Awramba Times

Awramba Times Awramba Times is an online media outlet providing latest news and analysis about Ethiopia & the horn
(1)

ዋናው አዛዥ ኃላፊነት ላይ ሆነው ምክትል አዛዡ በምስጢር የሚመሩት የትግራይ ሰራዊት! ሁሉም ሊያየው የሚገባ ልዩ መረጃ!ሊንክ ኮመንት ላይ
01/09/2026

ዋናው አዛዥ ኃላፊነት ላይ ሆነው ምክትል አዛዡ በምስጢር የሚመሩት የትግራይ ሰራዊት!
ሁሉም ሊያየው የሚገባ ልዩ መረጃ!

ሊንክ ኮመንት ላይ

29/08/2026

የኡጋንዳ ፖለቲከኞች የተወዛገቡበት የአቶ ግርማ ዋቄ የፓርላማ ሪፖርት
-----
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የኡጋንዳን ብሄራዊ አየር መንገድ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እየመሩ ያሉት አቶ ግርማ ዋቄ፣ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ይፋ ያደረጓቸው መረጃዎች በአገሪቱ ፖለቲከኞችና ሚዲያዎች ዘንድ ከፍተኛ የውዝግብ መንስኤ ሆነዋል።

ባለፈው ሐሙስ በኡጋንዳ ፓርላማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ፊት፣ ከሌሎች የማኔጅመንት አባላት ጋር በጋራ ቀርበው የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ግርማ፣ ወደዚሁ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት አየር መንገዱ በምን አይነት ቀውስና ኪሳራ ውስጥ እንደነበረና እሳቸው ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ያደረጓቸው ማሻሻያዎች ምን ምን እንደሆኑ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ከአገሪቱ የህዝብ እንደራሴዎች አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል።

በሙዋዳ እንኩይንጊ የተመራው ይህ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ የአየር መንገዱ የቀድሞዋ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጄኒፈር ባሙቱራኪም የተገኙበት ሲሆን አቶ ግርማ ዋቄ ይፋ ያደረጓቸውን ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ አስተያየት እንዲሰጡ ጥያቄ ቀርቦላቸው ትክክል መሆኑን አረጋግጠዋል።

የስብሰባውን ከፊል ይዘት በቪዲዮ ቀርቧል

አቶ ጌታቸው ረዳ ከሱዳን መንግስት ለቀረበ ክስ መልስ ሰጡ-------አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር "በአየር ክልሌ ውስጥ ገብተው አግኝቼአቸዋለሁ" ያላቸውን ሶ...
29/08/2026

አቶ ጌታቸው ረዳ ከሱዳን መንግስት ለቀረበ ክስ መልስ ሰጡ
-------

አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር "በአየር ክልሌ ውስጥ ገብተው አግኝቼአቸዋለሁ" ያላቸውን ሶስት የኢትዮጵያ ድሮኖችን በተከታታይ መትቶ እንደጣለ መግለፁን ተከትሎ ጉዳይ የአለምአቀፍ ሚዲያዎች መነጋገርያ ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል።

ይህንኑ ተከትሎ የአረቢኛው አልጀዚራ ጥያቄ ያቀረበላቸው የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ ጌታቸው ረዳ ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ የምታቀርበው ክስ፣ የውስጥ ቀውሷን ዓለም አቀፋዊ መልክ ለማስያዝ የምታደርገው ሙከራ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

"ኢትዮጵያ የሱዳንን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በጽኑ ታከብራለች" ያሉት አቶ ጌታቸው፣ "በዚህ መርህ የሚመራ አገርና መንግስት በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገባበት ምንም አመክንዮ የለም" በማለት የመንግስታቸውን አቋም ለሚዲያ ተቋሙ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው በዚህ ማብራሪያቸው ለሱዳን ቀውስ ወታደራዊ አማራጭ መፍትሔ አለመሆኑን ገልጸው በሱዳን ውስጥ እየተፋለሙ ያሉ ኃይላት ልዩነታቸውን በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ ምክረሀሳብ ለግሰዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ከብሄራዊ ደህንነት ዳይሬክተሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር በመሆኑ ወደ ፖርት ሱዳን ተጉዘው የጠ/ሚ አብይ አህመድን መልእክት ለጄነራል አብደልፈታህ አልቡርሐን ማድረሳቸው የሚታወስ ቢሆንም የሁለቱም ወገኖች ግንኙነት ከመሻሻል ይልቅ ባለፈው አንድ አመት "አንዱ የሌላውን ባላንጣ እየደገፈ ነው" በሚል በየሚዲያዎች ሲካሰሱ ማስተዋል የተለመደ ሆኗል።

5 የፖሊት ቢሮ አባላትን ያገለለው Centeral command እና ያልተጠበቀው የጄ/ል ክንፈ ሹመት!ሙሉ ፕሮግራሙን ለማየት ሊንክ ኮመንት ላይ ይገኛል
27/08/2026

5 የፖሊት ቢሮ አባላትን ያገለለው Centeral command እና ያልተጠበቀው የጄ/ል ክንፈ ሹመት!

