Ders shambel

Ders shambel Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ders shambel, Camera/Photo, Holland Landing, ON.

03/23/2022

አንተ ሰው ሁን ብቻ ሌሎች ከአንተ
ይማራሉ !!

03/02/2022

መልካሙን ዘመን ያምጣልን አሜን

በፊት ነበር አስቀድሞ መደቆስ አሁን ምን ያረጋል ደሰት ጥዶ ማልቀስአሉ አማቴ🤔
02/25/2022

በፊት ነበር አስቀድሞ መደቆስ አሁን ምን ያረጋል ደሰት ጥዶ ማልቀስ
አሉ አማቴ🤔

02/25/2022
02/23/2022

አገር የፖለቲካ ፍልስፍና ስሪት ናት
አገሪቱ ከ22 አመት በፊት ነዳጅ ስታገኝ ሁሉም የኤምሬትስ ጎሳዎች ጥል ውስጥ ገቡ። ሁላቸውም ጎሳቸውን እየሰበሰቡ እከሌ የሚባለውን ጎሳ አሸንፈን ስልጣን መያዝ አለብን እያሉ ወታደር ማስልጠን ጀመሩ። ያነየ ለሁላቸውም መሳሪያ አቅራቢዋ እንግሊዝ ነበረች።

አሁን አገሪቱን የሚመሩት የነ መሀመድ ቢን ዛይድ አያት ሁሉንም ጎሳዎች ሰበሰባቸው።

ስብሰባ ጀመረ። ወገኖቼ ሁላችንም አረብ ነን። ሁላችንም ሙስሊሞች ነን። ሁላችንም አንድ አገር ነው ያለን። ሁላችንም ድሀ የደህ ልጆች ነን። ሁላችንንም የፈጠረን አንድ ፈጣሪ ነው። ሁላችንም ሰው ነን። ሁላችንም ጎሳ አለን። ሁላችንንም ጎሳችንን እንወድዋለን። ሁላችንም ተጣልን ጥላቶቻችን ለሁላችንም መሳሪያ አቅርበው ተጋደሉ ሲሉን ተገዳድለን መጨረሻ ላይ የምናገኘው ትርፍ ምንድነው .? ሲል ጠየቃቸው። ሁሉም የጎሳው መሪዎች ለጥያቄው መልስ አተው ዝም አሉ። መልሱልኝ እንጅ ሲል ጠየቃቸው። አሁንም ዝም አሉ። እሽ ምን እንሁን አላቸው። ዝም አሉ። እናተ ዝም ካላችሁ እኔ ልናገር አላቸው እነሱም እሽ ተናገር አሉት።

ይች አገር የሁላችንንም ናት። አንዱ በልቶ አንዱ ተርቦ የሚኖርባት አገር አይደለችም። ሁላችንም የአገሪቱ ባለቤት ነን። ስለዚህ አንድ አስማምቶ የሚመራን ሰው እንምረጥ አላቸው። እዚህ የተሰበሰበው ጎሳ አንድ አ መንግስት መመስረ አለበት አላቸው። እነሱም እሽ አሉት። አንድ መንግስት መሰረቱ። የመንግስት ካቢኔም ከየጎሳው ተመረጡ። የዛኑ ቀን በእምነታቸው ቃለ መሀላ ፈፀሙ።

ሸህ ዛይድም የመጀመሪያ የኤምሬትስ ፕሬዚዳንት ተደርጎ ተሾመ። ያሁሉ የጎሳ መሪ ወደቤቱ ሊሄድ ሲል ሸህ ዛይድ (ፕሬዝዳንቱ ) አንድ ንግግር ተናገሩ። ለጦር ያዘጋጃችሁትን ጎሳችሁን ለልማት እንዲዘጋጅ ንገሩት አላቸው። ጉባዔው እንዴት ተጠናቀቀ ጦርነት አለ ቀረ እያለ በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው ወታደር ሁሉ
መንግስት መስረትናል፣ ጦርነት የለም። ለልማት ተዘጋጅ ተብለናል አሏቸው።

ወዲያው ልማት ጀመሩ። ይሄው አሁን አረብ ኤምሬትስ የመካከለኛው ምስራቅ የንግድ እና የኢንቨስትመንት፣ የቱሪስት ዋና ከተማ ሆና ዜጎቿን አንደላቃ እያኖረች ነው።
ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን የቤት ሰራተኛ ቀጥራ እያሰራች ነው። የዜጎቿ የወር ወጭ የኢትዮጵያ የአንድ አመት በጀት ነው። አገሪቱ በ2 ወር ውስጥ የምታስገባው ገቢ የኢትዮጵያ የአመት ከ3 ወር በጀት ነው።

ከሷ በፊት ስንት መንግስት ያላት ኢትዮጵያ ግን ዛሬ አንዱ አንዱን ለመብላት ሲፈላለግ ዜጎቹን እንዲህ በረሀብ አዋርዶ እያኖረ፣ ዛሬም ከችጋር በማያወጣ ብሔርተኝነት ይባላል። አገር የፖለቲካ ፍልስፍና ስሪት ናት። ቅን የፖለቲካ ፍልስፍና አገርን እንዲህ ያገናል። በተንኮል የታከነ ፍልስፍና ግን አገርን አድቆ ዜጋውን በችጋር እያሰቃየ ዛሬም ስለ ጦርነት ይሰብካል።

ሱሌማን አብደላ

ምስሎቹ ትግራይ ክልል የምትማር አንዲት ህፃን ልጅ እና የኤምሬትስ ዋና ከተማ ናቸው።

Address

Holland Landing, ON

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ders shambel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category