Amard Ethiopia

Directions

Amard Ethiopia ለህዝብ የመረጃ ቋት ሆኖ የሚያገለግል

ዜና መቀሌ ዙሪያህገ ወጡ የህወሃት ቡድን ሀገር ለማተራመስ ረዥም ጊዜ ሲዘጋጅ የቆዬ የጥፋት ቡድን መሆኑ ይታወቃል።በርካታ የሠው ሃይሉ ሙት ቁስለኛና ምርኮኛ የሆነበት ህገ ወጡ ህወሃት ለመገመ...
07/10/2026

ዜና መቀሌ ዙሪያ

ህገ ወጡ የህወሃት ቡድን ሀገር ለማተራመስ ረዥም ጊዜ ሲዘጋጅ የቆዬ የጥፋት ቡድን መሆኑ ይታወቃል።

በርካታ የሠው ሃይሉ ሙት ቁስለኛና ምርኮኛ የሆነበት ህገ ወጡ ህወሃት ለመገመት የሚያሥቸግር የተለያዬ ዓይነት መሣሪያና ተተኳሾች ተማርኳል። ይህ ቡድን በመቀሌና አካባቢው የደበቃቸው T62 እና T72 ታንኮችና 107 ሚ.ሜ መድፍ በሠራዊቱ ቁጥጥር ስር ሆነዋል።

በጉራጌ ዞን አገና ከተማ በመንግስትና በባለሀብት ትብብር ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ እጅግ ዘመናዊ የገበያ ስፍራ ለመገባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክ...
28/09/2026

በጉራጌ ዞን አገና ከተማ በመንግስትና በባለሀብት ትብብር ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ እጅግ ዘመናዊ የገበያ ስፍራ ለመገባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ የመሰረት ድንጋዩን ባኖሩበት ወቅት እንዳሉት ተወላጅ ባለሀብቶቻችን የተወለዱበት አካባቢን በማልማት እያሳዩት ያለው ቁርጠኝነት እጅግ በጣም የሚበረታታና የሚያስመሰግናቸው ነው።

በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች ከባለሀብቶችና ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የጉራጌ እናቶችን የሚመጥኑ ገበያዎችን ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

የቲናው አበባ እርሻ ልማት መስራችና ባለቤት አቶ ተስፋዬ ገብረህይወት በዞኑ ኢንቨስትመንት ብዙም ባልተስፋፋበት ወቅት ወደ ዞኑ በመምጣት በአበባ እርሻ ልማት በመሰማራት ለብዙ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠርም ባሻገር ህብረተሰቡ በተለያዩ ልማታዊ ስራዎች እያገዙ መሆናቸውን በመግለፅ ዛሬም ከባልደረባቸው ሸነን አጅየት አብነት ቴኒ ጋር በመሆን በአገና ከተማ የጉራጌ እናቶችን የሚመጥን ገበያ ለመገንባት በመወሰናቸው አመስግነዋል።

ሸነን አጅየት አብነት ቴኒ የጉራጌ እናቶችን ስቃይ የኔም ስቃይ ነው በማለት የጉራጌ እናቶች ሲሸጡም ሆነ ሲሸምቱ ጭቃ፣አቧራ፣ፀሃይም ሆነ ዝናብ ሊያሳቃያቸው አይገባም በማለት ከወንድማቸው ተስፋዬ ጋር በመሆን ይሄንን ሞዴል ስራ ለመስራት በመወሰናቸው በእናቶች ስም ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የጉራጌ እናት የኢትዮጵያ እናት ናት ያሉት ክቡር አስተዳዳሪው ለእኛ የሚገባንን ሰጥታን የሚገባትን ያልሰጠናት ናት በማለት በቁጭት ተናግረዋል።

ዛሬ የእናቶቻችን ስቃይን የሚቀንስና ክብራቸውን የሚመልስ ተግባር ለመስራት በተነሳሳችሁ ባለሀብቶች ኮርተንባችኋል በማለት ሌሎችም ባለሀብቶቻችን በትውልድ አካባቢያቸው ተመሳሳይ ስራዎችን እንዲሰሩ በእናቶች ስም ጥሪ አቅርበዋል።

