የወልቃይት ገጽ

የወልቃይት ገጽ Iይህን ገጽ
ስለወልቃይት ጸገዴ ባህል እና ኣኗኗር የምንማማርበት የምንወያይበት እንዲሁም የወልቃይትጠገዴ ገጸመሬት በፎቶ እና ቪድዮ የምንቃኝበት ገጵ ነው፡፡
(2)

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ግን ምን እየሰራ ነው?   በ 50 ቢልዮን ብር የተገነባው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ እየበሰበሰ ፣ አየዛገ እና እየወደመ ይገኛል። እንደዚህ ስል ብዙ ሰዎች ብዙ ነ...
15/06/2025

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ግን ምን እየሰራ ነው?

በ 50 ቢልዮን ብር የተገነባው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ እየበሰበሰ ፣ አየዛገ እና እየወደመ ይገኛል። እንደዚህ ስል ብዙ ሰዎች ብዙ ነገር ሊሉ ይችላሉ። የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ የኢትዮጵያ ሀብት ነው ወይ ደግሞ በብድር የተሰራ የኢትዮጵያ ዕዳ ነው። ሰላም ሳይኖር አንተ ስለ እድገት ታወራለህ የሚል አይጠፋም ከ ከተሞች ኮሪደር ፕሮጀክት ይልቅ አንድ ግዙፍ የስኳር ፋብሪካ ለአንዲት ሀገር እጅግ ጠቃሚ ነው። ሲቀጥል ፋብሪካዎች ከሌሉ ከተሞች ምንም አይደሉም።
ንሮ እንዲከብዱ ካደረጉ ነገሮች አንዱ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ፋብሪካዎች ስራቸውን በማቆማቸው ነው።
እርግጥ ነው በዚህ አምስት ዓመት ውስጥ ብዙ ፋብሪካዎች ስራቸውን እንዳቆሙ የሚታወቅ ነው። ነገር ግን የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ከግዙፉነቱ እና ከጨረሰው በጀት አንፃር እንዲሁም ከሚሰጠው ጥቅም አንፃር ሲታይ 90 ፐርሰንት አልቆ እያለ ኮርፖሬሽኑ ስራው ከመስርሳቱ የተነሳ እየወደመ ፣ እየዛገ እና እየበሰበሰ መገኘቱ ነው። አይደለም የ አምሳ ቢልዮን ብር ወይም ተገዢ የሆንለትን የ4.5 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት ይቅርና የአምስት መቶ ሺ ፕሮጀክትም እልባት ሳይሰጠው እንዲሁ ባክኖ አይቀርም ነበር። አምሳ ቢልዮን በቆየ ዋጋ ነው በአሁኑ ቢሆን ስንት ይሆን እንደነበር መገመት አይከብድም፣ ፋብሪካው ከተጀመረ አስር ዓመት አልፎታልና።

ኢትዮጵያ በሺዎች አልያም በሚልዮኖች ኩንታል ስኳር ከ ህንድና ሌሎች አገሮች ታስገባለች ታድያ ለዚህ መፍትሔው ያለቀው ግዙፍ ፋብሪካ ስራ ማስጀመር ፣መጠበቅ እና መንከባከብ ሲገባ አላውቀውም ተብሎ አምስት ዓመት ዝም ማለት ይገባ ነበር?
ሕዝቡ የሚጠብቀው ሌላ አዲስ ፋብሪካ እንዲገነባ ነው ካልሆነ ግን የተሰራውን መጨረስ እና ማደስ ያቆመውን እንዲጀምር ግን በብዙዎች ኢትዮጵውያን የሚጠበቅ ነው።

የማያውቁ ይመስልሀል? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ልክ ነው አውቆ የተኛን መቀስቀስ ከባድ ነው! ነገር ግን እንደተባለው እንዲሁ ከሆነ በዓለሙ ሁሉ ላይ ያሉ ሀገር ወዳድ ዜጎች ይመልከቱት ነው መልሱ።

