بلغوا عني ولو ايه አንድትንም አንቀፅ ብትሆን ከኔ የሰማችሁትን አስተላልፉ

  • Home
  • Saudi Arabia
  • Jeddah
  • بلغوا عني ولو ايه አንድትንም አንቀፅ ብትሆን ከኔ የሰማችሁትን አስተላልፉ
03/11/2024

ነጌ አላህ ዘንድ የወረደና የዘቀጠ ምክንያት ማለት አንተን ከመታዘዝና የአንተን ንግግር ከማንበብ ሶሻል ሚዲያ ቢዚ አድርጎኝ ነበር ብሎ ማቅረብ ነው።

አጅብብብ

13/03/2021

🔺 🔻
1. ፆም- አላህን ለመገዛት አላማ (ለኢባዳ) ከጎህ መቅደድ በፊት ጀምሮ እስከ ፀሀይ መጥለቅ ባለው ጊዜ ውስጥ ፆምን ከሚያፈርሱ ነገሮች ታግዶ መዋል ነው፡፡

2.የረመዳን ፆም ከታላላቆቹ የኢስላም መዓዘናት አንዱ ነው፡፡ይህም ቀጥሎ ባለው የነብያችን(ﷺ) ሀዲስ መሰረት ነው፡፡

‹‹ኢስላም የተገነባው በአምስት መሰረቶች ላይ ነው (እነሱም)፡- ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሀመድ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር ፣ሰላትን አዘውትሮ መስገድ ፣ ዘካን መስጠት የረመዷንን ወር መፆምና የጅ ሥርዓተ ጸሎት ማድረስ ናቸው፡፡››
ወንድሞቼ! የተከበረው ወር፣ ታላቁ ወር መጣላችሁ በውስጡ አጅር የሚደራረብበት፣ የአላህ ስጦታ የሚበረከትበት፣ መልካምን ፈላጊ ሁሉ የበጐ ነገራት በሮች የሚከፈቱበት የኸይር ወር፣ የበረካ ወር፣ የስጣታና የገፀበረከት ወር፡፡


1.ገላን የመታጠብ ግዴታ ሳይፈፅሙ (ጀናባን ሳይታጠቡ) ለፆም ኒያ ማድረግ እና ጎህ ከቀደደ በኋላ ገላን መታጠብ ለፆመኛ ሰው ይፈቀዳል፡፡

2.ሴት ረመዳን ውስጥ ከጎህ መቅደድ (ከፈጅር) በፊት ከወር አበባም ሆነ ከወሊድ ደም ከጠራች ገላዋን ከነጋ በኋላ የምትታጠብ ቢሆን እንኳ ፆሙን መፆም ግዴታ ይሆንባታል፡፡

3.ፆመኛ ሰው ጥርሱን መነቀል ቁስሉን ማከም በአይኖቹ እና በጆሮዎቹ መድሀኒት መጨመር ይፈቀድለታል፡፡ የመድሀኒቱ ስሜት አፉ ውስጥ ቢሰማው እንኳ ይህን ማድረግ ይፈቀድለታል፡፡

4.ፆመኛ ሰው ጠዋትም ሆነ ማታ ጥርሱን መፋቅ ይፈቀድለታል፡፡ ሲዋክ ለፆመኛ ሰውም ልክ እንደሌላው ሰው ሁሉ ሱንና ነውና፡፡

5.ፆመኛ ሰው ሙቀት እና የውሀ ጥሙን ሊያቃልሉለት የሚችሉ እንደ ቀዝቃዛ ሻወር እና ኮንዲሽነር ያሉ ነገሮችን መጠቀም ይፈቀድለታል፡፡

6.በደም ግፊት ምክንያትም ሆነ በሌላ ምክንያት የሚደርስበትን የትንፋሽ ማጠር ለመቋቋም በአፉ በኩል አየር መንፋት ይፈቀዳል፡፡

7.ፆመኛ ሰው ከንፈሮቹ ሲደርቁ በውሀ ሊያርሳቸው እንዲሁም አፉ ሲደርቅም አልፎ እንዳይገባ በመጠንቀቅ አፉን በውሀ መጉመጥመጥ ይፈቀድለታል፡፡

8.ስሁርን ማዘግየት ፍጡርን ማፋጠን ሱንና ሲሆን ሲያፈጥር በቴምር እት ወይም በተገኘው የቴምር አይነት ፆምን መፈሰክ ሱንና ነው፡፡ ካላገኘ ግን በውሀ ያፈጥራል፡፡ ውሀም ካላገኘ በተገኘው ማንኛውም ምግብ ማፍጠር ነው፡፡ ምንም ነገር ከጠፋ ግን እስኪያገኝ ድረስ ፆሙን ለማፍጠር በልቡ ኒያ ያደርጋል፡፡

