Gurage Amard

Gurage Amard የጉራጌ ባህልና እሴቶች እና ወቅታዊ መረጃዎች በሚዛናዊነት የሚቀርብበት የህዝብ ሚዲያ ነው

 በጉራጌ ዞን የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የወልቂጤ ምርጫ ክልል ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ ። #ወልቂጤ| ግንቦት 30/2018 ዓ.ምበጉራጌ ዞን የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የወልቂጤ ...
07/06/2026



በጉራጌ ዞን የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የወልቂጤ ምርጫ ክልል ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ ።

#ወልቂጤ| ግንቦት 30/2018 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የወልቂጤ ምርጫ ክልል ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ ሆኗል ።

የወልቂጤ ምርጫ ክልል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ ጀማል ግንቦት 24/የተደረገው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን ገልፀዋል።

በወልቂጤ የምርጫ ክልል ውስጥ 141 የምርጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ ገልፀው ከድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኃላ 141 የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ተሰብስቦ የማጠቃለል ስራ ሲሰራ እንደነበረ ተናግረዋል ።

በዛሬው ዕለትም ጥቅል ውጤቱን የማጠቃለል ስራ በማጠናቀቅ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ መደረጉን ገልፀዋል።

በዚህም በምርጫ ክልሉ ውስጥ 166,589 ህዝብ የምርጫ ካርድ እንደወሰዱ ገልፀው ከዚህ ውስጥ 156,291 ህዝብ ድምፅ እንደሰጠ ገልፀዋል።

በዚህም መሠረት በወልቂጤ ምርጫ ክልል

✅ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ከቀረቡት መካከል የተመዘገበው ውጤት

👉ሙአዝ በድሩ ሁሴን(ዶክተር) ብልፅግና ፓርቲ =142,456
👉መሀመድ አብራር መሀመድ ጎጎት ለጉራጌ አንድነት ፓርቲ =5198
👉መስፍን አበራ አብዛ ከነጻነትና እኩልነት ፓርቲ= 692
👉ደምስ ገብሬ መረቶ ከኢዜማ ፓርቲ=2211
👉ኢክራም ሰይፍ በሽር ከወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ= 547
👉አዲሱ ደቀባሽ አበበ ከወሎ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ=380
👉እንዳለ ኤርገንዶ ጥሊቦ ከትብብር ለኢትዮጵያ=439
ድምፅ ማግኘታቸውን ተገልጿል።

✅ለክልል ምክር ቤት

📌 ሙራድ ከድር መሀመድ ብልፅግና ፓርቲ =144,751
📌ዙልፋ አለዊ ነጋሽ ብልፅግና ፓርቲ = 142,850
📌ኢንጂነር ካሳዬ ተክሌ ስራ ብልፅግና ፓርቲ =142,367
📌መሀመድ አሚን በደዊ ነጋሽ ብልፅግና ፓርቲ =142,262
📌ካሱ ጁሀር ስንክርታ ብልጽግና ፓርቲ=142,071

📌ሳራ ጀማል ሻፊ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ=1,269
📌ሰማን አብድላ አህመድ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ=1,113

📌ማእረግ ፍቃዱ ናማጋ ጎጎት ለጉራጌ አንድነት ፍትህ ፓርቲ =2,833
📌ፍቃዱ ጠንክር ኬራጋ ጎጎት ለጉራጌ አንድነት ፍትህ ፓርቲ= 2,803
📌አንተነህ ኮሬ አጨ ጎጎት ለጉራጌ አንድነት ፍትህ ፓርቲ= 2,514
📌አብድላዚዝ ሙሰማ ሀሰን ጎጎት ለጉራጌ አንድነት ፍትህ ፓርቲ= 2,279

📌ሂክማ አብራህማን አረጋ ኢዜማ ፓርቲ= 2,162
📌አንተነህ ተስፋዬ ገ/ስላሴ ኢዜማ ፓርቲ= 2,446
📌ዳንኤል ኸ/ጊዮርጊስ ወጋየሁ ኢዜማ ፓርቲ= 2,172
📌ፈድሉ አህመድ በሽር ኢዜማ ፓርቲ= 1,981

📌ሙሀባ ግራኝ ሻፊ ከወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ= 905
📌አህመድ ጀማል ማረኝ ከወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ= 497
📌ሙክታር መኪ ነጋሽ ከወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ= 283