እንደኔ የተሰማችሁ ሼር አድርጉት የሚመለከተው አካል መልስ እንዲሰጠው።
Wendmsew Abrha

ወ/ት አለም አምባቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ  የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የማበረታቻ ሽልማት ለ44 ተማሪዎች እና ለ3 ወላጆች ስጦታ አበረከትች ሰኔ 06/2017ዓ/ምበአማራ ክልል በወልቃይት ጠገ...
14/06/2025

ወ/ት አለም አምባቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የማበረታቻ ሽልማት ለ44 ተማሪዎች እና ለ3 ወላጆች ስጦታ አበረከትች

ሰኔ 06/2017ዓ/ም
በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን
በቃብትያ ሁመራ ወረዳ ለከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተመሪዎች
በወ/ት አለም አምባቸው ድጋፍ ተደረገላቸው

ድጋፍ የተደረገላቸው ከ8ኛ ክፍልእስከ 12ኛ ክፍል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ የወጡ እንዲሁም በትምህርት ቤቱ በአበረጀ አሸናፊ የሆኑት እና በተመሳሳይ ደግሞ ከአንድ ቤት ሁለት ተማሪ ለሽልማት ያበቁ 3 ወላጆችም ተሸላሚ ሁነውል

ከ8ኛ-12ኛ አንደኛ ደረጃ የወጡ ለ14 ተማሪ ለአንድ ተሸላሚ 2000 ብር 14×2000=28000 ብር
ከ8ኛ-12ኛ ሁለተኛ ደረጃ ለወጡ ለአንድ ተማሪ 1500 ብር
14×1500=21000 ብር

ከ8ኛ ክፍል-12ኛ ክፍል 3ኛ ደረጃ ለወጡ 14 ተማሪ ለአንድ ተማሪ 1000ብር
14×1000=1400

ከትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ለሁለት ተማሪዎች
ለሁለቱ 10,000ብር እና ሁለት ቦርሳ የትምህርት ቤት
ለሶስት ወላጆች ሁለት ልጆቻቸው ከአንድ ቤት ተሸላሚ ላደረጉ
ለያንዳዳቸው 2500 ብር 2500×3=7500 ብር

በጠቅላላ 80500/ሰማንያሺ አምስት መቶ ብር/

በዚህ ፕሮግራም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አታላይ ታፈረ
የቃብትያ ከተማ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ደጀን ለማ
የቃብትያ ሁመራ ወረዳ የመንገድ ትራንስፖርት ሀላፊ
መ/ር ሹሙየ ታደለ
የአገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት
ለእህታችን አለም አምባቸው ደማቅ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን በትምህር ቤቱ ርእሰ መምህርት እርጎየ ለወይዘሮ አለም አምባቸው
የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተውላታል

በወረዳው አስተዳዳሪ እና በአቶ አታላይ ታፈረ 6330 ከሬ
ለትምህርት ቤት ግንባታ የሚሆን መሬት ለወ/ት አለም አምባቸው
ካርታና ፕላን አስረክበዋል
ወ/ት አለም አምባቸው የአንድነት ተምሳሌት የልማት አርበኛ የሆነች ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ብሎ ግንባሩ ለጥይት የሰጠ ጀግግናችን የባህርዳር ልጅ በስሙ ትምህርት ብከት ለመስራት ቦታዋን ተረክባለች የትምህርት ቤቱ ስም አበበ ገረመው ብላዋለች
ክብር ይስጥልን የኛ ጀግና
#ወልቃይትጠገዴአማራነው
Habtamu tadesse ሀብታሙ ታደሰ

ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫየማያባራው የአዞ እንባ ዕውነትን ጠርጎ ሊወስድ አይችልም!ከሰሞኑ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ...
12/06/2025

ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
የማያባራው የአዞ እንባ ዕውነትን ጠርጎ ሊወስድ አይችልም!
ከሰሞኑ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የወልቃይት ጠገዴና አካባቢው በተመለከተ ባወጣው ካርታ "አከራካሪ ቦታዎች (contested areas)" በሚል ስያሜ መጠቀሙን ተከትሎ ሳልሳይ ወያኔ ፓርቲና የትግራይ ዓለም አቀፍ ምሁራንና ባለሙያዎች ማኅበር ነን የሚሉ የሕወሓት ክንፎች አሳሳች መግለጫዎችን በማወጣት የአዞ እንባ ሲያነቡ ተመልክተናል።
ሕወሓትና የአስተሳሰብ ተሸካሚዎቹ ዕውነትን በመደብደብ፤ በሐሰት ትርክት አሳሳች ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሲያሳስቱ የነበረ ቢሆንም በጊዜ ሂደት በአደባባይ በመጋለጥ ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑም ለእያንዳንዱ መግለጫቸው መልስ መስጠት ባይጠበቅብንም የዘመኑ መንፈስ ድኀረ-ዕውነት (post truth) "ከሳሽ ዝም ሲል ተከሳሽ ይሆናል" ነውና ብሂሉ አስፈላጊ ነው ብለን ባመንበት ጊዜ በሚከተለው መልኩ ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫና ወቅታዊ ማብራሪያ አውጥተናል፡-
1.በመሠረቱ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ የወልቃይት ጠገዴና አካባቢው በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት ከተፈረመው የፕሪቶሪያ ስምምነት አንፃር ተነስቶ "አከራካሪ (contested areas) " ብሎ ይጥራው እንጅ የማንነት መገለጫዎች ከሆኑት ከባህል፣ ከታሪክ፣ ከቋንቋና ከሥነ ልቦና አንጻር ሲመዘንም ሆነ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 39/5 ማንነትን በተመለከተ በተቀመጠው መሠረት የጋራ ባሕልና ተመሳሳይ ልማዶቹን፣ የጋራ ሕልውናውን እና የሥነ ልቦና አንድነቱን እንዲሁም መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡን በማየት ወልቃይት ጠገዴና አካባቢው የሚያከራክር ሳይሆን የጎንደር አማራ አካል መሆኑ ፀሐይ በምስራቅ የመወጣቷን ያክል ነባራዊና የማይቀየር ዕውነታ ነው፡፡

የአማራ ታሪካዊ ርሰትት አካል የሆኑት እነ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ራያ "አከራካሪ" በሚል መገለጻቸው ይህም የ27 ዓመቱ የጭፍለቃ አገዛዝ ውርስ በመሆኑ ጉዳዩን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማስረዳት ተጨማሪ ሥራ እንደሚጠበቅ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ የወሰንና የማንነት አስመላሽ ኮማቴ ያምናል።
2. የሕወሓት አስተሳሰብ ተሸካሚ የሆኑት የድርጅቱ ክንፎች በሰጡት መግለጫ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰው ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀለ አስመስለው አሳሳች መረጃ ሲሰጡ ታይቷል።
በመሠረቱ በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት አቆጠጣር መሠረት ሕወሓት ከትግራይ አምጥቶ ያሰፈራቸውን ጨምሮ አጠቃላይ የወልቃይት ጠገዴ የሕዝብ ቁጥር እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ ከ480ሺ ያልበለጠ ነው። በተጨማሪም OCHA 17/08/2017, OCHA, accessed 03/02/2021 ዓለማቀፍ መረጃዎች ቁጥሩን ከ 467,890 እንደማያስበልጡት የመረጃ መረቦች ላይ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ዓለማቀፉ ማኀበረሰብም ይህን ዕውነታ ጠንቅቆ ይረዳል፡፡
ስለሆነም ሕወሓትና የአስተሳሰቡ ተሸካሚዎች "ተፈናቃይ" ብለው የሚጠሯቸው የምናብ እንጅ የዕውን የሚጨበጡና የሚዳሰሱ እንዳልሆኑ፣ ለቀጣይ የመገንጠል ፕሮጀከቱ ማስፈጸሚያ የፈጸመው የሐሰት ትርክት ስለመሆኑ የማንነትና የወሰን ኮሚቴው መግለጽ ይፈልጋል።
3. ሕወሓትና ክንፎቹ በተደጋጋሚ የሚያነሱት ተፈናቃይ (ሰፋሪ) መመለስን የተመለከተ ነው። በፕሪቶሪያ ስምምነት አንቀፅ 5(3) መሠረት ተፈናቃይ (ሰፋሪ) መልሶ የሚሰፍረው ‹ሁኔታው ሲፈቅድ› እንደሆነ ተመላክቷል።
በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አተያይ ሁኔታው ሲፈቅድ ማለት በወልቃይት ጠገዴ