9.ፆመኛ ሰው የአላህን እና የነብዩን ትዕዛዛት በቅንነት በመፈፀም ትሩፋት ስራዎችን ማብዛት እና ከተከለከሉ ነገሮች መራቅም ሱንና ነው፡፡

10.ፆመኛ ሰው ሀይማኖታዊ ግዴታዎችን በትጋት በመፈጸም እና ሀራም ከሆኑ ነገሮች ሁሉ በመራቅ አምስቱን እለታዊ የግዴታ ሰላቶች ጊዜያቸውን ጠብቆ በህብረት (በጀመዓ) መስገድ ይጠበቅበታል፡፡ ሀሰት መናገር ፣ ሀሜት ፣ ማጭበርበር እና አራጣዊ ግብይቶችን እንደዚሁም ማንኛውም ሀራም የሆነ ንግግር እና ተግባር መተው ግዴታ ነው፡፡ ነብያችን (ﷺ) ይህንኑ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ አንድ ሰው ሀሰት መናገርን እና በርሱ መሰረት ክፉ መስራትን እንደዚሁም ግብዝነትን ካልተወ በስተቀር ምግብ እና መጠጡን (በፆም) በመተው አላህ ጉዳይ የለውም፡፡

☑️ምንጭ፦የሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሳሊህ አል-ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስራዎችን መሰረት ያደረገ

------------*********--

12/03/2021

🌴🌴🌴🌴🌴🐫🌴🌴🌴🌴🌴🌴

🌴🐫የረሱል ሰ.ዐ.ወ ታላቅ ምክር🐫🌴

🐫 አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና "ለዱንያም ሆነ ለአኼራ የሚጠቅም.ንግግር ለመጠየቅ መጣው" አላቸው ።
❓🌴እሳቸውም ደግሞ "የመጣልህን ጠይቅ" አሉት።

🐫 "ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው❓
👉🌴እሳቸውም "አላህን ፍራ"🌴አሉት

🐫 "ከሰው ሁሉ ሀብታመ ለመሆን እፈልጋለው❓" ሲላቸው።
👉🌴"ባለህ ነገር ተብቃቅተ አላህን አመስግን"🌴 አሉት

🐫 "ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው❓" ሲል
👉"🌴ለራስህ የምትወደውን ለሰዎች ውደድ🌴" አሉት።

🐫"ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለው❓" ሲል
👉🌴"በአላህ ተወከል"🌴 አሉት

🐫 "በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን እፈልጋለው" ሲላቸው❓
👉🌴 "ዚክር አብዛ"🌴 አሉት።

🐫"ከሰው ሁሉ በላጭ ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን እፈልጋለው❓" ሲል
👉🌴"ለሰው ጠቃሚ ሁን 🌴አሉት።

🐫"የተከበረና ቸር ሰው ለመሆን እፈልጋለው❓" ሲላቸው
👉🌴"ችግርህን ለፍጡር አትንገር"🌴 አሉት።

🐫"ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ እፈልጋለው❓" ሲል
👉🌴"አንተም እነሱ የወደዱትን ውደድ🌴" አሉት::

🐫"ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህን መገናኘት እፈልጋለው"❓ሲል
👉🌴"ጀናባህን በደንብ ታጥበ እስቲግፋር አብዛ ማልቀስ መተናነስ መታመም አለብህ🌴" አሉት።

🐫 "ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው❓" ሲላቸውም
👉🌴"አላህን ልክ እንደምታየው ሁነክ ተገዛው"🌴 አሉት።

🐫"ኢማኔ እንዲ ሞላ እፈልጋለው❓ ሲል
👉🌴"ፀባይህን አሳምር"🌴 አሉት።

🐫"እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው" ❓ሲል
👉🌴 "ተዋዱዕ አዘውትር"🌴 አሉት።

12/03/2021

السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللّٰه وَبَرَكَاتُهُ

Address

جدة, السعودية
Jeddah
22233

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when بلغوا عني ولو ايه አንድትንም አንቀፅ ብትሆን ከኔ የሰማችሁትን አስተላልፉ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to بلغوا عني ولو ايه አንድትንም አንቀፅ ብትሆን ከኔ የሰማችሁትን አስተላልፉ:

Share