የካሜራ እይታ - camera veiw

የካሜራ እይታ - camera veiw Page �

ከ2026 ተነስቶ ወደ 2025 የተመለሰው "ተአምረኛው" አውሮፕላን! ✈️⏳ጊዜን ወደ ኋላ መመለስ የሚቻለው በፊልም ላይ ብቻ ነው ብለው ያስባሉ? ተሳስተዋል! ካቴይ ፓሲፊክ (Cathay Paci...
04/01/2026

ከ2026 ተነስቶ ወደ 2025 የተመለሰው "ተአምረኛው" አውሮፕላን! ✈️⏳

ጊዜን ወደ ኋላ መመለስ የሚቻለው በፊልም ላይ ብቻ ነው ብለው ያስባሉ? ተሳስተዋል! ካቴይ ፓሲፊክ (Cathay Pacific) የተሰኘው አውሮፕላን ይህንን የሳይንስ ልቦለድ በገሃዱ ዓለም እውን አድርጎታል።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ በረራ ቁጥር 880፣ ከሆንግ ኮንግ የተነሳው ጥር 1፣ 2026 ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነበር። የ2026ን አዲስ አመት ተቀብለው ወደ ሰማይ የወጡት መንገደኞች፣ ከ12 ሰዓታት በረራ በኋላ ሎስ አንጀለስ (LA) ሲያርፉ ግን የቀን መቁጠሪያው የሚነበበው ታህሳስ 31፣ 2025 ነበር!

ይሄ የሆሊዉድ ፊልም አይደለም፤ የአውሮፕላኑ መንገደኞች ከወደፊቱ (Future) ተነስተው ወደ ያለፈው (Past) ተመልሰዋል። ምስጢሩ ያለው አውሮፕላኑ ዓለምን በጊዜ ዞን (Time Zone) የሚያከፋፍለውን "International Date Line" አቋርጦ ስለበረረ ነው።

በዚህም ምክንያት መንገደኞቹ እድሜያቸው ላይ አንድ ቀን ሳይቀነስ፣ አዲሱን ዓመት ሁለት ጊዜ የማክበር "ታሪካዊ ዕድል" አጋጥሟቸዋል። 2026 ገብተው፣ መልሰው 2025ን የኖሩ ብቸኛ ሰዎች!

  በጠዋት መነሳትህ ለራስህ ሰፋ ያለ ጊዜ እንዲኖርህ እና ሳትቻኮል ተረጋግተህ ማድረግ ያለብህን ነገር አድርገህ ሳታረፍድ በጥሩ ስሜት ወደ ስራህ እንድትወጣ ይረዳሀል። ቀንህን የጀመርክበት ሙ...
11/11/2022




በጠዋት መነሳትህ ለራስህ ሰፋ ያለ ጊዜ እንዲኖርህ እና ሳትቻኮል ተረጋግተህ ማድረግ ያለብህን ነገር አድርገህ ሳታረፍድ በጥሩ ስሜት ወደ ስራህ እንድትወጣ ይረዳሀል።


ቀንህን የጀመርክበት ሙድ ቀኑን ሙሉ ይከተልሀል፤ ስለዚህ ቀንህን በጥሩ ስሜት መጀመር አለብህ። ፈገግታ ሙድህን አሪፍ ያደርገዋል፤ ጭንቀትን ይቀንሳል፤ በሽታን የመከላከል አቅምን እንደሚጨምር እና እድሜንም እንደሚያረዝም በሳይንስ ተረጋግጧል።


በህይወትህ ለተሰጠህ መልካም ነገሮች በዙሪያህም ስላሉ ሰዎች አመስግን።
ላለህ ስታመሰግን የሌለህ ይጨመርልሀል።


በቀን ውስጥ ልትሰራ ያሰብካቸውን ነገሮች በወረቀት ላይ ፃፋቸው። እቅድን በወረቀት ላይ መፃፍ ይበልጥ እንድታስታውሰው እና እንድታቀናጀው ይረዳሀል። በዚህም የተሻለ ውጤታማ ቀን እንዲኖርህ ይረዳሀል።


ጠዋት ላይ መጠነኛ የአካል-ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ቀኑን የምታሳልፍበትን energy ከፍ ያደርጋል፤ ትኩረት፣ ንቃትን እና ግንዛቤንም ይጨምረል።

𝗚𝗼𝗻𝗱𝗮𝗿𝙏𝙝𝙚 𝙘𝙖𝙢𝙚𝙡𝙤𝙩 𝙤𝙛 𝘼𝙛𝙧𝙞𝙘𝙖 Gondar, the center of Ethiopian politics, art and culture, is famous for its many medieval c...
08/11/2022

𝗚𝗼𝗻𝗱𝗮𝗿
𝙏𝙝𝙚 𝙘𝙖𝙢𝙚𝙡𝙤𝙩 𝙤𝙛 𝘼𝙛𝙧𝙞𝙘𝙖

Gondar, the center of Ethiopian politics, art and culture, is famous for its many medieval castles and the design & decoration of its churches. The historical Gondar city was founded by Emperor Fasil in 1632 and served as the royal capital of Ethiopian emperors for about 250 years.