የቃብትያ ሁመራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አታላይ ታፈረ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጠውን ክልል አቀፍ ፈተና አስጀመሩ።ሰኔ 03/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሠቲት ሁመራ ዞን ቃብ...
10/06/2025

የቃብትያ ሁመራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አታላይ ታፈረ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጠውን ክልል አቀፍ ፈተና አስጀመሩ።

ሰኔ 03/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሠቲት ሁመራ ዞን ቃብትያ ሁመራ ወረዳ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጠው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አታላይ ታፈረ በባዕከር አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት አስጀምረዋል።
የቃብቲያ ሑመራ ወረዳ የመንግስት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን

የነፃነት ሰገነት፣ የልማት ተምሳሌት! የወልቃይት ጠገዴ አማራ ትግል መንገዱ ላይ ነው፡፡ መንገዱም የእውነት፣የፍትህና የርትዕ ነው! የትግሉ መንገድ ደግሞ አርቆ የማየት፣ አልቆ የመስራት ጊዜ ...
08/06/2025

የነፃነት ሰገነት፣ የልማት ተምሳሌት!

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ትግል መንገዱ ላይ ነው፡፡ መንገዱም የእውነት፣የፍትህና የርትዕ ነው! የትግሉ መንገድ ደግሞ አርቆ የማየት፣ አልቆ የመስራት ጊዜ ላይ ነን።

በክልላችን መንግስት የሚመደብልንን ፕሮጀክትና ሃብት በውጤታማነት በመምራትና በማስተባበር አኩሪ ተግባር በመፈጸም እነሆ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በወልቃይት ወረዳ በክልላችን መንግስት በጀት የተሰራው የምድረ-ወይዘሮ የጠጠር መንገድ በጥራት በመጠናቀቅ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓልና እንኳን ደስ አላችሁ፣ ደስ አለን!! በዞናችን እየተመረቁ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት እየተደረጉ ያሉት “የነፃነት ሰገነቶቻችን፣ የልማት ተምሳሌቶቻችን፣ የአማራዊ ማንነታችን አርማ ናቸው”! በቅርብ ቀናት ደግሞ በርካታ ፕሮጀክቶች ይመረቃሉ፣ ቃልን በተግባር ይገላልጣሉ!!

“አንድ ፕሮጀክት በአንድ ወረዳ” ===================የማንጨርሰውን ፕሮጀክት አንጀምርም!! በሚለው መሪ ሀሳብ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የ...
03/06/2025

“አንድ ፕሮጀክት በአንድ ወረዳ”
===================

የማንጨርሰውን ፕሮጀክት አንጀምርም!! በሚለው መሪ ሀሳብ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የማይካድራ ከተማ አስተዳደር እና ህዝብ የሰራቸውን የመንገድ ስራ አጠናቆ እነሆ ዛሬ 26/9/2017ዓ/ም የዞናችን ከፍተኛ አመራሮችና የወረዳናከተማ አመራሮች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሁኗል። እንኳን ደስ አላችሁ፣ ደስ አለን!! ምርቃቱ ገና ተጀመረ እንጂ በሌሎች ወረዳዎችና ከተሞች ይቀጥላል።

በአብክመ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የማይ ካድራ ከተማ አስተዳደር በህዝብ ተሳትፎ የተሰሩ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ስራዎችን በዛሬ ቀን 26/09/2017 ዓ/ም ከፍተኛ የዞን እና የወ...
03/06/2025

