18/12/2025
ታዋቂው ቲክቶከር ጆን ዳንኤል ከ1 ዓመት ከ4 ወራት በኋላ በይፋ ተመለሰ!
ባለፉት 16 ወራት ከማህበራዊ ሚዲያ ርቆ የቆየው ታዋቂው ቲክቶከር ጆን ዳንኤል፣ "ስለሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን" በማለት ዳግም ወደ ተከታዮቹ መመለሱን አብስሯል።
ጆን ዳንኤል ባለፈው ጊዜ ውስጥ ያጋጠመው ሁኔታ ትልቅ ትምህርት እንደሆነው ገልጾ፣ "አለማስተዋሌ ዋጋ አስከፍሎኛል፤ በዚህም በአንድ ዓመት ውስጥ ብዙ ተምሬ ወጥቻለሁ" ሲል ተናግሯል።
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ለተፈጠረው አወዛጋቢ ክስተት የኢትዮጵያ አየር መንገድን በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።
ስህተትን አምኖ ይቅርታ መጠየቅና ካለፈው መማር ለሌሎችም ትልቅ ትምህርት ነው!
ለጆን ዳንኤል መልካም ዳግም መመለስ እንመኛለን።
በል ከስህተትህ ተማር ልጄ😂