Fune Media

Fune Media Ethiopia

19/04/2026

Big message for you 👂👂

የት ነው ? 🤔
19/04/2026

የት ነው ? 🤔

ሰርከስ ከምባታ ማዕከላዊ ኢትዮጵያን ወክሎ በሀገር አቀፍ ውድድር እንዲሳተፍ ተመረጠ።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ የሚገኘው "ሰርከስ ከምባታ" በክልሉ ካሉ የሰርከስ ...
19/04/2026

ሰርከስ ከምባታ ማዕከላዊ ኢትዮጵያን ወክሎ በሀገር አቀፍ ውድድር እንዲሳተፍ ተመረጠ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ የሚገኘው "ሰርከስ ከምባታ" በክልሉ ካሉ የሰርከስ ቡድኖች የተሻለ ሆኖ መመረጡን የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታውቋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የሰርከስ ቡድኖችን ብቃት ለመለየት በተደረገ ግምገማ “ሰርከስ ከምባታ” በላቀ ውጤት የተመረጠ ሲሆን ቡድኑም ክልሉን በመወከል በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ውድድር ላይ ብቁ ሆኖ ለመቅረብ የሚያስችሉትን የተለያዩ ዝግጅቶች ለባለሙያዎቹ አቅርቧል።

የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ምህረት ኩራቱ ከሁሉ በማስቀደም ለዚህ አስደሳች ስኬት ፈጣሪን በማመስገን ለአጠቃላይ የዞኑ ማህበረሰብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያሰማራቸው ባለሙያዎች በቡድኖቹ አሁናዊ ቁመና ፣ በኪነ-ጥበባዊ ፈጠራ እና በማህበራዊ ተደራሽነት ዙሪያ ባደረጉት ጥብቅ ግምገማ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው ሰርከስ ከምባታም ካቀረበው ድንቅ ትርኢትና ካለው የካበተ ልምድ በመነሳት ክልሉን ወክሎ በሀገር አቀፍ መድረክ እንዲቀርብ በብቃት ተለይቷል ብለዋል።

ባለፉት 20 ዓመታት በዘርፉ በስፋት ሲንቀሳቀስ የቆየው ይህ የጥበብ ስብስብ የአካባቢውን ባህልና ትውፊት ከጅምናስቲክ ስራዎች ጋር በማቀናጀት ረገድ ውጤታማ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ምህረት ቡድኑ ለሀገር አቀፍ ውድድሩ የሚያስችለውን ዝግጅት እያጠናቀቀ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ኃላፊዋ አክለውም ለዚህ ስኬት መመዝገብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በተለይም ​የዞን የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ፣ የከተማ አስተዳደሩን አመራሮች ፣ ​ለቡድኑ አባላትና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ​ጥበብ አፍቃሪ የሆነው የሺንሽቾ ከተማ ነዋሪዎች ላደረጉት ያልተቆጠበ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ወ/ሮ ምህረት አክለውም ይህ ስኬት ቡድኑ ለጥበብ እድገት የከፈለውን መስዋዕትነት የሚያሳይና ለከተማዋም ትልቅ ኩራት መሆኑን ገልጸው ሰርከስ ከምባታ በሀገር አቀፍ መድረክ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲቀርብም የከተማው ነዋሪና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

17/04/2026
ከከምባታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የተሰጠ የሀዘን መግለጫየከምባታ ዞን ፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ኮማንደር አልማዝ ዮሀንስ ሰብሮ በሀገር ደረጃ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮምሽን ለስት...
14/04/2026

ከከምባታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

የከምባታ ዞን ፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ኮማንደር አልማዝ ዮሀንስ ሰብሮ በሀገር ደረጃ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮምሽን ለስትራቴጂክ አመራር ስልጠና በወጣው መስፈርት መሰረት ተወዳድረው በማሸነፍ በኢትዮጽያ ሀገር መከላከያ ዮንቨርሲቲ ዋር ኮሌጅ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙና ለትንሳዔ በዓል ወደ ቤተሰባቸው ደርሰው ወደ ትምህርት ገበታቸው አዲስ አበባ ሲመለሱ በቀን 05/08/2018 ዓ/ም 11:35 ደቂቃ በሚሆንበት ጊዜ በታጠቁ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ህይወታቸው አልፏል ።

ኮማንደር አልማዝ ዮሀንስ በከምባታ ዞን ፖሊስ መምሪያ በተለያዩ ኃላፈነት ደረጃ ከ21 ዓመት በላይ ህብረተሰቡንና የዞኑን ማህበረሰብ አንዲሁም የፖሊስ መምሪያው የማኔጅመንት አባል በመሆን መንግስትን በታማኝነትና በቁርጠኝነት ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ አገልግለዋል ።

የፖሊስ ከፍተኛ አመራሯ በአመራር ዘመኗ ጥሩ ስነ_ምግባር ያላቸውና በዞኑ ለሚገኙ የፖሊስ አመራርና አባላት አርዓያ የሆኑና ብዙ የፖሊስ አባላትን ያፈሩ ጠንካራ የፖሊስ ከፍተኛ አመራርና መኮንን ነበሩ።

ኮማንደር አልማዝ ዮሀንስ ከፖሊስ ሙያ ውጪ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከፊት በመሆንና በመምራት ለተለያዩ ለተቸገሩ ወገኖቻችን ህብረተሰቡን በማስተባበር እስከሞታቸው ጊዜ ድረስ እየረዱ ቆይተዋል።