በአብክመ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የማይ ካድራ ከተማ አስተዳደር በህዝብ ተሳትፎ የተሰሩ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ስራዎችን በዛሬ ቀን 26/09/2017 ዓ/ም ከፍተኛ የዞን እና የወረዳ እንዲሁም የከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል
@ሀረግ ሾው

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ኦረንቴሽን ለሚመለከታቸው አካላት ተሰጠ።ሁመራ: ግንቦት 25/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁ...
02/06/2025

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ኦረንቴሽን ለሚመለከታቸው አካላት ተሰጠ።

ሁመራ: ግንቦት 25/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ከትምህርትና ባለድርሻ አካላት ጋር በክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ኦረንቴሽን በሰቲት ሁመራ ከተማ ተካሂዷል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ሰላምና ጸፅታ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽቤት፣ የክልሉ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ኃላፊ እቶ አገኘሁ ካሳ ፣ክልሉ ግብርና ጥራት እና ደህንነት አማካሪ እቶ ጥላሁን አለምነህ፣ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ገ/ማርያም መንግስቴ፣ሌሎች የዞን የስራ ኃላፊዎች፣ የወረዳ አስተዳደሮችና የጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።

በዞኑ ከ6ሽህ በላይ ተማሪዎች የስድስተኛ ክፍል እንዲሁም ከ5ሽህ በላይ የስምንተኛ ክፍል ተፈታኞች በዞኑ መኖራቸውን የገለፁት የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ገ/ማርያም መንግስቴ የኦላይን ምዝገባው የኢንተርኔት ችግሮች ቢኖሩም ሁሉም መመዝገባቸውን አንስተዋል።

ካሁን በፊት የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች የተደረጉ መሆናቸውን ያነሱት ኃላፊው ስድስተኛ ክፍል ሰኔ 5-6 እና ስምንተኛ ክፍል ሰኔ 3-4 የሚወስዱ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞችም ከአሁን ጀምሮ ዝግጅት እንደሚጠይቅ ጠቁመው ተፈታኞች መሄድ ባለባቸው ጊዜ ወደመፈተኛ ቦታቸው (ዩንቨርስቲ) ያለምንም ችግር እንዲደርሱ በቅንጅት ልንስራ ይገባል ብለዋል።

ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ማህበረሰቡ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

ችግር ፈች ትውልድን ለመፍጠር የትምህርት ተቋም ላይ አበክረን መስራት አለብን ያሉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ሰላምና ጸፅታ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተማሪዎችን በፈተና ወቅት የፍርሀት ስሜት እንዳያድርባቸው በስነልቦና ማዘጋጀት አለብን ብለዋል።

ኩረጃን በማስወገድ ተማሪዎች በራሳቸው አቅም ተመዝነው የራሳቸውን የልፍት ውጤት ይዘው ወደቀጣዩ የክፍል ደረጃ ይዘው እንዲዘዋወሩ ማድረግ መቻል አለብን ሲሉ አስረድተዋል።

ጥራት ያለው መፈተኛ ክፍሎችን ማዘጋጀት ለተፈታኝ ተማሪዎች ውጤት ወሳኝነት አለው ያሉት የክልሉ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ኃላፊ እቶ አገኘሁ ካሳ ተፈታኞቸ ፈተናቸውን በሰላም ጀምረው እስኪያጠናቅቁ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የጀግናው  ታጋይ  ብርሀኑ ፈረደ አስከሬን በደንሻ ከተማ ሲደርስ የተደረገ አቀባበል ።ነፍስ ይማር 😭😭😭
31/05/2025

የጀግናው ታጋይ ብርሀኑ ፈረደ አስከሬን በደንሻ ከተማ ሲደርስ የተደረገ አቀባበል ።

ነፍስ ይማር 😭😭😭

ህዝብ  #ይመራል መንግስት ይከተላል=================ህዝብ መንግስትን ይመራል እንጅ መንግስት ህዝብን አይመራም ።የዚህ ቃል ማረጋገጫ ደግሞ  #በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወል...
30/05/2025