ድምፅ መሆኑን ጊዜያዊ የወልቂጤ ምርጫ ክልል ውጤት ያሳያል።

ዘገባው የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ወቅታዊ የትራንስፖርት ዋጋ ንረትና የህዝቡ እሮሮ​በአገራችን በአሁኑ ወቅት የነዳጅ እጥረት መከሰቱ የማይካድ ሀቅ ነው። ይሁን እንጂ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም አንዳንድ የትራንስፖርት አገልግሎት...
13/04/2026

ወቅታዊ የትራንስፖርት ዋጋ ንረትና የህዝቡ እሮሮ
​በአገራችን በአሁኑ ወቅት የነዳጅ እጥረት መከሰቱ የማይካድ ሀቅ ነው። ይሁን እንጂ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም አንዳንድ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የሚያደርጉት ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በዝቅተኛው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ ይገኛል።

​ከዚህ በፊት 600 ብር የነበረው የጉዞ ታሪፍ፣ አሁን ላይ 2,500 ብር ደርሷል። ይህ ማለት ከአራት እጥፍ በላይ ጭማሪ ተደርጓል ማለት ነው። ነዳጅ ለማግኘት ረጅም ወረፋ መቆም ወይም በእጥፍ ዋጋ መግዛት እንደ ምክንያት ቢቀርብም፣ ጭማሪው ግን ካለው ሁኔታ ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠንና "አይን ያወጣ" ብዝበዛ ነው።
​በጉራጌ ዞንና አካባቢው ያለው ተጨባጭ ሁኔታ
​በተለይ ከጉራጌ ዞን ተነስተው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በሚጓዙ መስመሮች ላይ ያለው የዋጋ መናር የህዝቡን ምሬት አባብሶታል። ተጓዦች አማራጭ በማጣታቸው ብቻ የተጠየቁትን ያህል ለመክፈል ቢገደዱም፣ ይህ አሰራር ግን የነዋሪውን የኑሮ ጫና ከመቼውም ጊዜ በላይ አክብዶታል።
​ሀገሪቱ ካለችበት አጠቃላይ የኑሮ ውድነት አንጻር፣ የትራንስፖርት ዋጋ በዚህ ልክ መጨመሩ ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የማይቻልበት ደረጃ ላይ አድርሶታል። የምግብ ዋጋ፣ የቤት ኪራይና ሌሎች አገልግሎቶች በናሩበት በዚህ ወቅት፣ የትራንስፖርት ዘርፉም ያለምንም ቁጥጥር የፈለገውን ያህል ዋጋ መቆለሉ ፍፁም ግፍ ነው።
​ጥሪ ለሚመለከታቸው አካላት
​ የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላትና የትራንስፖርት መቆጣጠሪያ ክፍሎች በየደረጃው ያለውን የዋጋ ጭማሪ በጥብቅ እንዲከታተሉ ጥሪ እናቀርባለን።
​ካለው የነዳጅ እጥረትና ወጪ ጋር የሚመጣጠን፣ ነገር ግን ህዝቡን የማይበድል ግልጽ የታሪፍ ማስተካከያ ተደርጎ ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል።
​ የነዳጅ እጥረቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ህዝብን የሚያማርሩ አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን።

ማንም ሰው ከዚህ ቀደም በነበረው ታሪፍ ይሰራ አይልም፤ ነገር ግን አራት እጥፍ መጨመር የችግሩ ተካፋይ መሆን ሳይሆን ሆን ብሎ ህዝብን ማስመረር ነው። የዜጎች የመንቀሳቀስ መብት በገንዘብ እጥረት እንዳይገደብና የኑሮ ውድነቱ ክንድ እንዳይበረታ አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልጋል።

© ወልቂጤ ሚዲያ

"ኩርፍወ" የጉራጌ ልጃገረዶች ልዩ የሆነ ባህላዊና መንፈሳዊ ይዘት ያለው ከሰሞነ ሕማማት እስከ ዳግመ ትንሣኤ ድረስ የሚከወን ጨዋታ ነው፦አቶ ክፍሌ ቸገን መጋቢት 28/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)...
06/04/2026

"ኩርፍወ" የጉራጌ ልጃገረዶች ልዩ የሆነ ባህላዊና መንፈሳዊ ይዘት ያለው ከሰሞነ ሕማማት እስከ ዳግመ ትንሣኤ ድረስ የሚከወን ጨዋታ ነው፦አቶ ክፍሌ ቸገን

