HD Films Production

HD Films Production Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from HD Films Production, Photographer, Awassa.

* Mesk photographs,
* studio photographs
* music clip,
* advertising promotion
* HD Production
+251913392300/+251777772300
https://t.me/hdfull60
https://t.me/HDfilmpr
tiktok.com/
https://www.youtube.com/
john.nazi
John Naziraw

21/05/2026

‎ ክፍል 2
# ‎የሥላሴ ምንነት
‎የእግዚአብሔር አንድነት
‎የተዋሀደ አንድነት (ዘጸ6:4፣ ኤፌ4:3-6፣ 1ጢሞ2:5)
‎ከሁሉም በላይ መሆኑን የሚያመለክት አንድነት (ዘጸ20:3፣ ዘዳ6:4፣ 1ቆሮ8:4-6፣ ያዕ2:19)
‎የእግዚአብሔር ሶስትነት (አሐዱ ሥሉስነት) ሥላሴ
‎ሥላሴ የሚለው ቃል ሦስትነትን በአንድ ለመግለጽ የምንጠቀምበት የግዕዝ ቃል ነው:: ይህም የእግዚአብሔርን ሦስትነት ሳይሆን አንድነት ለመግለጽ ነው::

‎አዲስ ኪዳን በእግዚአብሔር ዘንድ ሦስት አካል እንዳሉና ስማቸውም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ይገልጻል:: እያንዳንዱ ፍጹም አካል አለው:: ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር በሦስት አይነት መልክ ሳይሆን በባህርይና በመለኮት አንድ የሆኑ ሦስት ፍጹማን አካላት አሉ ማለት ነው:: አካል ማለት በዚህ ትርጉም ፍጹም ሙለአዊና እኔ ባይ ማለት ነው:: ለሥላሴ ትምህርት መሰረቱም፡-

‎የጌታ ኢየሱስ ጥምቀት (ማቴ3:13-17)
‎ለጥምቀት የተሰጠን ሥርአት (ማቴ28:19)
‎የሰው መፈጠርና መውደቅ (ዘፍ1:26,3-:-22)
‎ለበረከት ያላቸው ውህደት(2ቆሮ13-:-13) ናቸው፡፡
‎የሥላሴ ሥራ
‎በመፍጠር

‎አብ - ዘፍ1፡3
‎ወልድ - ዮሐ1:1
‎መንፈስ ቅዱስ - ዘፍ1:2፣ ኢዮ26:12-13
‎በጌታ መወለድ

‎አብ - ዮሐ3:16
‎ወልድ - ሉቃ2:11
‎መንፈስ ቅዱስ - ሉቃ1:35
‎በድነት

‎አብ - ሉቃ15:22
‎ወልድ - ሉቃ15:4
‎መንፈስ ቅዱስ - ኤፌ1:13
‎በሕብረት

‎አብ - ኤፌ2:18
‎ወልድ - 2ቆሮ5:19
‎መንፈስ ቅዱስ - ኤፌ2:18
‎በክብር

‎አብ - 1ቆሮ15:24
‎ወልድ - ፊል3:21
‎መንፈስ ቅዱስ - ራዕ22:17
‎የእግዚአብሔር አብ፣ የእግዚአብሔር ወልድ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ግንኙነት
‎አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ ስሞች ናቸው::

‎አብ የምክር፣ የሀሳብና የፈቃድ ምንጭ የሆነው አካል ነው:: (ኤፌ1:1፣ ሐዋ22:12-14)
‎ወልድ ከአብ የተገኘ አንድያ ልጁና ፈቃዱን፣ ምክሩንና ሀሳቡን ፈጻሚ ሆኖ የሚገለጥ መለኮታዊ አካል ነው:: (ዮሐ1-:-18,ቆላ1:15-22፣ መዝ40:7-10)
‎መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ የሚወጣ የአብና የወልድን ፈቃድ ሞራልና ሐሳብ የሚያስፈጽም መለኮታዊ አካል ነው:: (ዮሐ15:26፣ ኤፌ1:13፣ ዘፍ1:2)
‎አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አይነት መለኮታዊ ባሕርይ፣ እኩል አምላክነትና እኩል ዘላለማዊነት አላቸው:: በምክር አንድ ናቸው፤ በሕልውናቸው አይቀዳደሙም፤ በባሕርይም አይበላለጡም:: አንዱን ስንጠራ ሁሉን እየጠራን ነው፤ አንዱን ስናመልክም ሁሉን እያመለክን ነው:: አንዱ በሚሰራበት ሁሉም በአንድነት ይሰራሉ፤ አንዱ የሚያውቀውንም ሁሉም ያውቃሉ:: የማይለያይ፣ የማይከፋፈልና የማይጨፈለቅ (የማይዋጥ) አንድነት አላቸው:: አንዱ ከሌላው ሳይቀድም ለዘላለም በአድነትና በሦስትነት ይኖራሉ::

‎የእግዚአብሔር አብ፣ የእግዚአብሔር ወልድ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ልዩነት
‎በአካልና በስራ ይለያያሉ:: አብን አብ የሚያሰኘው የአባትነት ባሕርይ ነው፤ ወልድን ወልድ የሚያሰኘው የልጅነት ባሕርይ ነው፤ መንፈስ ቅዱስን መንፈስ የሚያሰኘው የተልዕኮ ባሕርይ ነው:: አብ ወልድ አይደለም፤ አብ መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ አብም ወልድም አይደለም::

‎ስለ ሰው ልጆች ድነት (መዳን) ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ዓለም የላከው አብ ነው::
‎ለሰው ልጆች ኃጢአት በመሰቀል የሞተው በግንባር ቀደምነት ወልድ ነው::
‎በበዓለ ሃምሳ ቀን ለአማኞች ኃይልና መጽናናት እንዲሆን የመጣው መንፈስ ቅዱስ ነው::
‎አብ የራሱ አካል አለው፤ ወልድ የራሱ አካል አለው፤ መንፈስ ቅዱስም የራሱ አካል አለው፡፡ ስለዚህ በአካል ሦስት ናቸው::

‎ጥንቃቄ
‎በዚህ ዓለም በአይናችን በምናያቸው ነገሮች የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለመግለጽ ብቁ ስለማይሆኑ ምስጢረ ሥላሴን በምሳሌ ለማስረዳት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል::

‎👉 አዳዲስ ትምህርታዊ, አስተማሪና ቁምነገር ያለውን መንፈሳዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይህንን ( Page Like Follow share ) እያደረጋችሁ ተከታተሉን


‎የማህበር ምዕመናን ዲጂታል የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ

‎ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለው Page Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
https://tr.ee/VcHXkRfRGI
‎Facebook
https://www.facebook.com/share/1BX2xBEgrx/
‎YouTube
https://www.youtube.com/
‎Telegram
https://t.me/EECMYR70








11/03/2026

With HD Films Production – I just made it onto their weekly engagement list by being one of their top engagers!

Address

Awassa
SIDAMA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HD Films Production posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category