21/03/2026
ጥያቄ?
ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ከከፍተኛ እስከ እግረኛ ሰራዊቱ እና ደጋፊዎች ማህበረሰቡን ሲዘርፉ፤ሲገሉ እና ሲያፈናቅሉ የነበሩ ሽፍቶች በፋኖ ስም በእየሰፈሩ ተደራጅተው የቀደመ እኩይ ተግባራቸውን እንደቀጠሉ ናቸው።
ለምሳሌ በአምባሰል ወረዳ በ017 እና 023 ቀበሌዎች በእነ ሰለሞን አሊ እውቅና እና ፈቃድ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሽፍቶች አምባሰል 023 ቀበሌ "መንጣላ"እየተባለ በሚጠራው ቦታ ጌትነት አስረጋ ደጉ(ዳውድ)የሚባልን አርሶ አደር መግደላቸውን አንድ የአካባቢው መምህር አረጋግጧል።ሌሎችም እጅግ አስከፊ ወንጀሎች እየፈፀሙ ናቸው።
ታዳ እንዲህ አይነት ወንጀለኞች የተሰገሰጉበት ፋኖ ማንን ነው ነጻ የሚያወጣው?
ተገቢስ ነው ወይ?
አርበኛ ዘመነ ካሴ እንዳለው የአማራ ሕዝብ "ውሻዬን ሽጨ ቀበሮ ገዛሁ" አይሆንም ወይ?ጭራሽ ይባስ ብለው የሟችን ቤተሰብ ድምጽ ከሰማንባችሁ እንደግማችሗለን እስከማለት የደረሱበት ሁኔታ አለ ስለዚህ እንዲህ አይነት አምባገነኖችን የምትዳኙበት የፋኖ ሕግ እና ደንብ የለም ወይ?
ፍትህ ለጌትነት አስረጋ ደጉ/ዳውድ😭