መጋቢት 28/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)

ኩርፍወ ልጃገረዶች አምባሬ የተሰኘውን ለምለም ተክል ቅጠል ከስሩ ነቅለው ሸንሽነውና አስጊጠውት ወገባቸው ላይ አስረው እጆቻቸው ዘርግተው ልክ እንደ ቁም ለቅሶ እግራቸው ከመሬት ከፍ አርገው እየዘለሉ አውራጇ አምባሬ ኩርፍወ እያለች ስታወርድ ሌሎችም ዋይ ዋይ እያሉ በመቀባበል እያዜሙ የሚጫወቱት የጨዋታ አይነት ነው።

የኩርፍወ ጨዋታ ከሰሙነ ሕማማት ተጀምሮ እስከ ዳግም ትንሳዔ ድረስ የሚቆይ የጨዋታ አይነት መሆኑን የምሁር አክሊል ወረዳ ባህል ቱሪዝም ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ቸገን ገልጸዋል።

በዓሉ ከጥንት አያቶቻችን ጀምሮ የነበረ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ አንስቶ እየተረሳ የመጣ ቱባ ባህል መሆኑን አንስተው ባህላዊ እሴቱ እርስ በርስ የሚያገናኝ ስለሆነ ይህ ቱባ ባህል ዳግም እንዲያንሰራራ ተቋሙ አበክሮ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኩርፍወ በዓል ሀይማኖታዊ ዳራና ባህላዊ ይዘቶች አካቶ የያዘ ድንቅ በዓል ሲሆን ልጃገረዶች በዓሉ በሚያከብሩበት ሰዓት ሲደሰቱም አንድ ጊዜ ሲያዝኑ የሚስተዋልበት ሁኔታ እንዳለ ጠቁመዋል።

ሀይማኖታዊ ይዘቱ በሰሙነ ህማማት የሚሆንበት ምክንያት እየሱስ ክርስቶስ በአይሁዳውያን የደረሰበት መከራ፣ ስቃይና ሞት መነሻ በማድረግ ልጃገረዶች በወገባቸው አምባሬ ሚባለው ከስር አሚቾ ያለው ለምለም ሳር በወገባቸው በማሰርና በእጃቸው በመያዝ እያወዛወዙ ሀዘኑ የሚገልፁበት መንገድ ሲሆን አለፍ ብሎ የክርስቶስ ትንሳዔ መሰረት በማድረግ ሀዘኑን ተሻግረው ሲደሰቱ በትዕይንት እንደሚያስረዱ ተናግረዋል።

ጨዋታው በአንድ በኩል ሀዘን መሰል በሌላ በኩል የክርስቶስ ትንሳዔ መነሻ በማድረግ ደስታቸውና ሀዘናቸው ለመግለፅ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቱ በጠበቀ መልኩ የሚያከብሩት በዓል መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል።

የዳግም ትንሳዔ ዕለት የኩርፍወ ፕሮግራም ማብቂያ ሲደረግ ልጃገረዶች አምባሬ ሚባለውን ከስር አምቾ ያለው አረንጓዴ ለምለም ሳር በመያዝ አምቾው ወንዶች በማያገኙት ቦታ ላይ ይቀብሩታል የደበቁትን አምቾ ወንዶች ካላገኙት የልጃገረዶች የወደፊት መፃኢ ዕድል ብሩህ ተስፋ እንዳላቸው የሚያሳይ ባህላዊ መገለጫ እንዳለው ጠቅሰዋል።

የዚህ ፕሮግራም ዋና አላማው ኩርፍወ የተሰኘው ባህላዊ ዳራ ያለው ድንቅ ጭፈራ እየጠፋ ከነበረበት ለመታደግ እና በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ እንዲሰርፅ በማድረግ በየአመቱ እንዲከበር እና የቱሪስት መስህብ ማድረግ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል።

ጨዋታው እየተተው በመምጣቱ ለመጥፋት ተቃርቦ እንደነበር በመግለፅ ጽ/ቤቱ ለተከታታይ አመታት በእናቶች በኩል ልጃገረዶቹ ባህሉን እንዲለምዱት ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ካለፋት ዓመታት ጀምሮ በልጃገረዶች እንዲከወን በማድረግ አሁን ላይ ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

