Gughe By Camera Eye

Wegbeschreibung Website

Gughe By Camera Eye promotion of naturally gifted the gughe geographical landscape.

02/10/2026

የሀገር ጋሻ፣መከታ
መከላኪያ ስራዊት!
🇪🇹✌🇪🇹 አጨብጭብ 👏👏👏!

24/09/2026
24/09/2026

ዜና ሹመት !!
‎ 👇
‎1ኛ #አዕምሮ ➡️ የት/ት ሚንስቴር
‎2ኛ #ጆሮ ➡️ ቴሌ ኮምዩንኬሽን ዋና ኃላፊ
‎3ኛ #አይን ➡️ _የመብራት ኃይል ብሮ ዋና ኃላፊ
‎4ኛ #አፍንጫ ➡️ _የጤና ጥበቃ ሚንስቴር
‎5ኛ #ምላስ ➡️ _የውጭ ጉዳይ ኮምሽን ኮምሽነር ኃላፊ
‎6ኛ #አንገት ➡️ _ከተማና ልማት ምንድስና ኃላፊ
‎7ኛ #እጅ ➡️ _መከላከያ ሚንስቴር
‎8ኛ #ደረት ➡️ ህፃናት ክትትል ስፖርት ሜዳ ዋና ኃላፊ
‎9ኛ #ሆድ ➡️ ማዘጋጃ ቤታዊ አግልግሎት ጽ/ቤት ዋና ስራአስኪያጅ፣
‎10ኛ #እግር ➡️ መንገድ ትራንስፖርት ዋና ኃላፊ
‎11ኛ #ጥርስ ➡️ የፋይናንስ ዋና ኃላፊ።
‎12ኛ #ከንፈር ➡️ የመንግስት ዋና ተጠሪ
‎13ኛ #ፀጉር ➡️ የተፈጥሮ ደን አከባቢ ከፍተኛ ቢሮ ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል ።
‎
‎ክብራትና ክብራን እነዚህ ከፍተኛ አመራሮች ሌሎች ደግሞ የሰውነት ክፊሎች በምክትል ማዕረግና በዳይሬክተርነት ተሹመዋል፡፡
‎
‎ እጅ 🖐️፦ _የስውንና የመንግስትን ንብረት አትንካ
‎አይን 👁️፦_ ወደ ክፋት መንገድ አትይ
‎ምላስ 😛፦ _እባክህን ሰውን አትጉዳ
‎ጆሮ 👂፦:-ሀሜትና ወሬ አትስም
‎ እግር 🦶፦-መጠጥ ቤት አትሂጅ
‎ሆድ ፦-ከስርቆት ምግብ አትስማማ
‎
‎ ማሳሰቢያና አደራ ❤✌️
‎እናንተ ከፍተኛ አመራሮች ሆይ ተናባቹሁ ካልስራችሁ ሀገር ይፈረስልና ተናባቹ ስሩ አትበላሉ ፣አትገፋፉ በአንድነት መንፈስ በወንድማማችነት ህብረት ጠንክራቹ ስሩ፡፡
‎
‎መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ !!

19/09/2026

|| ትዝታ ግምት ና እውነት !!

የዛሬ ሃያ ዓመት ገደማ ከዩኒቨርስቲ መልስ ወደ በተሰብ ስንመለስ ከአርባምንጭ በገንታ_ ጋፀ - ላካ -ቦንኬ -ጉጌ የሚንጋፈጠው የእግር ጉዞ መቼም አይረሳም ። ከሴቻ ጧት በግምት 12:00 ሰዓት ተነሥቴን ጉጌ ቤት የሚንደርሰው ምሽት 12:00 ፀሐይ ስትጠልቅ ነበር ። የርቀቱ ግምት ግን ወደ 90 ወይም 100 ኪሎ ሜትር ይለመስለኝ ነበር ። ምክንያቱም 12:00 ነው የሚፈጀው ። በርግጥ ይኸ ሁሉ ግምት ነው ማረጋገጫ የለውም ።

