E T H I O T I M E S

E T H I O T I M E S 🇪🇹 Ethiopia is the best country from Africa 🌍

 !👌ይህ  #ውብ የኮሪደር መንገድ  #የት አካባቢ ነው  #የተገነባው?ቀድመው በትክክል የመለሱ 3 (ሶስት) መላሾች የመቶ የመቶ ብር  #የሞባይል ካርድ ይሸለማሉ!!! #ማሳሰቢያ ምላሽ ሲሰጡ ...
05/04/2026

!👌
ይህ #ውብ የኮሪደር መንገድ #የት አካባቢ ነው #የተገነባው?
ቀድመው በትክክል የመለሱ 3 (ሶስት) መላሾች የመቶ የመቶ ብር #የሞባይል ካርድ ይሸለማሉ!!!
#ማሳሰቢያ ምላሽ ሲሰጡ Visit Hawassa ገፅን @ሜንሽን ማድረግ ይኖርቦታል
Hawasa

Iran war live: Tehran rejects Trump’s ultimatum; fire at Kuwait oil complex
05/04/2026

Iran war live: Tehran rejects Trump’s ultimatum; fire at Kuwait oil complex

በኢራን ኢንተርኔት ከተቋረጠ እና አብዛኛው ተጠቃሚ ከቀሪው ዓለም ከተቆራረጠ 36ኛ ቀኑን ይዟል።የዓለም የኢንተርኔት ግንኙነትን የሚቆጣጠረው ኔትብሎክስ በኢራን ኢንተርኔት ከተቋረጠ ከ840 በላ...
05/04/2026

በኢራን ኢንተርኔት ከተቋረጠ እና አብዛኛው ተጠቃሚ ከቀሪው ዓለም ከተቆራረጠ 36ኛ ቀኑን ይዟል።

የዓለም የኢንተርኔት ግንኙነትን የሚቆጣጠረው ኔትብሎክስ በኢራን ኢንተርኔት ከተቋረጠ ከ840 በላይ ሰዓታት ማለፉን አስታውቋል።

በኢራን ውስን ሰዎች እንደ ስታርሊንክ ያሉ ሳተላይቶች በመጠቀም የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛሉ። ነገር ግን ክፍያው ውድ ነው።

በኢራን ስታርሊንክ ሲጠቀሙ የተገኙ ግለሰቦች እስከ ሁለት ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣሉ።

የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት የቡሻህር የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ አካባቢ ጦርነቱ ከተጀመረ ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ጥቃት እንደደረሰበት አስታወቀ።ድርጅቱ ከፋብሪካው የጥበቃ ሠራተኞች አንዱ በጥቃቱ...
05/04/2026

የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት የቡሻህር የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ አካባቢ ጦርነቱ ከተጀመረ ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ጥቃት እንደደረሰበት አስታወቀ።

ድርጅቱ ከፋብሪካው የጥበቃ ሠራተኞች አንዱ በጥቃቱ መገደሉን የገለጸ ሲሆን አሜሪካንና እስራኤልን ተጠያቂ አድርጓል።

አሜሪካ እና እስራኤል ጥቃቱ ስለመፈጸሙ አላረጋገጡም

ሠበር መረጃ‼️12 የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ኮበለሉ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ በህዝብና በሃገር ላይ የፈጸምነው ስነ-ምግባር የጎደለው ዘገባ መዘገባችን ሳይበቃን ተጨማሪ የጥፋት ስ...
03/04/2026

ሠበር መረጃ‼️

12 የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ኮበለሉ
ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ በህዝብና በሃገር ላይ የፈጸምነው ስነ-ምግባር የጎደለው ዘገባ መዘገባችን ሳይበቃን ተጨማሪ የጥፋት ስራ እንደንሰራ እየተገደድን በመሆኑ በገዛ ፍቃዳችን ስራችንን ለቀናል ሲሉ የትግራይ ቴሌቪዠን ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡

እነዚህ ቁጥራቸው 12 የሆኑ የተግራይ ቴሌቪዠን ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ ህዝብና የፌደራል መንግስት የቅርታ ካደረጉልን ሃገራችንና ህዝባችንን መካስ እንፈልጋለን ሲሉ ከሚሰሩበት የትግራይ ቴሌቪዠን ኮብልለው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ታማኝ ምንጮች ገልፀ ዋል፡፡

በሌለና ባልተያዘ የድል ዜና የምናየው እና ያረጋገጥነው መረጃ ሌላ ሆኖ ሳለ፤ የትግራይ ወጣትን ድል እየተቀዳጀህ ነው ግፋ በለው እያልን የብዙ ወጣቶች ሂወት እንዳይቀጠፍ ሞያዊ ግዴታችንን መወጣት ሲገባን፤ የአንድ ቡድን ልሳን ሆነን ይትግራይ ህዝብን ከጥፋት አለማዳናችን ይቆጨናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ያ ሳይበቃ አሁን ላይ የፌደራል ምንግስትን እየወንጀልን የጦርነት ዜና ብቻ እንደንሰራ እና ወጣቱን ወደ ጦርነት እንድንቀሰቅሰው አቅጣጫ በመሰጠቱና ፀረ ፕሪቶርያ ስምምነት የሆኑ ዘገባዎችን በግላጭ እንድንሰራ መደረጉ ሂሊናችን ስላልተቀበለው ተቋሙን እንድንለቅ ግድ ሆኖብናል ብለዋል፡፡

