ራስ ደጀን ዲጅታል ፎቶግራፊ - Ras Dejen Digital Photography

ራስ ደጀን ዲጅታል ፎቶግራፊ - Ras Dejen Digital Photography Ras Dejen photograph

Congregationsየአቶ ሰሎሞን ተ/ብርሃንና የወ/ሪት አቢጊያ ገዛኸኝ ስርዓተ ቁርባን የጋብቻ ሥነ ስርዓትነሐሴ 24/2018 ዕ/ምUAE AbuDabi
03/09/2026

Congregations
የአቶ ሰሎሞን ተ/ብርሃንና የወ/ሪት አቢጊያ ገዛኸኝ ስርዓተ ቁርባን የጋብቻ ሥነ ስርዓት
ነሐሴ 24/2018 ዕ/ም
UAE AbuDabi

01/09/2026
23/08/2026
በዓለ ደብረ ታቦር በአቡዳቢ ምስካየ ህዙናን መድኃኒዓለም ወአቡነ ተክለኃይማኖት ገዳምነሐሴ 14/2018 ዓ/ምUAE Abudabi
20/08/2026

በዓለ ደብረ ታቦር በአቡዳቢ ምስካየ ህዙናን መድኃኒዓለም ወአቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም
ነሐሴ 14/2018 ዓ/ም
UAE Abudabi

ደባርቅ የቱሪዝምና የልማት አቅሟን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር አዲስ የልማት ጉዞ ጀመረች‼️የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መዳረሻ የሆነችው ደባርቅ ከተማ፣ ያላትን የተፈጥሮ፣ የታሪክና የቱሪዝ...
12/08/2026

ደባርቅ የቱሪዝምና የልማት አቅሟን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር አዲስ የልማት ጉዞ ጀመረች‼️

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መዳረሻ የሆነችው ደባርቅ ከተማ፣ ያላትን የተፈጥሮ፣ የታሪክና የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ከተማዋን የተሻለ የቱሪዝምና የልማት ማዕከል ለማድረግ እና የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት አዲስ የልማት እንቅስቃሴ ጀምራለች።

ደባርቅ በተፈጥሮ የታደለች ከተማ ከመሆኗ ባሻገር፣ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ብርቅዬው ዋልያ፣ የተለያዩ የዱር እንስሳትና አእዋፋት እንዲሁም ሀገር በቀል እጽዋት የሚገኙበት የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መግቢያ በመሆኗ ከፍተኛ የቱሪዝም አቅም አላት።

የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ደባርቅ፣ በራስ ደጀን ተራራና በሊማሊሞ ጠመዝማዛ መንገድ የተከበበች ሲሆን፣ በአካባቢዋ የሚገኙ የተፈጥሮና የቱሪዝም ሀብቶች ከከተማዋ አቅም ጋር ተጣጥመው እንዲለሙ የልማት ሥራዎች መጀመራቸው ተገልጿል።

በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማትም ለደባርቅ ያላትን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ የልማት ውጤት ለመቀየር ትልቅ ዕድል እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህንን የልማት ጉዞ ለማጠናከር የከተማዋ ነዋሪዎችም በሰላም ማስጠበቅ ላይ ያሳዩትን ተሳትፎ ወደ ልማት በማሸጋገር ንቁ ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

የደባርቅን የቱሪዝም አቅም፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክንና በአካባቢው የሚገኙ ቅርሶችን ለመጠበቅና ለማልማት የሚያግዝ የምክክር መድረክም ተዘጋጅቷል።

“ቅርሶቻችንን እንንከባከብ፤ የወደፊታችንን እንገንባ!” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው ይህ መድረክ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ከ12፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 2፡00 ሰዓት በታላቅ ድምቀት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ክቡር ታዬ አጽቀሥላሴ የክብር እንግዳ ሆነው እንደሚገኙ መረጃው ያመለክታል።

መድረኩ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክንና ደባርቅን በማልማት፣ ቅርሶችን በመጠበቅና የአካባቢውን የቱሪዝም አቅም በማሳደግ ረገድ የሕዝብ፣ የተቋማትና የባለድርሻ አካላትን ትብብር ለማጠናከር የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

ደባርቅ ያላትን የተፈጥሮ፣ የታሪክና የቱሪዝም ፀጋ ከተገቢው ጥበቃና ልማት ጋር በማጣመር ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚና የከተማ ልማት ለመቀየር የጀመረችው ጉዞ የከተማዋን ነገ የበለጠ ተስፋ ሰጪ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል።

በዚህ ጥረት የደባርቅ ተወላጆች፣ ነዋሪዎችና ደጋፊዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑም ተጠቁሟል።

«ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ፤ አንተ ወታቦተ መቅደስከ» (መዝሙር 132:8)(«አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት»)ይህ የነቢዩ ዳዊት ትንቢታዊ ቃል ስለድንግል ማርያም ...
06/08/2026

«ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ፤ አንተ ወታቦተ መቅደስከ» (መዝሙር 132:8)
(«አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት»)
ይህ የነቢዩ ዳዊት ትንቢታዊ ቃል ስለድንግል ማርያም ፍልሰትና ዘለዓለማዊ ክብር የሚናገር ነው።
«የመቅደስህ ታቦት» ተብላ የተገለጠችው ድንግል ማርያም ናት። መለኮታዊ ክብር ያደረባት፣ መናና የሕጉ ጽላት የተቀመጠባት እንደነበረች፣ እንዲሁም እውነተኛዋ ታቦት ድንግል ማርያም የሕይወት እንጀራና የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዘጠኝ ወር ከዐምስት ቀን በማሕፀኗ ተሸክማዋለች።
ስለዚህ፣አንተና የቅድስናህ ታቦት ወደ ዕረፍትህ ተነሥ» ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣና እንደ ዐረገ ሁሉ፣ «የመቅደሱ ታቦት» የተባለችውን እናቱን ድንግል ማርያምንም ከመቃብር አሥስቶ፣ ሥጋዋን ከነፍሷ ጋር በማዋሐድ ወደ ዘላለም ዕረፍቱና ክብሩ ወደ ሰማይ አሳርጓታል ማለት ነው።
ውድ ዘመዶቼ፣ በጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሥጋዊ ፍላጎታችንን ለነፍስ ፍላጎት በማስገዛት፣ ሥጋችንም በዚህ ኀላፊ ዓለም በስብሶ የማይቀርና በትንሣኤ ዘጉባኤ ከነፍሳችን ጋር ተዋሕዶ በክብር እንደሚነሣ ተስፋ ሰንቀን፣ የመንፈስ ፍሬዎችን እያፈራን እንድንኖር የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን።

🎉 Facebook recognised me as a consistent reels creator this week!
04/08/2026

🎉 Facebook recognised me as a consistent reels creator this week!

Address

Al Ain

Telephone

+971502073884

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ራስ ደጀን ዲጅታል ፎቶግራፊ - Ras Dejen Digital Photography posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share