ሙሉ ፕሮግራሙን ለማየት ሊንክ ኮመንት ላይ ይገኛል

በአፍሪካ ህብረት በኩል እየተደረገ ያለውን የሰላም ጥረት እንደሚደግፉ የአውሮፓ ህብረት ልኡካን አስታወቁ----አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - "በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ውጥረት እንዲረግብ...
26/08/2026

በአፍሪካ ህብረት በኩል እየተደረገ ያለውን የሰላም ጥረት እንደሚደግፉ የአውሮፓ ህብረት ልኡካን አስታወቁ
----

አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - "በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ውጥረት እንዲረግብ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተደረገ ያለውን የሰላም ጥረት እንደግፋለን" ሲሉ የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ዛሬ አመሻሽ ላይ ይፋ ባደረጉት የጋራ መግለጫ አስታወቁ።

በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት ተጠሪ የሆኑ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድኖች ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የዲፕሎማቲክ ተልዕኮዎች ማለትም ከኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ ቡልጋሪያ፣ ቼክ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሀንጋሪ፣ አየርላንድ፣ ጣሊያን፣ ሉክሰምበርግ፣ ማልታ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ፖርቱጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቫኪያ፣ ስሎቬንያ፣ ስፔን፣ ስዊድን — እንዲሁም በአዲስ አበባ ከሚገኙት የካናዳ፣ ኖርዌይ እና የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲዎች ጋር በመሆን ነው የጋራ መግለጫውን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ያደረጉት።

ልኡካኖቹ በዚሁ የጋራ መግለጫቸው "በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄዱ ሁኔታዎችን በጥልቅ ስጋት እየተከታተልን እንገኛለን" ያሉ ሲሆን "ሁሉም ወገኖች የፕሪቶሪያውን የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነትን (CoHA) ተግባር ላይ ለማዋል በበጎ ፈቃደኝነትና በአዎንታዊ መልኩ እንዲሳተፉ እናበረታታለን" ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ የሆኑትን የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሰጉን ኦባሳንጆ እንደ አዲስ የሚያደርጉትን ጥረት በመግለጫቸው ያደነቁት ልኡካኖቹ፣ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በአዲስ አበባና በመቐለ ያካሄዷቸውን ስብሰባዎች በጎ ጥረት መሆናቸውን በመግለጽ ቀደም ሲል በድርቅና በሌሎች ሰው ሰራሽ ጉዳቶች የተዳከመውን እንዲሁም ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልገውን የትግራይ ክልል ወደ ሌላ ዙር የጦርነት ግጭት ቢገባ ጉዳቱ እጅግ ከፍተኛ ስለሚሆን የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ሁኔታውን በማርገብ ረገድ ጥረት ያድርጉ ሲሉ የጋራ መግለጫቸውን አገባድደዋል።

- ደብረጽዮንን ያስቆጣው የኦባሳንጆ የድርድር ቅድመ-ሁኔታ!- እንደገና የተከለሰው የህወሓት አቋም- 'ጽምዶ'ን ያመሱት ፖለቲከኛሊንክ ኮመንት ላይ
25/08/2026

- ደብረጽዮንን ያስቆጣው የኦባሳንጆ የድርድር ቅድመ-ሁኔታ!
- እንደገና የተከለሰው የህወሓት አቋም
- 'ጽምዶ'ን ያመሱት ፖለቲከኛ

ሊንክ ኮመንት ላይ

25/08/2026

ህወሓት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን 'የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ' ሲል ወነጀለ
-----

አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - "ጽምዶ" በሚል ስያሜ በኤርትራ መንግስት ፊታውራሪነት በተመሰረተው ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰሞኑን የሰጡት አወዛጋቢ አስተያየት ህወሓትን አስቆጣ።

አቶ አንዳርጋቸው "አንከር" ከተባለ የበይነ-መረብ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ እንዳብራሩት፣ ህወሓት እና ፋኖ በኤርትራ መንግስት አሸማጋይነት እንደተቀራረቡ ገልጸው፣ ተቀራርበው በተወያዩበት ወቅትም የፋኖ ኃይሎች ህወሓቶችን "ምዕራብ ትግራይንና ራያን እናስመልሳለን በሚል አካባቢውን በኃይል ለመቆጣጠር የምትሞክሩ ከሆነ ተቀባይነት የለውም" ብለው እንደነገሯቸውና የህወሓት አመራሮችም በዚህ ሀሳብ ተስማምተው ወደ ጥምረቱ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