በመጨረሻም ይህ በዓል ከጥንት ጀምሮ በምሁር አክሊል ወረዳ ልጃገረዶች አንድ ላይ በመገናኘት ስለህይወታቸው የሚመካከሩበት በድምቀት የሚያከብሩት ቱባ ባህል መሆኑን ማህበረሰቡ ተገንዝቦ ወደ ፊት ይህ ጨዋታ በየዓመቱ በደመቀና ባህላዊ ይዘቱ በጠበቀ መልኩ እንዲካሄድ የሁላችንም ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቶ ክፍሌ አሳስበዋል።

የኩርፍወ በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቶች አጣምሮ የያዘ ልዩ ትዕይንት እንደሆነና በጭፈራው እጃቸውን አንስተው በማወዛወዝ በዜማ እያዜሙ በዓሉን በድምቀት እንደሚያከብሩት ወ/ሪት ሀይማኖት እና ወ/ሪት ጽዮን ተናግረዋል።

ኩርፍወ በየዓመቱ በሰሙነ ሕማማት ተጀምሮ እስከ ዳግም ትንሳኤ ድረስ ባሉት ቀናቶች በልጃገረዶች እየተዘፈነ የሚቆይ ባህላዊ የጨዋታ ዓይነት ነው።

ይህም በአካባቢው ባህል መሰረት በጣም ታዋቂና ክብር ያለው ሰው በሚሞትበት ሰዓት የሚደረግ ልዩ ባህላዊ ለቅሶ ሲሆን ይህ ደግሞ ከእየሱስ ክርስቶስ መከራ፣ ስቃይና ሞት አስመለክቶ የሚደረግ ክዋኔ መሆኑን ጠቅሳለች።

በሌላ በኩል በከበሮ በዜማና ጭፈራ ወጣት ወንዶች በተገኙበት ይደሰታሉ ይጨፍራሉ ይህ ከክርስቶስ ትንሳዔ ጋር እንደሚያያዝም አንስተዋል።

ከሚዜመው ዜማ መካከል

አውራጇ ተቀባይ
ኩርፍወ ኩርፍወ(2) ኤዋዬ ኩርፎ
ኩርፍወ በሞቴ ""
ሁትም ባማማቴ ""
ኩርፎ ኩርፎ ዋዬ ኩርፎ
ኩርፎ ሞቴም ""
ባማማቴ ""
ጎር ቲገባ ዘር የገባ እያለ ይቀጥላል።

ዘገባው የምሁር አክሊል ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው

  ንግዱን ከአረቦች ወደ ጉራጌዎች ያዞረ ጀግና‼️   በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጣልያንን ድል ካደረግን በሗላ ንግዱን የተቆጣጠሩት የመናውያን አረቦች ነበሩ እነኝህ አረቦች ንግዱን ከመ...
06/04/2026

ንግዱን ከአረቦች ወደ ጉራጌዎች ያዞረ ጀግና‼️

በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጣልያንን ድል ካደረግን በሗላ ንግዱን የተቆጣጠሩት የመናውያን አረቦች ነበሩ እነኝህ አረቦች ንግዱን ከመቆጣጠራቸው ባሻገር በገንዘብና በተለያዩ መንገዶች ኢትዮዽያውያን ሴቶችን እያማለሉ ካስወለዱ በሗላ አብዛኞቹ ከነልጆቻቸው ሜዳ ላይ ጥለዋቸው ወደ ሀገራቸው ይሄዱ ነበር::
በወቅቱ የነበረው ማህበረሰብ እነኝህ ከአረብ የወለዱ ሴቶች በማለትና በማግለል ለቤት ለሰራተኝነት እንኳን አይቀጥሯቸውም ነበር:: እንዲሁም እነኝህ የየመን አረብ ነጋዴዎች ሸቀጦችን በፈለጉት ዋጋ እይሸጡ ኢኮኖሚውን ተቆጣጥረውት ስለነበር ጉዳዩ አሳሳቢ ሆነ::