ዛሬ ግን የቴክኖሎጂ ዘመን ሆኖ ርቀቱንም ሆነ ሰዓቱን ማወቅ እጅግ በጣም ቀላል ሆነ ። ዛሬ በመኪና ከአርባምንጭ በተመሳሳይ መንገድ ቦንኬ ጋዜሶ ገበያ ድረስ 41.01 ኪሎሜትር በመኪና የወሰደብን ሰዓት 2:59:36 ነው ። ለውጥማ አለ። ነገር ግን 41.01 ኪሎሜትር መንገድ 3:00 ሰዓት መንዳት ጥሩ ጉዞ አይደለም ። የዚህ መንገድ ችግር የጋሞ ዞን አስተዳደር ና የቦንኬ ወረዳ አስተዳዳሪ እንደምፈቱ ተስፋ አለኝ።

ከዛም በሃላ ምግብ ገዜሶ በልቴን ከወንድሜ ጋር ወደ ጉጌ ጉዞ ጀመርን። ከቦንኬ ጉጌ ያለውን ርቀት ና የሚወስድብኝን ሰዓት ለማወቅ ጓግቻለሁ። በጣም የሚገርመው ከአርባምንጭ እስከ ጉጌ ድረስ ርቀቱ 46.29,ኪሎሜትር የወሰደብን ጊዜ ደግሞ 05:59:50 ነው ("ማስረጃ ተያይዟል).

እንግዲህ 46.29 ኪሎሜትር ነበር 12:00 ሲጓዝበት የነበረው ማለት ነው ።ዛሬ ከሃያ ዓመት በሃላ 05:59:50 ላይ ቤት ደረስኩ ። መሻሻልማ አለ። ከቦንኬ እስከ ጉጌ ያለው ርቀት ራሱ እጅግ ገርሞኛል ። ከግምቴ እጅግ በጣም የራቀ ሆነ። ትዝታ ግምት ና እውነት ። እውነትን ማወቅ እንደት ደስ ይላል ። እጅግ በጣም የገረመኝ በጉጌ ና የቦንኬ ወረዳ ድንበር ኩታ ቀበሌ መብራት አለ። ተሌቪዥን ና ሬድዮ ተከፍቶ የመንፈሳዊ መዝሙር ይደመጣል ። የቦንኬ ወረዳን አለማድነቅ አይቻልም። ቦንኬ በርቱ ስሩ ህዝባቹሁን አገልግሉ።
በነገራችን ላይ ከገዜሶ ጉጌ ያለውን ርቀት ቀናንሳቹ ድረሱበት። ትገረማላችሁ።

መስከረም 08 2019,ዓ/ም
ጉጌ ሀርንጋሶ ❤!!

ዶክተር ትዝታውን ስለጫዎቱን ከልብ እናመሰግናለን !!

17/09/2026

የጉጌ መንፈስን የሚወክል ቤተሰብ ❤️⛰️
አንዳንድ ታሪኮች በመጽሐፍ አይጻፉም፤ በቤተሰብ፣ በትምህርት፣ በመስዋዕትነት እና በትውልድ ግንባታ ይጻፋሉ!!

ይህ የሚያምር የካፊቴ ቤተሰብ ለበርካታ ዓመታት በጉጌ ቦይሬ ኖረው፣ የማህበረሰቡ አካል በመሆን በማህበራዊ ሕይወቱም አስተዋፅኦ አድርገዋል።

በተለይም ልጆቻቸውን ለማስተማር ያሳዩት ቁርጠኝነት በአካባቢው ላለው ማህበረሰብ የሚያነሳሳ ምሳሌ ነው።
ትምህርት ትምህርት ቤት መሄድ ብቻ አይደለም፤ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብ እና በመጪው ትውልድ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው። ወላጆች ለትምህርት ትልቅ ዋጋ ሲሰጡ፣ ለልጆቻቸው የተሻለ የወደፊት በር ይከፍታሉ፤ ሌሎችንም እንዲከተሉ ያነሳሳሉ።

