንዝ ከመጠን በላይ የሞላ ለት ማንም ሰው መሻገር አይችልም። የአገሬው ሰው የሞላው ወንዝ እስኪጎል እኛ ቤት ነበር የሚያድሩት።
ውሾቻችን እጅግ በጣም አደገኛና ፈጣን እሯጮች ነበሩ። አጋጣሚ ከብት ስንጠብቅ ጥንቸል ካገኘን " አዉ… አዉ… አው…" ብለን ውሾቹን እንጠራቸዋለን። ውሾቹም ወዲያው ጥንቸሉዋን አባረው ይይዙና ይበሏታል…
የዶሮው ፣ የድመቱ ፣ የንብ ቀፎዎው ብዛት አይቆጠርም… አንዳንዴ በትትዝታ ወደኋላ ሄጄ ምነው ያ የልጅነት ጊዚ ተመልሶ ቢመጣ እያልኩ አስባለሁ።
ልጄ ልያት ከመጠን ያለፈ ደስታ ተሰምቷታል በርካታ የድሮ የግሪክ መፅሀፍትን እና ፎቶዎችን በኤአይ እገዛ ግሪካዊ ቤተሰቦቹዋን ለመፈለግ ደፋ ቀና እያለች ነው። አራት ትውልድ ወደኋላ ፈጣሪ ያበርታሽ…
ዛሬ ላይ በተለይ በኛ ቤተሰብ ግርም የሚለኝ ነገር ቅድም አያቶቻችን በዘመናቸው መኅበረሰብን የሚያገለግል በርካታ ስራዎችን ሰርተው ፣ ሀብትና ንብረት አፍርተው አውርሰውን አለፍ። እኛስ ከነሱ ምን ተማርን ? ምንስ ሰራን? የሚለው ጥያቄ ብዙ ያስጨንቀኛል።
አራት እና አምስት ትውልድ እነሱ በዘመናቸው ባቆዩልን ሀብት ብቻ ተጧሪ ሆነናል። ፈጣሪ ቢፈቅድ እኛም በዘመናችን ህብረተሰብን የሚጠቅም ስራ መስራት እንዳለብን ይሰማኛል። ፈጣሪ ታሪክ ተቀባይ ብቻ አያድርገን ታሪክ ሰሪዎችም ያድርገን።
ይህ አጭር ታሪክ በእናቴ ቤተሰብ በኩል ያለው ነው።
በቀጣይ የአባቴን እሸቱ ሻረው ተክለወልድን ቤተሰብ እንጎበኛለን። እስከዛው ቸር ሰንብቱልኝ።

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

08/25/2026

ሁላችንም ከሩት ጎን በመቆም በአስደናቂ ጥንካሬዋ ላይ ተጨማሪ ግርማ ሞገስ እናላብሳት ዘንድ ድምፅ በመስጠት አጋርነታችንን እናሳያት።

Vote for Miss World 2026 Ethiopia, Ruth Yirgalem.

Vote now at:
missworld.1voting.com

ዘመን ተሻጋሪው ድምፃዊ ይሁኔ በላይ በ10ኛው አልበሙ "ዞማዬ" በተሰኘ መጠሪያ በአዲስ አመት ልባችንን ሊያወዛውዘው ነው!🎤       🎤         🎤      🎤       🎤      🎤​ኢት...
08/21/2026

ዘመን ተሻጋሪው ድምፃዊ ይሁኔ በላይ በ10ኛው አልበሙ "ዞማዬ" በተሰኘ መጠሪያ በአዲስ አመት ልባችንን ሊያወዛውዘው ነው!
🎤 🎤 🎤 🎤 🎤 🎤
​ኢትዮጵያዊነትን በዜዬ፣ ባህልን በቅንብር፣ የሃገር ፍቅርን ደግሞ በውብ ግጥም እያዋሃደ ለበርካታ አስር አመታት በልባችን ውስጥ ዘላቂ ዙፋን የሰራው የተከበረውና ተወዳጁ ድምፃዊ ይሁኔ በላይ 12 ዓመታትን ተጨንቆና ተጠቦ ያዘጋጀውን ድንቅ የጥበብ ፍሬ፣ 10ኛ አልበሙን "ዞማዬ" በሚል መጠሪያ ከአድናቂዎቹና ከአድማጩ ጋር ሊያገናኝ ዋዜማ ላይ ይገኛል!