የህዝቡን መማረር የተረዳው መንግስት በወቅቱ የእርሻና ንግድ ሚኒስቴር የነበሩት ይህን ጉዳይ የሚያጠና ኮሚቴ አቋቁመው መምከር ጀመሩ በወቅቱ የኮሚቴው አባል እና ቃለ ጉባኤ ያዥ የነበረው አንድ ዘዴ ይዘይድና ለክቡር ሚኒስትር መኮንን ሀብተወልድ ደብዳቤ ይፅፋል የደብዳቤው ይዘት እነኝህን አረቦች ዝም ብለን ብናባርራቸው የኢትዮዽያ ዲፕሎማሲ አደጋ ውስጥ ይወድቃል ስለዚህ እኔ ተወልጄ ያደግኩባቸው የጉራጌ ተወላጆች በስራ ታታሪዎች ሲሆኑ በንግድም የተዋጣላቸው ናቸው ለእነሱ የንግድ ቦታዎችና የተወሰነ መንቀሳቀሻ የሚሆን የገንዘብ ብድር ብናመቻችላቸው ንግዱን መቆጣጠር ይችላሉ ብሎ ይነግራቸዋል እሳቸውም ከሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ጋር ከመከሩ በሗላ #በሩጋ ሀሳብ ይስማማሉ::

በዚሁ መሰረት ብዛታቸው 40 የሆኑ የጉራጌ ተወላጆችን ለእያንዳንዳቸው 700/ሰባት መቶ ብር/ ጠቅላላ ድምር 28,000 /ሀያ ስምንት ሺህ ብር/ ብድር በመስጠት ከተለያየ ቦታ የጉራጌ ተወላጆችን በማስተባበር መርካቶን ጨምሮ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ከአረቦቹ ሱቅ አጠገብ ሌላ ሱቅ በመክፈት እና አረቦቹ ከሚሸጡበት ዋጋ ቅናሽ በማድረግ ገበያውን ተቆጣጠሩት::

ለበርካታ አመታት አረብ ሱቅ በመባል የሚታወቀውን አረቦች በብቸኝነት ይዘውት የነበረውን ንግድ ያለምንም ደም መፋሰስ: አንድ ጥይት እንኳን ሳይተኮስ ህዝባችንን ሲበዘብዙና ሴት እህቶቻችንን አስወልደው ሜዳ ላይ ጥለዋቸው ሲሄዱ የነበሩ የየመን አረቦችን በስራ ብቻ የጉራጌ ነጋዴዎችን መፎካከር አቅቷቸው በዝረራ ተሸንፈው ሰቆቻቸውን ለጉራጌ እየሸጡ ወደ ሀገራቸው ሄዱ::

ይህ እንዲሳካ በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት የነበሩ ሚኒስትሮችን ያሳመነ እንዲሁም የጉራጌ ተወላጆች ለስራ ያላቸውን እውቀትና ጥንካሬ እንዲጠቀሙበት ያመቻቸው ጀግና ይባላል::

#ምንጭ:-አምባሳደር ዘውዴ ረታ "የቀዳማዊ ሀይለስላሴ መንግስት" ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ ሲሆን አባቶቻችንም ይህን ታሪክ ነግረውናል::
Misbah Kedir✍️

ትዝብቴ ላጋራቹ!.....የጉራጌ ባህል ሲባል ካድሬ ከፊት እና ከኋላ ገጭ የዘመናት ተመሳሳይ አንድ አይነት ሰው: 🖍የጉራጌ አንድነት መድረክ ሲባል ተመሳሳይ አንድ አይነት ሰው: 🖍የጉራጌ ባለድ...
04/04/2026

ትዝብቴ ላጋራቹ!.....
የጉራጌ ባህል ሲባል ካድሬ ከፊት እና ከኋላ ገጭ የዘመናት ተመሳሳይ አንድ አይነት ሰው:
🖍የጉራጌ አንድነት መድረክ ሲባል ተመሳሳይ አንድ አይነት ሰው:
🖍የጉራጌ ባለድርሻ ሲባል ተመሳሳይ ያው አንድ አይነት ፊት ከዃላ እና ከፊት ዘጭ:
🖍የጉራጌ ልማት ሲባል ተመሳሳይ አንድ አይነት ፊት:
🖍የጉራጌ ቅርስ ሲባል አንድ አይነት ሰው አንድ አይነት ፊት
🖍የጉራጌ ታሪክ ሲባል ያው የ20/የ35 ዓመት ያው ተመሳሳይ ፊት ነው። እረ ብዙ መዘርዘር ይቻላል!
〰እኔ ከእናንተ አብሬ ማህበር መጠጣት አምሮኝ ማህበር አጡጡኝ እያልኩ አይደለም ግን እስኪ ወጣቶች በማህበረሰባቸው ጉዳይ አሳትፏቸው። :ሙህራን; አርቲስቶች; የባህል; የፖለቲካ: የታሪክ ሰዎች : ሲቭል ማህበራት እና ሙህራን እንደ ዘርፋቸው ሃሳብ ቢያዋጡ እናተርፋለን!
የጉራጌ እጣ ፈንታ ለዘመናት በጥቂት ነባር ካድሬ ፈላጭ ቆራጭነት ብቻ አይሁን። ጠቅላይነት ለማንም አይጠቅምም። ጉራጌነት የጋራችን የሁላችን ነው! ብቃት እና ንቃት ያለው ካድሬ ምንም የለም ባልልም በተለይ መደበኛ የመንግስት ፕሮግራሞች ሳይሆን ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ጠቅላላው በካድሬ ጋጋታ ብቻ አይሁን! ጉራጌነት የጉራጌው ሁሉ እንጂ እናንተ በስልጣን ላይ ያላቹ የጥቂቶች የግል ተቋም አይደለም! ከዘመኑ ጋር ለመዋጀት ሞክሩ!
ታረቀኝ ደግፍ እንደከተበው

