Abelpappy

Abelpappy Best Comedy Images, VideosTrolls and Many More Here.

23/01/2026
ኪን የተለያዩ የእንጨት ስራ ውጤቶችን-ኮፊ ቴብሎች-ቲቪ ስታንዶች-መመገቢያ ጠረቤዛዎች-የኮምፒውተር ዴስክ-የህጻናት አልጋዎች እና የማጥኛ ወንበርና ጠረፔዛ-የሶፋ የመሀል ጠረፔዛ እና የተለያዩ ...
24/11/2025

ኪን የተለያዩ የእንጨት ስራ ውጤቶችን
-ኮፊ ቴብሎች
-ቲቪ ስታንዶች
-መመገቢያ ጠረቤዛዎች
-የኮምፒውተር ዴስክ
-የህጻናት አልጋዎች እና የማጥኛ ወንበርና ጠረፔዛ
-የሶፋ የመሀል ጠረፔዛ እና የተለያዩ ሼልፎችን በተለያዩ ዲዛይንና ጥራት እንዳቅም እንሰራለን።
በተጨማሪም ምርቶቻችንን ለነጋዴዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እናስረክባለን
https://t.me/+aUdcwVmbINNjNmM0
አድራሻችን
22 ከጎላጎል ወደ ሾላ በሚወስደዉ መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ :-0911456160
0939965001

ኦርጅናል ከሚስ ፒሲሲ 1302 ኮንትሮለር Power Command ControllerOriginal Cummins PCC1302 Controller for reliable generator performance...
15/11/2025

ኦርጅናል ከሚስ ፒሲሲ 1302 ኮንትሮለር
Power Command Controller
Original Cummins PCC1302 Controller for reliable generator performance.
Compatible with specific Cummins models, ensuring the right fit.
New condition for optimal functionality.
Includes Generator Control Mainboard Board only.

 ‼️ወቅቱ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ነው። ጃፓን ክፉኛ ተደቁሳለች። ምድር የሬሳ ማሳ ሆናለች። የአሜሪካው ፎቶግራፈር አንድ ህፃን ላይ ቀልቡ አረፈ። ቤተሰቦቹን ያጣ፣ የሞተ ታናሽ ወንድሙን በ...
18/12/2024

‼️

ወቅቱ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ነው። ጃፓን ክፉኛ ተደቁሳለች። ምድር የሬሳ ማሳ ሆናለች። የአሜሪካው ፎቶግራፈር አንድ ህፃን ላይ ቀልቡ አረፈ። ቤተሰቦቹን ያጣ፣ የሞተ ታናሽ ወንድሙን በጀርባው ያዘለ ህፃን። ሐዘኑን በእልህ የዋጠ፣ ላልማልቀስ የጨከነ ህፃን።

ወንድሙን ሬሳ ወደሚቃጠልበት ቦታ ይዞ ሄደ። የሚያቀጥለው ሰው "አምጣ የተሸከምኸውን ነገር ልቀበልህ" አለው።

ህፃኑም በንዴት "የተሸከምሁት ወንድሜን እንጂ ዕቃ አይደለም" አለው። ጨክኖ ከወንድሙ መለዬት አልቻለም። ነገር ግን ማልቀስ አልፈለገም። ከንፈሮቹን ነክሶ ሳጉን ወደ ውስጥ ሞጅሮታል። ይህ ምስል ዛሬ ድረስ በጃፓን እንደ ትልቅ የጥንካሬ ማሳያ ይቆጠራል። ጃፓን ከዚያ በኋላ ላለማልቀስ ወሰነች። እነሆ ላለፉት 80 ዓመታት ጃፓን አላለቀሰችም።

ኢትዮጵያ ሀገሬ መሰል አደጋ ፊቷ ላይ አንዣቧል። ከጦርነቱ ማግስት የሚኖረው የሞራል ስብራት ከባድ ነው። እልፎች ወላጆችን፣ ወንድምን፣ እህትን፣ ልጅን፣ ህፃናትን ያጣሉ።ትንቢት ሳይሆን እውነት ነው። ዛሬም በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች እንደ ሸክላ እየደቀቁ ነው። ነገ የባሰ ያስፈራል። ኢትዮጵያ በየ20 እና 30 ዓመታት ጉዞ፣ ወጣቶቿን እንደ ራባት ድመት ቀርጥፋ የምትበላ ምታተኛ ምድር ናት። መድኃኒት ያጣች የደም ምድር-አኬልዳማ።

መፍትሔው አንድ ነው። ላለማልቀስ መጨከን ነው። ለዚህ ያበቁን ለመሳቅ ሲከጅሉ፣ እኛ ላለማልቀስ መጨከን። ላለማልቀስ ካልተጨከነ፣ ከጦርነቱ ማግስት ያለው የስነልቦና ቀውስ ሌላ ጦርነት ነው። ሌላ የሀገር ስብራት ነው። ዛሬ በስሜት ፈረስ ላይ ሆነን አይታይም። ነገ ቆም ስንል፣ የሁላችንም ምስል የዚህ ህፃን ነው። ማዳን ባንችል፣ ላለማልቀስ እንጨክን-ኢትዮጵያ ትቀጥል ዘንድ🙏
@ዘላለም ጥላሁን