የአገና ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ በበኩላቸው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የጉራጌ እናቶችን የሚመጥኑ ገበያዎች በሁሉም አካባቢዎች እንዲሰሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በከተማችን እውን እንዲሆን ለጀመሩ ባለሀብቶች አመስግነዋል።

የአገና ገበያ ታዋቂና የብዙ እድሜ ባለፀጋ ቢሆንም በሚፈለገው መጠን ባለመልማቱ እናቶች ሲቸገሩ እንደነበርም አውስተዋል።

ባለሀብቶቹ አቶ ተስፋዬ ገብረህይወትና ሸነን አጅየት አብነት ቴኒ በበኩላቸው በቀጣይ በዞኑ ህዝብን ተጠቃሚ በሚያደርጉ በልማት ስራዎችና በኢንቨስትመንት በስፋት እንደሚሰማሩ በመግለፅ ሌሎችም ባለሀብቶች ህብረተሰቡን ሊያግዙ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

መስቀል በጉራጌ የደስታ ጊዜ
27/09/2026

መስቀል በጉራጌ የደስታ ጊዜ

መስቀል በቤተ-ጉራጌበቤተ- ጉራጌ መስቀል የአንድ ቀን በዓል አይደለም፡፡ ከ10 ቀናት በላይ የሚወስድ ልዩ የደስታ በዓል ነው ፡፡ መስቀል በቤተ ጉራጌ በአቡነ ዜና ማርቆስ ገቢረ ተዓምራት ምክ...
25/09/2026

መስቀል በቤተ-ጉራጌ

በቤተ- ጉራጌ መስቀል የአንድ ቀን በዓል አይደለም፡፡ ከ10 ቀናት በላይ የሚወስድ ልዩ የደስታ በዓል ነው ፡፡ መስቀል በቤተ ጉራጌ በአቡነ ዜና ማርቆስ ገቢረ ተዓምራት ምክንያት እንደተጀመረ ይነገራል ። በዓሉ በጉራጌዎች ዘንድ የተለየ የአከዋወን ሥርዓት አለው።

ከመስከረም 12 በፊት የጉራጌ ብሄር ተወላጆች፤ ከመላው የሀገሪቱ ክፍል ወደ ትውልድ ስፍራቸው ይተማሉ፡፡ ከወጣቶች በሰው እስከሚደገፉ አዛውንቶች ድረስ የመስቀል ሰሞን ሀገር ቤት የመግባታቸው ነገር አያጠያቅም፡፡ መስቀል በጉራጌ ሃይማኖታዊ በዓል፣ የመተጫጫ ወቅት፣ የቤተሰብ የዘመድ አዝማድ መጠያዬቂያ፣ የእርቅ እና የአንድነት አውድ ስለሆነ መች በደረሰ እየተባለ በናፍቆት የሚጠበቅ በዓል ነው፡፡

መስከረም 13 ወሬት ያህና በተሰኘው የበዓል መክፈቻ መሰናዶ ሰሞነ መስቀል ይጀመራል፡፡ ወሬት ያህና ጉጉት እና ናፍቆት የፈጠረውን እንቅልፍ አልባ ቀን የሚዘክር ቃል ነው፡፡

መስከረም 14 የእርድ ዋዜማ ሲሆን የልጆች የደመራ ፣ የሴቶች የአይቤ እና ጎመን ቀን ይባላል፡፡ ቤቶች የሚሰነዳዱበት የእንፋሎት ቆጮ የሚቀርብበት ቀንም ነው፡፡

መስከረም 15 ዋናው የጉራጌ የመስቀል በዓል (ወኀምያ ) ነው፡፡ በዚህ ዕለት እርድ ይፈጸማል፡፡ መስከረም 16 ምግይር ወይም ደመራ የሚባለው ቀን ነው ፡፡ በየቤቱ፤ ጥዋት የህጻናት፣ ማታ ደግሞ የአባቶች ደመራ ይለኮሳል፡፡ በዚህ ዕለት ከብቶች ከቤት አይወጡም፡፡

መስከረም 17 ንቅባር ወይንም ትልቁ በዓል ነው፡፡ ዘመድ አዝማድ ሻኛ አስመርቆ በጋራ የሚቋደስበት፣ ጎረቤት በአንድ ሆኖ ሲስቅ ሲያወካ የሚውልበት የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ቀን ነው፡፡

