04/02/2023
ይህን ሁላችሁም እወቁ አሳውቁ !!!!
ደውል የተጀመረው በኖኀ ዘመን እንደ ነበረ አባቶች ያስተምራሉ። ደውል ካህናት ለአገልግሎት እንዲወጡ ለመጥሪያነት ያገለግል ነበረ።
ደውል በተለያየ ሰዓት በቤተክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት ይደወላል። ነገር ግን ለሁሉም አገልግሎት አንድ ዓይነት ደውል አይደውልም!
"በአደጋ ጊዜ ሲደወል ከሌሎቹ የሚለየው ደውሉን ቶሎ ቶሎ በፍጥነት ሲደወል ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር አለ ድረሱልን ማለት ነው።"
ቤተክርስቲያን ችግር ከገጠማት "ያለማቋረጥና በደውሎቹ መካከል ያለምንም እረፍት በተከታታይ ትደውላለች።" ይህ ጥሪ ቤተክርስቲያን የተለያየ ድንገተኛ አደጋ ሲገጥማት ነው።
ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ የደውል አደዋወል አላት ነገር ግን በአደጋ ጊዜ ሲደወል ከሌሎቹ የሚለየው ደውሉን ቶሎ ቶሎ በፍጥነት ሲደወል ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር አለ ድረሱልን ማለት ነው
ንቁና ጠብቁ !!!!!!!!!
ሼር አድርጉ ለጎደኞቻችሁ በቁምነገር መሃል አውሩት።