እንደጋዜጠኞቹ ገለፃ አዲስ የተሾሙት የተቋሙ አመራሮች በቅርቡ ጋዜጠኞችን ሰብስበው በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ሰላም እነደምንፈልግ ግን ደግሞ ሰላም የሚረጋገጠው በጦርነት ብቻ መሆኑን አውቃችሁ የጦርነት አጀንዳዎች ብቻ ላይ ትኩረት አድርጋችሁ እንደትሰሩ ተብለናል ያሉ ሲሆን፤ በተጨማሪም ከቡድኑ እሳቤ ውጪ የሆኑ ወጣቶችንም ሆነ የማህበረስ ክፍል የሃሰት መረጃን በመጠቀም ውግንናቸው ለህወሓት ብቻ እንዲያደርጉና የስራ አፈፃፀማቸውም በዚህ ተግባራቸው እንደሚለካ ተነግሮናል ብለዋል፡፡
ከዛ ባሻገር ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የመመለስ ጉዳይ በአጀንዳነት ይዘው የፌደራል ምንግስት ለፕሪቶርያ ስምምነት እያደረገ ያለው ተጨባጭ ስራ በመገልበጥ፤ በተቃራኒው ለፕሪቶርያው ስምምነት መንግስት ተገዢ አይደለም ብለው እንዲሰሩ መገደዳቸውን ጋዜጠኞቹ አብራርተዋል፡፡

የህንን በታሪክም በሞያም ይቅር ሊያስብል የማይችለውን ተግባር ከምንፈፅም የክልላችነ ህዝብም ሆነ የሃገራችንን ጥቅም ማስጠበቅ የምንችልበትን እና ህዝባችንን የምንክሰበት አጋጣሚ በመፈለግ ከተቋሙ ለመኮብለል ተገደናል ሲሉ ገልፀ ዋል፡፡

ጋዜጠኞች በትግራይ ክልልም ሆነ እንደ ሃገር መደረግ ያለነበረባቸው ተግባራት በኛ የሞያ ዲሲፒሊን ክፍተት መፈፀሙ ተፀፅተናል ያሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅር እንዲለን እየተማፀን፤ በቀጣይ የጋዜጠኝነት ሞያ ስነ-ምግባር ባከበረና የሃገራችንን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ መካስ እንፈልጋለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ገዜጠኞቹ በቅርቡ የመኮብለላቸውን ምክንይት ለኢትዮጵያ ህዝብ ማብራራት እንደሚፈልጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሰበር ዜና፦ ሁለተኛው የአሜሪካ አየር ኃይል የጦር አውሮፕላን በፋርስ ባሕረ ሰላጤ (Persian Gulf) አካባቢ ወደቀ፤ ብቸኛው አብራሪ በሰላም መዳኑን ኒው ዮርክ ታይምስ (NYT) ዘገበ።
03/04/2026

ሰበር ዜና፦ ሁለተኛው የአሜሪካ አየር ኃይል የጦር አውሮፕላን በፋርስ ባሕረ ሰላጤ (Persian Gulf) አካባቢ ወደቀ፤ ብቸኛው አብራሪ በሰላም መዳኑን ኒው ዮርክ ታይምስ (NYT) ዘገበ።

ሰበር ዜና፦ የኤፍ-15 (F-15) አብራሪዎችን ለማዳን በተሰማራው ግዳጅ ላይ ሁለት የአሜሪካ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች በኢራን ተኩስ ተመቱ፤ ሆኖም ሁሉም የአሜሪካ ወታደሮች በሰላም መተርፋቸውን ...
03/04/2026

ሰበር ዜና፦ የኤፍ-15 (F-15) አብራሪዎችን ለማዳን በተሰማራው ግዳጅ ላይ ሁለት የአሜሪካ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች በኢራን ተኩስ ተመቱ፤ ሆኖም ሁሉም የአሜሪካ ወታደሮች በሰላም መተርፋቸውን ኤን ቢ ሲ (NBC) ዘገበ።

  ❤  🌐
31/03/2026


🌐

🤲⚠️🚸
31/03/2026

🤲⚠️🚸

  Welcome to Harari Region Tourism - "The Living Museum."Harari Region Tourism is committed to showcasing the beauty and...
31/03/2026



Welcome to Harari Region Tourism - "The Living Museum."

Harari Region Tourism is committed to showcasing the beauty and authenticity of this living museum, and we invite you to join us on an unforgettable journey where past meets present in perfect harmony.

Cuba crisis explained: Who holds power, and could Diaz-Canel be replaced?
31/03/2026

Cuba crisis explained: Who holds power, and could Diaz-Canel be replaced?

ሰበር ዜና፦ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራቅቺ፣ የቀጠናዊ ግንኙነቶችን ለማበላሸት የታለሙ ተደጋጋሚ የሀሰት ጥቃቶች (False Flag Operations) ሊሰነዘሩ እንደሚችሉ ለቱርክ ማስጠ...
31/03/2026

ሰበር ዜና፦ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራቅቺ፣ የቀጠናዊ ግንኙነቶችን ለማበላሸት የታለሙ ተደጋጋሚ የሀሰት ጥቃቶች (False Flag Operations) ሊሰነዘሩ እንደሚችሉ ለቱርክ ማስጠንቀቂያ ሰጡ።
ምንጭ፦ ብሪክስ ኒውስ (BRICS News)

Address

London
London

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when E T H I O T I M E S posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share