ከመስከረም 18 እስከ 23 የጀውጀው የሚባለው ስርዓት ይቀጥላል፡፡ የጀውጀው የመተያያ ቀን ሲሆን ባለትዳሮች ስጦታ እና መመረቂያ ይዘው የወላጆቻቸውን ቤት በማቅናት የሚጠይቁበት ነው፡፡

የመዝጊው በዓል አዳብና ይባላል፡፡ አዳብና ጎረምሶች እና ልጃገረዶች የጭፈራ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት፤ የወደፊት የትዳር ተጣማሪያቸውን የሚያዩበት፣ የሚያጩበት በዓል ነው፡፡ ጭፈራው ለተወሰኑ ቀናትን ሊቀጥል ይችላል፡፡

ሁሉም የብሄረሰቡ አባላት የሚሳተፉበት የመስቀል በዓል የሚያካትታቸው ክንውኖች ካለ ምርቃት እና መልካም ምኞቶች አይደመደሙም፡፡ የዕድሜ ባለጸጎች "የሀገራችንን ዳር ዳር ለጠላት እሳት፤ ለህዝቦቿ መሃሏን ገነት ያድርግልን" ከሚለው ምርቃት ጀምሮ፤ ሰው፣ ከብቱ፣ ጋራ እና ሸንተረሩ ሰላም እና ልምላሜ፣ በረከት እና ጸጋ እንዳይለየው ይመረቃል፡፡ ታዳሚውም የአባቶችን ምርቃት እየተከተለ "አሜን!" ይላል፡፡

የመስቀል በዓልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እየገቡ የሚገኙ እንግዶች ድባብ በምስል በከፊል
24/09/2026

የመስቀል በዓልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እየገቡ የሚገኙ እንግዶች ድባብ በምስል በከፊል

አርዓያ ሰብየልማት አርበኛው ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋልማት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው በሚል መርህ ተነስተው ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው የሚበጅ ተግባር በማከና...
13/09/2026

አርዓያ ሰብ
የልማት አርበኛው ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ

ልማት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው በሚል መርህ ተነስተው ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው የሚበጅ ተግባር በማከናወን የልማት አርበኝነትን በተግባር ከሚያሳዩ ዜጎች መካከል ከቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አንዱ ናቸው።

አምባሳደሩ በምስጋናው በጎ አድራጎት ድርጅት አማካኝነት በጉራጌ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች፣ በተለይም በትምህርት ልማት ዘርፍ፣ ትውልድ ተሻጋሪ አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ። የእርሳቸው አስተዋጽኦ ዛሬን ብቻ የሚያገለግል ሳይሆን፣ የነገውን ትውልድ ዕውቀትና ብቃት ለመገንባት የሚያግዝ ነው።

በእኖር ወረዳ የትምህርት ዘርፍ ያደረጉት አስተዋጽኦም የዚህ በጎ ተግባር ግልጽ ማሳያ ነው። የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የመማሪያ ቁሳቁሶችን በማበርከትና በመብራት እጥረት ውስጥ በሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች ለሚማሩ ተማሪዎች የሶላር ድጋፍ በማድረግ፣ ተማሪዎች በተሻለ የመማሪያ ሁኔታ እንዲማሩ እያደረጉ ነው። ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ላፕቶፖችንና ሌሎች የማበረታቻ ሽልማቶችን በማበርከት፣ በማነቃቃት ላይ ይገኛሉ፡፡

በወረዳው የትምህርት ቤቶች ደረጃ በማሻሻል ረገድ በተለይም በሸብራበር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እገዜ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ጋዝአንቸ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና በጎ አድራጎት ድርጅታቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

የቀጠለው የትምህርት ድጋፋቸውም በገጠር አካባቢ ለሚኖሩ ተማሪዎች የሶላር ድጋፍ በማድረግ ትልቅ ተስፋ ሰጥቷል፡፡ ክቡርአምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቁ፣ ዕውቀት ያላቸውና ተወዳዳሪ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያደርጉት ይህ ድጋፍ የአንድ ትውልድ ሳይሆን የትውልድ ተሻጋሪ ኢንቨስትመንት ነው፡፡

