16/06/2022
በአንድ ወቅት ጫካ ውስጥ መውለጃዋ የቀረበ አንዲት ሚዳቆ ነበረች ።🦌 መውለጃ ሰዐቷ ደርሶ ትግል ላይ ሳለች ድንገት አከባቢዋን ስትቃኝ ከፊት ለፊቷ ወንዝ ፣ ከኋላዋ ቀስት ያነጣጠረባትን አዳኝ፣ ወደ ጎን ስትዞር የተራበ አንበሳ አሰፍስፎባት ትመለከታለች።
ይህም ሳይበቃት ጭማሪ ከፍተኛ ነጎድጓድና መብረቅ ያጀበው ደመና መጥቶ ሰማዩን ያጨልመዋል።💭💭
መብረቁም ከፍተኛ ነበርና ደኑን ይመታና ከፍተኛ ቃጠሎን ያስነሳባታል።⚡😱አስቡት ያለችበትን ጭንቅ 😟😱...
ወደ ፊት ሮጣ እንዳታመልጥ ጥልቅ ወንዝ ተደቀነባት፤ከኋላዋ አዳኙ፤ከጎኗ ደግሞ አንበሳው፤ወደ ጫካ ገብታ እንኳ እንዳትደበቅ ከፍተኛ ቃጠሎ ላይ ነው... በዚያ ላይ የውልደት ህመም ነፍስ ውጪ ግቢ እያስባላት ነው ...
ትኩረቷን መፈፀም ወደ ምትችለው ነገር ላይ ብቻ በማድረግ ቀሪውን ለፈጣሪ በመተው በመወለድ ላይ ስላለው ልጇ ብቻ ማሰብ ጀመረች።🤔🤔
የመብረቁ ብልጭታ💥 አይኑን ብዥ ያደርግበትና ቀስቱ አምልጦት ወደ ተራበው አንበሳ ይሄድና አንበሳውን ይገለዋል።
አጉበድብዶ የነበረው ደመናውም መዝነብ ይጀምርና የደኑን ቃጠሎ በቅፅበት አጠፋው።👏👏
በጭንቅ ታጅባ የነበረችው ሚዳቆም በሰላም ተገላገለችና ወደ ቀደመው ሂይወቷ ተመለሰች ይባላል.🤗🤗🤗🤗
#መልእክቱ
አንዳንዴ በህይወትህ ውስጥ በብዙ ፈተናዎችና ጭንቀቶች ልትከበብ ትችላለህ ያኔ አንተ ልትፈታው በምትችለው ነገር ላይ ብቻ አትኩርና ቀሪውን ለመፍትሄዎች ሁሉ ባለቤት ለ ፈጣሪህ ተወው።💚💚
መውጫ መፍትሄ አንተ ጋ እንጂ ፈጣሪህ ዘንድ አይጠፋም.
ብለህ ለጭንቆች እውቅና ከመስጠትህ ይልቅ የትላልቅ ጭንቀቶች አለቃ የሆነው ጌታ አለኝ እያልክ ጭንቀቶችህን አቅልላቸው።
በፈጣሪህ ፈፅሞ ተስፋ አትቁረጥ በጠረጠርከው ታገኛዋለህ