ህዝብ #ይመራል መንግስት ይከተላል
=================
ህዝብ መንግስትን ይመራል እንጅ መንግስት ህዝብን አይመራም ።
የዚህ ቃል ማረጋገጫ ደግሞ #በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በወልቃይት ወረዳ ጠለሎ የወልና ደብረማርያም ህዝብ ትለቅ ማሳያ ነው።ይህ ካልኩ ዘንዳ መጀመሪያ የወለል ቀበሌ ህዝብ እንግልት በቃኝ ብሎ የመንገድ ጠረጋ ስራውን ባገኘው ባህላዊ ቁሳቁስ በመጠቀም የጉልበት ስራውን ጀምሮ ጠርጎ መንግስትን መርቶ ለመንግስት አስረከበ ይህ ካደረገ በኋላስ መንግስት በህዝብ ተመርቶ ማሽኖቹን ይዞ ቦታው ላይ ከቻለ ።ከዛስ እንደገና ህዝቡ የመሪነት ሚናውን አጠናክሮ በመቀጠል ማሽኑንና ባለሞያዎቹን ካገኘንማ እኛ ደግሞ ልጆቻችንና ማህበረሰቡን አጣምረን የነዳጅ አቅርቦት በማቅረብ ቃል ሳይሆን በተግባር ነዳጁን ይዞ በመቅረብ ይኸው መንገዱ በሕዝብ መሪነት በመንግስት ተከታይነት ያለማቋረጥ መንገዱ በምታዩት መልኩ እየከነፈ ይገኛል ።መሪና ተመሪ ተመሪና መሪ ማለት እነደዚህ ነው ።
አሁንም እኛ ስራ ላይ ነን የምንለው በምክንያት ነው ።
via mamay ayana

የቃብትያ ሁመራ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች በወረዳው እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ጎበኙ።ግንቦት 22/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ቃብትያ ሁመራ ወረዳ የመንግሥት ...
30/05/2025

የቃብትያ ሁመራ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች በወረዳው እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ጎበኙ።

ግንቦት 22/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ቃብትያ ሁመራ ወረዳ የመንግሥት ሰራተኞች የቃብትያ-ዘርባቢት መንገድ ፕሮጀክት እና የቃብትያ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጎበኙ።

በወረዳው እየተሰሩ ካሉ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የቃብትያ-ዘርባቢት መንገድ ማህበረሰቡ: ዲያስፖራው:የመንግስት ሰራተኛው እና የወረዳው በጀት በመጠቀም እየተሰራ ፕሮጀክት ነው።

የመንግስት ሠራተኛው ያደረገው ድጋፍ ለታቀደለት ዓላማ እየዋለ እንደሆነ ለማየት እና እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለማየት ዓላማ ያደረገ ጉብኝት ሲሆን የመንግስት ሰራተኞቹ ባዩት ነገር በጣም ደስተኛ መሆናቸው ተናግረዋል።

በጉብኝት መርሃግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ መ/ር አዛናው ብርሃኔ አሁን በወረዳችን እየተሰሩ ያሉ ልማቶች የለውጡ ትሩፋቶች መሆናቸውን በመገንዘብ ለውጡ ያስገኘልን ነፃነት መጠበቅ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
የቃብቲያ ሑመራ ወረዳ የመንግስት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን

ሠላም ከራስ ለራስ!!በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሰቲት ሁመራ ከተማ ወጣቶች መድረክ ስለአከባቢያቸው አዎንታዊና ዘላቂ ሰላም መስፈን የበኩላቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ ተና...
28/05/2025

ሠላም ከራስ ለራስ!!
በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሰቲት ሁመራ ከተማ ወጣቶች መድረክ ስለአከባቢያቸው አዎንታዊና ዘላቂ ሰላም መስፈን የበኩላቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ ተናገሩ።
4ቱም ቀበሌዎች በፎቶ

Address

Welkayt
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወልቃይት ገጽ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የወልቃይት ገጽ:

Share