ኮማንደር አልማዝ ዮሀንስ ባለትዳርና የሁለት ሴትና የአንድ ወንድ ልጅ እናት ነበሩ።

በኮማንደር አልማዝ ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለመላው ቤተሰብ፣ለዞን ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለዘመድ አዝማዶቿ መፅናናትን እንመኛለን ።

የከምባታ ዞን ፖሊስ መምሪያ
ዱራሜ
06/8/2018 ዓ/ም

አስደሳች ዜና ✍️🙏 ከ3 ቀን በፊት አፋልጉኝ ማስታወቂያ ስለ መምህር ኤርጃቦ ጎበና ፖስተን ነበርን አሁን ግን ደስ የሚል ዜና ተሰምቷል !!መምህር ኤርጃቦ ጎበና ምናቸውም ሳይጎደ በህይወት አ...
13/04/2026

አስደሳች ዜና ✍️🙏

ከ3 ቀን በፊት አፋልጉኝ ማስታወቂያ ስለ መምህር ኤርጃቦ ጎበና ፖስተን ነበርን አሁን ግን ደስ የሚል ዜና ተሰምቷል !!

መምህር ኤርጃቦ ጎበና ምናቸውም ሳይጎደ በህይወት አግኝተናቸዋል ብሏል ቤተሰበቸው ።

ሼር በማድረግ የተባበረችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። ✍️🙏

Fune Media

Luke 24 አማ - ሉቃስ1: ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ።2: ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት...
12/04/2026

Luke 24 አማ - ሉቃስ
1: ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ።
2: ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥
3: ገብተውም የጌታን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።
4: እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤
5: ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ “ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።

Inbox 👇ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ፣ በበቅሎ ሰኞ ደብረ መድኃኒት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ደጋግ ኢትዮጵያውያን በእግዚአብሔር እርዳታና ...
12/04/2026

Inbox 👇

ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ፣ በበቅሎ ሰኞ ደብረ መድኃኒት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ደጋግ ኢትዮጵያውያን በእግዚአብሔር እርዳታና በእናንተ ትብብር ለነዳያን የትንሳኤ በዓል መዋያ እንዲሆን ከገዙት በሬ ሆድ ውስጥ፣ ከዚህ በታች በምስሉ የምትመለከቱት በጣም ትልቅ ወርቅ ተገኝቷል።

Via Elias Anjamo ከስፍራው

እንኳን ለጌታችን ለመደንታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን በዓሉ የሰላም የፍቅር የጤና  ይሁንላችሁ ❤️
12/04/2026

እንኳን ለጌታችን ለመደንታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን በዓሉ የሰላም የፍቅር የጤና ይሁንላችሁ ❤️

የአፋልጉኝ ማስታወቂያ በጡረታ የተገለሉ መምህር ኤርጃቦ ጎበና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ዶዮገና ገበያ በወጡበት ከእኛ ተለይተው ስለጠፉብን እየተፈለጉ ይገኛሉ።የሚፈለጉት ግለሰብ መግለጫስም: መም...
11/04/2026

የአፋልጉኝ ማስታወቂያ
በጡረታ የተገለሉ መምህር ኤርጃቦ ጎበና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ዶዮገና ገበያ በወጡበት ከእኛ ተለይተው ስለጠፉብን እየተፈለጉ ይገኛሉ።
የሚፈለጉት ግለሰብ መግለጫ
ስም: መምህር ኤርጃቦ ጎበና
የቆዳ ቀለም: ቀይ
ቁመት: ረዥም
መኖሪያ አድራሻ: በካፋ ቀበሌ
ልዩ ስም: ጥንጥቾ
የጠፉበት ቦታ: ዶዮገና ገበያ
የጠፉበት ቀን: 2/08/2018
የለበሱት ልብስ: ቡላ ሙሉ ሱፍ
ዘመድ አዝማድ፣ ወዳጅ ጎደኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በአፋለጋ ላይ እንገኛለን።
መምህር ኤርጃቦ ጎበናን ያየ ወይም ስለ እርሳቸው መረጃ ያለው ማንኛውም ሰው እባክዎ በሚከተለው አድራሻ ይጠቁሙን።
የጥቆማ አድራሻ
መምህር ደስታ ገብረና — 0912041442
መምህር አስራት ለማ — 0912392518
“እባክዎትን ይህን ማስታወቂያ በሰፊው ያሰራጩ፤ የእርስዎ መረጃ አንድን ቤተሰብ ከጭንቀት ሊያወጣ ይችላል።”

የመ/ር ኤርጃቦ ጎበና ፎቶግራፍ

🇪🇹 የጨዋታ ቀን ! ⚽️በቱርኪዬ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ዩኤፋ ፍሬንድሺፕ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ኢትዮጵያ በሁለተኛ የምድብ ጨዋታዋ ኮስታ ሪካን ከቀኑ 10፡30 ላይ ትገጥ...
11/04/2026

🇪🇹 የጨዋታ ቀን ! ⚽️

በቱርኪዬ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ዩኤፋ ፍሬንድሺፕ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ኢትዮጵያ በሁለተኛ የምድብ ጨዋታዋ ኮስታ ሪካን ከቀኑ 10፡30 ላይ ትገጥማለች።

በጨዋታው የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ፣ ቀይ ካሶተኒ ለብሰው ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fune Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category