30/04/2019
ሴት ሆይ ለትዳርሽ ብቁ ነሽን?
፩ኛ. ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ
{ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
፪ኛ. ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
፫ኛ. ባለቤትሽ በተቆጣ ጊዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት
ከሆነ፣ድምፅሺን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
፬ኛ. ከባለቤትሽ አጠገበ በተቀመጥሽ ጊዜ ጠረንሽ ጥሩ
ካልሆነ፣የልብስሽን ንፅህና ካልጠበቅሽ፣እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
፭ኛ. ከሱጋ በተጣላሽ ወቅት ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
፮ኛ. ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የሱን ቤተሰቦች
መልካምን በማድረግ የማትንከባከቢ ከሆንሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
፯ኛ. በፀሎት ጊዜ እሱን የማትቀሰቅሺ ከሆንሽ፣ ፈጣሪን
በመታዘዝ ላይ የማተበረታቺው ከሆነ፣ ክልክል ነገራቶችን
እንዲተው የማታደርጊ እና ወደ ተውበት የማትገፋፊው ከሆንሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
፰ኛ. ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
ወንድ ሆይ ለትዳርህ በቁ ነህን?
፩ኛ. ሚስትህ ምቾት እና እንክብካቤ ስለምትፈልግ
ካልተንከባከብካት እና ያለህን ነገር በሙሉ ሳትሰስት ካላጋራሃት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፪ኛ. ሚስትህ ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። ባገኘከው አጋጣሚ ከንፈሯን እየሳምክ ፍቅርህን የማትገልፅላት ከሆነ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፫ኛ. ሚስትህ ግትር ባል ትጠላለች። ደካማ ባልን ደግሞ
ትንቃለች አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር መሆንን ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፬ኛ. ሚስትህ መልካም ንግግር፣ ወንዳ ወንድ ገጽታ፣ በስፖርት የተገነባ ሰውንት፣ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ይማርካታል እነዚህን ማድረግ ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፭ኛ. ለሚስትህ ቤቷ ቤተ መንግስት ነው። ይህን ቤተመንግሥቷን ካስደፈርክባት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፮ኛ. ሚስትህ እጅግ በጣም ብትወድህም ቤተሰቦቿን ማጣት አትፈልግም። ቤተሰቦቿን ብትንከባከብ ከነበረው ፍቅር ላይ ሌላ ፍቅር ትጨምራለህ ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፯ኛ. ሚስትህ አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ይህን ባህሪዎቿን ባትወድላት ሌሎች የሚወደዱ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት ከዘነጋህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፰ኛ. ሚስትህ አካላዊ ድካም፣ ተፈጥሯዊ ወይንም ወራዊ ህመም እና ስነልቦናዊ ጫና እየተፈራረቁ ስለሚያጠቋት ልትነጫነጭ ትችላለች። ይህን ዘንግተህ እሷን ከመንከባከብ ፈንታ አንተም እንደሷ ከተነጫነጭክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፱ኛ. ባገኘሁ አጋጣሚ ሚስትህን እቀፍ፣ ሳም፣ ፀጉሯን ወገቧን እሽ ሚስትህ ላንተ ሁሌም ቆንጆ እንደሆንች አስመስክር። ሚስትህ እንደ አንተ አልጋ ላይ የፍቅር ጨዋታ ያምራታል በግልፅ ፍላጎቷን በሚገባ አርካት ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፲ኛ. ሚስትህ እንደ አቅሟ ተውባ እና አጊጣ መታየትን
ትፈልጋለች። የመጀመሪያ የውበቷ አድናቂ ቧልዋ መሆኑን አትዘንጋ ስለዚህ ሁሌም ውበቷን አድንቅላት። ሚስትህ ተውባ እና አጊጣ ማየት ካልፈለክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፲፩ኛ. ደስታን፣ ሀዘንን፣ ችግርን እና ቅሬታን ለሚስትህ በግዜ ንገራት። ደስታውን አመስግኑ። ሀዘኑን ተፅናኑ፣ ችግርን እና ቅሬታን ብቻችሁን በውይይት ፍቱ። ሚስትህን በፍፁም አታኩርፍ እንዚህን መምራት ካቃተህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፲፪ኛ. ሚስትህ ስትናገር እስከመጨረሻው በጥሞና ካላደመጥካት ችግሯን ካልፈታህላት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
፲፫ኛ. ከፈጣሪ ቀጥሎ ከምንም እና ከማንም በላይ መጀመሪያ አንተ፣ ሚስትህ፣ እና ልጆችህን ብቻ አስቀድም። ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት እና ሌላው ከእናንተ ቀጥሎ ናቸው። ይህን ማስተዋል ከተሳነህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
መልካም ትዳር!!!
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»