በጉራጌ ውስጥ ከ56 በላይ የእንሰት ዝሪያዎች መኖራቸውን ያውቃሉ?እርሶ አንድ የእንሰት አይነት ይጥቀሱእኔ "ፈረዝየ" እንሰት ብያለሁ
02/04/2026

በጉራጌ ውስጥ ከ56 በላይ የእንሰት ዝሪያዎች መኖራቸውን ያውቃሉ?

እርሶ አንድ የእንሰት አይነት ይጥቀሱ

እኔ "ፈረዝየ" እንሰት ብያለሁ

በጣም_አሳዛኝ_ዜና -ህፃን_በጅብ_ተበላ ዛሬ ጠዋት በቀን 13/7/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ድንቁላ ከተማ አካባቢ ህጻን ልጅ በጅብ ተበልቷል።ወቅቱ ዝናባማና ጫካ ስለበዛ ለህፃ...
22/03/2026

በጣም_አሳዛኝ_ዜና -ህፃን_በጅብ_ተበላ

ዛሬ ጠዋት በቀን 13/7/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ድንቁላ ከተማ አካባቢ ህጻን ልጅ በጅብ ተበልቷል።

ወቅቱ ዝናባማና ጫካ ስለበዛ ለህፃናቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ እናድርግላቸው።
ወላጆች ህጻናት ከትምህርት ቤት ጀምሮ ለብቻቸው ባለመላክ ከፍተኛ ጥንቃቄ እናድርግ .

ያዝልቅላቹ ከማለት ውጪ ምን ይባላል
19/03/2026

ያዝልቅላቹ ከማለት ውጪ ምን ይባላል

ኪም ጆንግ ኡን በፓርላማ ምርጫ 100 በመቶ ድምፅ ማግኘት ተስኖአቸው 99.93 በመቶ ብቻ በማገኘታቸው በአካል ይቅርታ ጠየቁ።መሪው በውጤቱ "በጣም ማዘናቸውን" የገለጹ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ጊዜ...
19/03/2026

ኪም ጆንግ ኡን በፓርላማ ምርጫ 100 በመቶ ድምፅ ማግኘት ተስኖአቸው 99.93 በመቶ ብቻ በማገኘታቸው በአካል ይቅርታ ጠየቁ።

መሪው በውጤቱ "በጣም ማዘናቸውን" የገለጹ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ጊዜ 100 በመቶ ድምፅ ለማግኘት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ድምፅ ያልሰጧቸው እነዚያ 0.07 በመቶ ሰዎች "ምንም ዓይነት አድልዎ (discrimination) አይደርስባቸውም" ሲሉ ቃል ገብተዋል።

እናስተውል!!ዛሬ ላይ የምንመርጣቸው ሰዎች ነገ ላይ በእኛ ጉዳይ የሚወስኑ ሰዎች እንደሆኑ ማሰብ ያስፈልጋል።ስለዚህ ጉራጌዎች ልጆችህን ለይተህ ደግፍ
13/03/2026

እናስተውል!!
ዛሬ ላይ የምንመርጣቸው ሰዎች ነገ ላይ በእኛ ጉዳይ የሚወስኑ ሰዎች እንደሆኑ ማሰብ ያስፈልጋል።
ስለዚህ ጉራጌዎች ልጆችህን ለይተህ ደግፍ

Address

Addis Ababa
1212

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Amard posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category