🔘​ከጎጃሙ የኪነት እንቁ "ግሽ አባይ" ተነስቶ እስከ ግዙፎቹ የሙዚቃ መድረኮች የተጓዘው ይሁኔ በላይ፤ ጥበብን በዕውቀት ከተፈጥሮ ድምፁ እና ባህሪውን በሕዝብ ፍቅር አምቆ፣ አቋሙን ደግሞ በሃገር ወዳድነት አፅንቶ የኖረ ብርቅዬ የጥበብ ሰው ነው።

🔘​ይህ "ዞማዬ" የተሰኘው አስረኛ አልበሙ ተራ የሙዚቃ ስብስብ አይደለም፤ ሙሉ 12 ዓመታትን በስሜት፣ በሙያዊ ብስለት እና በጥበብ ፍለጋ የተጠመቀ የጥበብ ማዕድ ነው!

🔘​ የሃገራችንን ህብረ-ቀለማት ያንጸባረቁ የይሁኔ በላይ' ዞማዬ' አልበም ውስጥ..
1: መላ አለው
2: እኔስ ባገሬ
3: እንጃልኝ
4: ዞማዬ
5: እኔ ሆይ
6: አገኜሽኝ እና
7: ተይ ዘው ዘው
8: እቴ አዶ ወሸባ.. የተሰኙ ስምንት ልዩ ልዩ የዜማ ስልቶች ተካተውበታል። ​

🔘ስለ ሃገር፣ ፍቅር እና ባህል: ልብን የሚነኩ፣ መንፈስን የሚያድሱና የቆየ ትዝታን የሚቀሰቅሱ መሳጭ ግጥሞችና ዜማዎች አሰባስቧል።

🔘​የዝነኛውና አንጋፋው የግጥምና ዜማ ደራሲ አበበ ብርሃኔ እና የሌሎች ታላላቅ ባለሙያዎች አስደናቂ አሻራ አርፎበታል።

🔘​"ሙዚቃዎቹን አስቀድመው ያደመጡ ታዋቂ ግለሰቦችና የጥበብ ሰዎች በስራው ጥራትና ውበት በመደመም አልበሙ ለህዝብ ክፍት እስኪሆን ድረስ በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ!"

🔘​የባህል አምባሳደር እና የሃገር ፍቅር ህያው ምስክር የሆነው የይሁኔ በላይ ድምፅ ዳግም ቤታችንንና ልባችንን ሊሞላው ጥቂት ቀናት ቀርተውታል።
🔘​የድምፃዊ ይሁኔ በላይ ፕሮሞተር ደመወዝ ገነቱ እንደገለጹት፤ ይህ ድንቅ ስራ በከፍተኛ ጥራትና በቃት ተሰርቶ በአዲሱ ዓመት ለህዝብ ይደርሳል። ካሉ በኋላ
"ጆሮአችሁን አዘጋጁ... "ዞማዬ" መንገድ ላይ ነው! "ብለዋል።

🔘​ከዳሞት ምድር እስከ ዓለም አቀፍ መድረክ የዘለቀው የኢትዮጵያ ባህል አምባሳደር እና
​የኢትዮጵያ ባህላዊ ዜማ ውበት የሆነው ተወዳጁ ድምፃዊ ይሁኔ በላይ፣ ተወልዶ ያደገው በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር በቆላ ደጋ ዳሞት አውራጃ በምትገኘው በውቧ ፍኖተ ሰላም ከተማ ነው።
።።።።።።።።።።።