YZ Studio
18/12/2024

YZ Studio

በሚንሳፈፍ በረዶ ላይ የተኛ ድብ የዓመቱ ምርጥ የዱር እንስሳት ፎቶግራፍ አሸናፊ ሆነ በሚንሳፈፍ በረዶ ላይ የተኛ ድብን የሚያሳይ ድንቅ ፎቶ ያነሳው እንግሊዛዊ የዓመቱ ምርጥ የዱር እንስሳት ...
18/12/2024

በሚንሳፈፍ በረዶ ላይ የተኛ ድብ የዓመቱ ምርጥ የዱር እንስሳት ፎቶግራፍ አሸናፊ ሆነ

በሚንሳፈፍ በረዶ ላይ የተኛ ድብን የሚያሳይ ድንቅ ፎቶ ያነሳው እንግሊዛዊ የዓመቱ ምርጥ የዱር እንስሳት ፎቶግራፈር ሽልማትን አሸንፏል።

ጀማሪ የፎቶ ግራፍ ባለሞያ የሆነው ኒማ ሳሪካኒ ሽልማቱን ለማሸነፍ የበቃው በዓመቱ ከተነሱ ውብ እና ጠንካራ መልዕክት ካላቸው የዱር እንስሳት ፎቶዎች ውስጥ በህዝብ ድምጽ ከፍተኛ ውጤት በማግኘት ነው።

ፎቶው እንስሳት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ጋር ያላቸውን ጥብቅ ቁርኝት በማሳየት ምድራችን በዓየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተጋረጠባትን ከባድ አደጋ በጥልቀት እንደሚያስረዳም የእንግሊዙ የተፈጥሮ ታሪክ ሙዚየም ዳይሬክተር ዶ/ር ዳግላስ ጉር ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ የዓለም ሙቀት መጨመር ግግር በረዶን በማቅለጥ በሰዎች እና በእንስሳት ላይ የህልውና አደጋ መደቀኑንም ገልጸዋል።

ኒማ ሳሪካኒ ፍቶውን ለማንሳት ኖርዌይ ውስጥ በሚገኙት እና የአርክቲክ ውቅያኖስ አካል በሆኑት የስቫልባርድ የበረዶ ደሴቶች ለ3 ቀናት እንደተጓዘም ቢቢሲ ዘግቧል።

የልጅ እና የሌኒን ፎቶ፣ ኢትዮጵያ 1991በ1991 በኢትዮጵያ የተነሳው ይህ ታሪካዊ ፎቶ፣ የደርግ መንግስት መውደቅን የሚያሳይ ነው። ፎቶው አንድ ትንሽ ልጅ በወደቀው የሌኒን ሀውልት ፊት ለፊ...
18/12/2024

የልጅ እና የሌኒን ፎቶ፣ ኢትዮጵያ 1991

በ1991 በኢትዮጵያ የተነሳው ይህ ታሪካዊ ፎቶ፣ የደርግ መንግስት መውደቅን የሚያሳይ ነው። ፎቶው አንድ ትንሽ ልጅ በወደቀው የሌኒን ሀውልት ፊት ለፊት ቆሞ የሚታይበት ሲሆን፣ ይህም የሶቭየት ህብረት ተጽእኖ በኢትዮጵያ መቋጫን የሚያመላክት ነው።

በወቅቱ የኢህአዴግ ሃይሎች ደርግን ሲገረስሱ፣ እንደ የሌኒን ሃውልቶች ያሉ የሶቭየት ምልክቶች በርካታዎቹ ተናድው ነበር። ይህ ፎቶ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ ወሳኝ ምዕራፍን የሚያሳይ ሲሆን፣ ከሶቭየት ህብረት ጋር የተሳሰረውን የወታደራዊ ማርክሳዊ አገዛዝ መጨረሻ ያመላክታል።

ፎቶው ያለው የታሪካዊ ፋይዳ ከፍተኛ ነው። አንድ ትንሽ ልጅ በወደቀው የሌኒን ሃውልት ፊት መቆሙ፣ ከአንድ የፖለቲካ ስርዓት ወደ ሌላ የመሸጋገርን ሁኔታ በአምሳያዊ መልኩ ያሳያል። ይህም ከሶቭየት መር ኮሚኒስታዊ አስተዳደር ወደ አዲስ የፖለቲካ ስርዓት የተደረገውን ሽግግር ይወክላል።

ታሪካችን
18/12/2024

ታሪካችን

23/06/2023

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abelpappy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share