ዛሬም ይህ ቤተሰብ የቤተሰብ አንድነት፣ የቁርጠኝነት እና የትምህርት ኃይል ምሳሌ ሆኖ ይታያል።
መጪውን ትውልድ ማስተማር የተሻለ ማህበረሰብ ለመገንባት ከሚደረጉ ታላላቅ ተግባራት አንዱ ነው።

📍 ጉጌ ቦይሬ፣ ጉጌ
❤️ ቤተሰብ • ትምህርት • ማህበረሰብ • ቅርስ

⛰️🌿

🙏🙏
08/09/2026

🙏🙏

🇪🇹 ከጉጌ ቦይሬ እስከ ኢትዮጵያን ወደ ማገልገል — ሻምበል ዮሐንስ በለጠ

ሻምበል ዮሐንስ በለጠ የጉጌ ቦይሬ መንደር ልጅ ነው። ጉጌ ቦይሬ ትንሽ መንደር ብትሆንም፣ ትጋት፣ ትሕትና፣ ጠንካራ ሥራ እና ቆራጥነት የሚሰማቸው ማህበረሰብ ናት።

በዚህ ትሑት ማህበረሰብ ተወልዶ ያደገው ዮሐንስ፣ ሕይወቱን ለሥነ-ሥርዓት፣ ለኃላፊነት እና ለአገልግሎት መስጠትን መርጧል። ዛሬም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) አባል በመሆን ከ18 ዓመታት በላይ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ አገልግሎት ሰጥቷል። 🇪🇹

🎖️ 18+ ዓመታት የአገልግሎት ጉዞ(ለእናት ሀገሩ 🇪🇹❤🙏)

ዩኒፎርምን መልበስ ብቻ ሳይሆን፣ ከዚያ ጋር የሚመጡትን ኃላፊነት፣ ትዕግሥት፣ ዲሲፕሊን፣ ድፍረት እና መስዋዕትነት በተግባር መሸከም ነው። የሻምበል ዮሐንስ በለጠ ጉዞም ይህንን ትርጉም የሚያሳይ የትጋት ታሪክ ነው።

🏡 ከትንሿ የጉጌ ቦይሬ መንደር የተነሳ ሰው እስከ አገር አገልጋይ መሆን!

የትውልድ ቦታ የአንድን ሰው የወደፊት ዕጣ አይወስንም። በትጋት፣ በትምህርት፣ በሥነ-ሥርዓት እና በጽናት ከሩቅ መንደር የተነሳ ሰው ለአገሩ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረግ ይችላል።

ሻምበል ዮሐንስ በለጠ የጉጌ ቦይሬ ልጅ ብቻ አይደለም፤ ለወጣቱ ትውልድ በአገልግሎት፣ በታማኝነት፣ በትጋት እና በጽናት የተሻለ የወደፊት ሕይወት መገንባት እንደሚቻል ምሳሌ የሚሆን ሰው ነው።

🇪🇹 18+ ዓመታት አገልግሎት
🏡 የጉጌ ቦይሬ ተወላጅ
🎖️ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል
❤️ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ አገልጋይ

የጉጌ ልጆች በተለያዩ የሥራ መስኮች ለማህበረሰባቸውና ለኢትዮጵያ እያበረከቱ ያሉትን አስተዋፅኦ እናውቅ፣ እናክብር እና ለቀጣዩ ትውልድ እንካፈል።

ከጉጌ ቦይሬ ተራሮች እስከ ኢትዮጵያ አገልግሎት — የሻምበል ዮሐንስ በለጠ ጉዞ የትጋት፣ የጽናት እና የኩራት ታሪክ ነው። 🇪🇹

📸 Promote Guge

ሕዝባችንን እናስተዋውቃለን • ጉዟቸውን እናከብራለን • ቀጣዩን ትውልድ እናበረታታለን

🇪🇹

Adresse

Berlin

Benachrichtigungen

Erfahren Sie als Erste/r von Neuigkeiten und Aktionen: Wir schicken Ihnen eine E-Mail, wenn Gughe By Camera Eye etwas veröffentlicht. Ihre E-Mail-Adresse wird für keinen anderen Zweck verwendet, und Sie können sich jederzeit abmelden.

Verknüpfungen

Teilen

Kategorie