ከዝጝ ሳረ Kezgn sare

ከዝጝ ሳረ Kezgn sare This is the personal Woldekiros Dessie Amare (WDA) facebook pag- where you can get all the latest news in Amharic and Himtagna. you can follow us on.

16/01/2025
14/01/2025
10/01/2025

ኢትዮጵያ በካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት ባደረሰው ጉዳት የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ የተከሰተው ሰደድ እሳት በሰው ሕይዎት እና በንብረት ላይ ባደረሰው ጉዳት የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገለጸች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ÷ በደረሰው ጉዳት ኢትዮጵያ ማዘኗን አስታውቋል፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ከአሜሪካ መንግሥትና እንዲሁም በሎስ አንጀለስ አካባቢ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጎን መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

10/01/2025

ለኢትዮጵያውያን እና መንግሥታቸው ያልተደረገ ድጋፍ እንደተደረገ አድርጎ ማውጣት ተገቢ እንዳልኾነ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተማላሾች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር: ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ከ26 ሀገራት የመጡ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስጠልላ ከለላ እና የተለያዩ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የምትገኝ ሀገር እንደኾነች የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተማላሾች አገልግሎት ገልጿል፡፡

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በስደተኞች ስም የመጣ ማንኛውም ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን የመከታተል እና የመቆጣጠር ኀላፊነት ያለበት በመኾኑ ከዋና መሥሪያ ቤት ጀምሮ የስደተኛ ማዕከላት ድረስ የክትትል እና ቁጥጥር ሥርዓት ዘርግቶ እየሠራ እንደሚገኝም ነው ያብራራው፡፡

በዚህም መሠረት የራሺያ ፌደሬሽን የደቡብ ሱዳንን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ እና በጋምቤላ ክልል ለተጠለሉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ብሎም ጥገኝነት ጠያቂዎች በዓለም የምግብ ፕሮግራም (ዋፋ) በኩል 1ሺህ 632 ነጥብ 4 ሜትሪክ ቶን የስንዴ ድጋፍ አድርጓል ነው ያለው።

የስደተኞች ሰብዓዊ ድጋፍ ከተለያዩ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሚደረግ ድጋፍ በዓለም የምግብ ፕሮግራም በኩል ሲከናወን መቆየቱ እና የአሁኑ ድጋፍም የተደረገው ለተመሳሳይ ዓላማ እንደኾነ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተማላሾች አገልግሎት ጠቁሟል፡፡ ይህም በሩሲያ ኤምባሲ እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይፋዊ መግለጫዎች በግልጽ ተሰጥቷል ነው ያለው።

ኾኖም በተለያዩ የመገናኛ ብዙኀን ድጋፉ “ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት” እንደተደረገ በማስመሰል የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ እንደሚገኙ መገንዘቡንም ነው ያብራራው፡፡

በመኾኑም በተለያየ መነሻ የተሳሳተ ዘገባ ያስተላለፉ እና በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት እና አካላት ይህንን የእርምት መረጃ ግምት ውስጥ በማስገባት የተሳሳተ መረጃን እንዲያርሙም ጠይቋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

በረከት ስላለው በረከቱን ለማግኘት እለፋለሁ ነውና እና ከቻልነ...!
07/01/2025

በረከት ስላለው በረከቱን ለማግኘት እለፋለሁ ነውና እና ከቻልነ...!

26/12/2024

Address

ሳቁጠ
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከዝጝ ሳረ Kezgn sare posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category