ይህ የአቶ አንዳርጋቸው መረጃ በማህራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል። "የበግ ልምድ የለበሱ ተኩላዎች ሴራ" የሚል አገላለጽ ተጠቅመው ምላሻቸውን የሰጡት አቶ አማኑኤል፣ ማብራሪያቸውን ሲቀጥሉ "አንዳርጋቸው ጽጌ ከዚህ በፊት ከብልፅግና ጋር በመተባበር በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመው ድርጊት ሳይበቃው፣ አሁን ደግሞ ከስርዓቱ ጋር የተጣላ መስሎ በህዝባዊ ኃይሎች መካከል ስንጥቅ በመፍጠር ፅምዶውን ለማፍረስ እየሰራ ነው" ሲሉ ከሰዋል።

አቶ አማኑኤል ዛሬ ይህን ይበሉ እንጂ ከአንድ አመት በፊት በርእዮት ሚዲያ ቀርበው እነ ጄነራል ጻድቃንን በከሀዲነት በከሰሱበት ቃለምልልስ ላይ "ማስረጃዎ ምንድነው?" ተብለው ሲጠየቁ ማስረጃቸው በአቶ አንዳርጋቸው የተሰራጨ ሰነድ መሆኑን ያብራሩ ሲሆን በወቅቱ "የአንዳርጋቸውን መረጃ ምን ያህል ያምኑታል" ተብለው በጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ሲጠየቁ "ከጻድቃን አንዳርጋቸውን አምናለሁ" ማለታቸው ይታወሳል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጽምዶውን በይፋ በመቀላቀል ባለፉት ጥቂት ወራት በፖርት ሱዳን፣ በናይሮቢ እና በሌሎች የጽምዶ መድረኮች ንቁ ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከቪዲዮው ይመልከቱ

21/08/2026

ግልጋሎት ኢሚግሬሽን ኢትዮጵያ ብጊዜያዊ ምምሕዳር ዘይተፀሓፉ ዶክመንታት ኣይቅበልን ኢሉ
-------
ኣውራምባ ታይምስ [ኣዲስ ኣበባ] - ካብ ግልጋሎት ኢሚግሬሽንን ዜግነትን ኢትዮጵያ ፓስፖርት ንምውፃእ ይኹን ዝተፈላለዩ ግልጋሎታት ንምርካብ ካብ ትግራይ ዝመፁ ዜጋታት ብጊዜያዊ ምምሕዳር ዘይተፀሓፉ ዶክመንታት ሒዞም እንተመፅዮም ከምዘይተኣናገዱ ተሓቢሩ።

ኣብቲ ዓውዲ ንሱ ጉዳይ ብምፍፃም ዝነጥፉ ሰብ ሙያታት ከምዝሕብሩዎ ልደት ካርዲን መለለዪ መንነትን ሓዊሱ ፓስፖርት ንምውፃእ ክማልኡ ዝግቦኦም ኩሎም ዶክመንታት ብጊዜያዊ ምምሕዳር ማህተምን "ሄዲንግን" ክፀሓፉ ከምዘለዎም ብምግላፅ፣ ካብኡ ወፃኢ እቶም ሰነዳት "ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይ" ዝብል ሄዲንግን ማህተምን ዝዓረፎም እንተኾይኖም ግን እቲ ኣፀዋውዓ ንሱ ብፌደራል መንግስቲ ኣፍልጦ ስለዘይብሉ ከምኡ ዝበሉ ዶክመንታት ንዝሓዙ ተጋሩ እቲ ትካል ገልጋሎት ምሃብ ከምዘቋረፀ ሓቢሮም።

ካብቶም ኣብቲ ዓውዲ ንሱ ዝነጥፉ ሰብ ሙያታትን ሓደ ብቪዲዮ ዝሃቦ መብራህርሂ ተኣንገዱ

ህወሓት እንደገና ወደ 4ኪሎ!ህዝብ ሳይመክርበት፤ ልሂቃን ሳይስማሙበት፤ ተቃዋሚዎች ሀሳብ ሳይሰጡበት!ሊንክ ኮመንት ላይ
18/08/2026

ህወሓት እንደገና ወደ 4ኪሎ!
ህዝብ ሳይመክርበት፤ ልሂቃን ሳይስማሙበት፤ ተቃዋሚዎች ሀሳብ ሳይሰጡበት!

ሊንክ ኮመንት ላይ

ደብረጽዮንና ማሲንጋ ተደዋውለዋልን?ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንክ በአስተያየት መስጫው ላይ ይገኛል!
16/08/2026

ደብረጽዮንና ማሲንጋ ተደዋውለዋልን?
ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንክ በአስተያየት መስጫው ላይ ይገኛል!

Address

700 Bellevue Way NE
Addis Ababa
98004

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awramba Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Awramba Times:

Shortcuts

Share