ከትምህርት ልማት ባሻገርም አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የማኅበረሰቡን የዘመናት የንጹህ መጠጥ ውሃ ጥያቄ ለመመለስ እያደረጉ ያሉት ጥረት ሌላው የልማት አርበኝነታቸው መገለጫ ነው።

በመንግሥት አቅም ብቻ ለመሸፈን ያልተቻሉ የማኅበረሰቡን የውሃ ፍላጎቶች በመጋራት፣ ሕዝቡ ንጹህና አስተማማኝ ውሃ እንዲያገኝ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ። ንጹህ ውሃ ለዜጎች ህይወት /ጤና፣ ትምህርት፣ ክብርና የተሻለ ኑሮ ማለት ነው። ስለዚህ የውሃ ድጋፋቸውም ከአንድ ፕሮጀክት በላይ የሆነ የሰው ልጅ ኑሮን የሚቀይር በጎ ተግባር ነው።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የሚያከናውኑት ተግባር በአንድ ቃል ሲገለጽ “አርአያነት” ነው፡፡ የልማት አርበኝነት በንግግር ሳይሆን በተግባር የሚገለጽ መሆኑን በሥራቸው እያሳዩ ነው። ዛሬ የሚያበረክቱት ድጋፍ ነገ በተማረ ትውልድ፣ በተሻሻለ የኑሮ ሁኔታ እና በተሻለ ማኅበረሰብ መልከ ይመለሳል።

እኛም ይህንን መልካም ተግባራቸው በወፍ በረር በጋዓት ዓመታዊ መፅሔታችን እንዲህ ልናስቃኛችሁ ወደድን ሰላም!! የእኖር ኮሚ

ይህ ከታች የምትመለከቱት ምስል የሚያመለክተው የጉራጌ ብሄር ለረጅም ዘመናት የሚታወቅበት የመረዳዳት፣ የመተባበር፣ በጋራ እንደግ ባህሉ ማሳያ ነው። እኔ የሚገርመኝ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባልነበረ...
13/09/2026

ይህ ከታች የምትመለከቱት ምስል የሚያመለክተው የጉራጌ ብሄር ለረጅም ዘመናት የሚታወቅበት የመረዳዳት፣ የመተባበር፣ በጋራ እንደግ ባህሉ ማሳያ ነው። እኔ የሚገርመኝ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባልነበረበት መተባበር ሀይል መሆኑን ገብቶት ሲተባበር የኖረ ህዝብ ነው። ስለዚህ ይህን ድንቅ እሴት ተንከባክቦ በማቆየት ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል።

13/09/2026

🌼 መልካም እሁድ! 🌼
☀️ ፈጣሪ ለሰው ልጅ የሰጠው እጅግ ውድ ስጦታ ሕይወት ነው፤ ይህ እሁድም በእግዚአብሔር ጸጋና በረከት የተሞላ፣ የሰላምና የደስታ ቀን ይሁንልን።
🙏 እግዚአብሔር በሕይወታችን ይሁን፤ የሰጠንን ውድ የሕይወት ስጦታ በጥበብ እንድንጠቀምበት ይርዳን፣ በጸጋው ያጽናናን፣ በፍቅሩ ይምራን፣ በምሕረቱም ይጠብቀን።
✨ በቤታችን ሰላም፣ በልባችን እምነት፣ በሥራችንም በረከት ይብዛ፤ የእግዚአብሔር ጸጋ ከእኛ ጋር ሁልጊዜ ይኑር።
“ይህች እለት እግዚአብሔር ያደረጋት ናት፤ ሐሴት እናድርግባትም፣ ደስም ይበለን።”
📖 መዝሙረ ዳዊት 117፥24
🌺 እግዚአብሔር በጸጋው ይጠብቀን፣ በበረከቱ ይምራን፣ በፍቅሩም ይባርከን።
አሜን! 🙏

ምርጥ የእናት ምግብ ሳይበሉት ያጠግባል
12/09/2026

ምርጥ የእናት ምግብ ሳይበሉት ያጠግባል

11/09/2026

የክትፎ አምሮትዎ ለመወጣት

Address

Addis Ababa
1212

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amard Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category