ለውድ አድማጮቼ

12 ዓመታትን ከፈጀ ልፋትና ድካም በኋላ፤ እነሆ 10ኛውን የሙዚቃ አልበሜን "ዞማዬ" በሚል ርዕስ ይዤላችሁ እመጣ ዘንድ የፈጣሪ ፈቃድ ሆነ🙏

ለዚህም ልዑል እግዚአብሔርን አመሠግናለሁ🙏

ይህ ሥራ በትዕግስት፣ በፍቅርና በብዙ ጥረት የተሰራ ሲሆን፤ በርካታ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

በአልበሙ የተሳተፉ ሁሉንም የዜማና የግጥም ደራሲዎች፣ አቀናባሪዎች፣ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች እና ሌሎች ባለሙያዎች በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ!

ውድ አድማጮቼንም ሁሌም ከጎኔ ስለሆናችሁ እጅግ አመሰግናለሁ!!!

ለውድ አድማጮቼ

12 ዓመታትን ከፈጀ ልፋትና ድካም በኋላ፤ እነሆ 10ኛውን የሙዚቃ አልበሜን "ዞማዬ" በሚል ርዕስ ይዤላችሁ እመጣ ዘንድ የፈጣሪ ፈቃድ ሆነ🙏

ለዚህም ልዑል እግዚአብሔርን አመሠግናለሁ🙏

ይህ ሥራ በትዕግስት፣ በፍቅርና በብዙ ጥረት የተሰራ ሲሆን፤ በርካታ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

በአልበሙ የተሳተፉ ሁሉንም የዜማና የግጥም ደራሲዎች፣ አቀናባሪዎች፣ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች እና ሌሎች ባለሙያዎች በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ!

ውድ አድማጮቼንም ሁሌም ከጎኔ ስለሆናችሁ እጅግ አመሰግናለሁ!!!

🎬 ነገ ቅዳሜ ከአልበሙ ውስጥ “ዞማዬ” የተሰኘው የመጀመሪያ የቪዲዮ ክሊፕ በዩቱብ ቻናሌ
www.youtube.com/ ይለቀቃል

በየጊዜው የሚለቀቁ አዳዲስ ስራዎችን ወዲያውኑ ለማግኘት ቻናሉን Subscribe ማድረግ እና የማሳወቂያ ደወሉን 🔔 ማብራት አይርሱ። እናመሰግናለን!

🎉 ሙሉ አልበሙ ደግሞ በመጪው ሐሙስ በይፋ የሚለቀቅ ይሆናል

— ይሁኔ በላይ

Artist Yehunie Belay Official Channel of all his music videos and more.

🎬 🔥🔥🔥 ነገ ከአልበሙ ውስጥ “ዞማዬ” የተሰኘው የመጀመሪያ የቪዲዮ ክሊፕ በአርቲስት ዩሁኔ በላይ ዩቱብ ቻናል ላይ ይለቀቃል። www.youtube.com/  ይለቀቃል 🔥🔥🔥ቻናሉን Subscrib...
08/21/2026

🎬 🔥🔥🔥 ነገ ከአልበሙ ውስጥ “ዞማዬ” የተሰኘው የመጀመሪያ የቪዲዮ ክሊፕ በአርቲስት ዩሁኔ በላይ ዩቱብ ቻናል ላይ ይለቀቃል።
www.youtube.com/ ይለቀቃል 🔥🔥🔥

ቻናሉን Subscribe ማድረግ እና የማሳወቂያ ደወሉን 🔔 ማብራት ይጠብቁን። እናመሰግናለን!

🎉 ሙሉ አልበሙ ደግሞ በመጪው ሐሙስ በይፋ የሚለቀቅ ይሆናል

— ይሁኔ በላይ

Address

42129 Robins Hatch Ter
Brambleton, VA
20148

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Kids posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Kids:

Shortcuts

Share

Category