The foundation of this imperial capital witnessed a period of optimism and renaissance from the golden days of Aksum and Lalibela architecture, literature, education, music, painting and commerce that ended after that period and gradually rose to prominence.

Gondar is situated in northwestern Ethiopia, at about 727 and 175 kilometers away from Addis Ababa and Bahir Dar respectively. Its altitude is about 2200 meters above sea level.

The royal medieval capital has valuable heritage to offer for visitors. The construction of the castles, the baths and churches remain intact to this day. The castles of Gondar have been registered as world heritage sites by UNESCO since 1979.

𝗖𝗼𝗺𝗲 & 𝗘𝘅𝗽𝗹𝗼𝗿𝗲 𝗺𝗼𝗿𝗲

ይህንን ያውቁ ኑሯል⁉️""ያሎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው እባክዎን ሂሳቦን ይምሉ  ""የምትለው ሴት ይህቺ ናት🙆   ህሊና ተፈራ ትባላለችበአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ትኖራለች። በሚሊዮን የሚቆጠር...
06/11/2022

ይህንን ያውቁ ኑሯል⁉️

""ያሎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው እባክዎን ሂሳቦን ይምሉ ""
የምትለው ሴት ይህቺ ናት🙆
ህሊና ተፈራ ትባላለች

በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ትኖራለች። በሚሊዮን የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ በድምፅ ያውቃታል። ሞባይል በአገራችን ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ድምፅዋ አለ።

"ያልዎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው፣ መስመሩ ስለተያዘ እባክዎን ትንሽ ቆይተው ይደውሉ፣ ደምበኛው ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ናቸው" እነዚህን የመሰሉ ድምፆች የህሊና ተፈራ ናቸው። ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተወልዳ ያደገችው ህሊና ልቅም ያለች ቆንጆ ናት! በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ፣ በደርጉ ፕ/ት ፅህፈት ቤት ልዩ ረዳት ዘጋቢ፣ በኃላም በሚድሮክ C.E.O (ከእሷ በኃላ ቦታውን ዶ/ር አረጋ ያዙት) እንዲሁም የጥረት መፅሄት አዘጋጅ ነበረች። ህሊና ስትለቅ መፅሄቱም ቆመ። የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ህሊና ወንድ ልጇ በአሜሪካ ድምፅ ሲሰራ፣ ሴት ልጇ በሞንቶጎሞሪ ትሰራለች።

ጉልቱ ተፈራ የህሊና ወንድም ነው። ሙዚቃ መሳሪያ ይጫወታል፣ የተማረና ብሩህ አእምሮ ከንፁህ ልብ ጋር የተጎናፀፈ ነው። በነጉልቱ ቤት ማንም ሰው ገብቶ በልቶ ጠጥቶ የሚወጣበት ነው! በጣም መልካም ቤተሰብ ነው!

ትግራይ ሀገርትግራይ ከ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ መቐለ ነው። ሌሎች ታዋቂ ከተሞች ውቅሮ፣ ዛላምበሳ፣ ዓብዪዓዲ ፣ዓድዋ፣ነበለት፣ ሸራሮ፣ዓዲግራት፣ አኽሱም፣ ሽረ እን...
05/11/2022

ትግራይ ሀገር

ትግራይ ከ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ መቐለ ነው። ሌሎች ታዋቂ ከተሞች ውቅሮ፣ ዛላምበሳ፣ ዓብዪዓዲ ፣ዓድዋ፣ነበለት፣ ሸራሮ፣ዓዲግራት፣ አኽሱም፣ ሽረ እንዳስላሰ፣ ማይጨው ናቸው። የሕዝብ ብዛት በ1999 ህዝብ እና ቤት ቆጠራ መሰረት 7.9 ሚልዮን ነው። ትግርኛ የክልሉ ዋና ቋንቋ ነው። እምባ ኣላጀ፣ ፅበት እና ወርሐት በትግራይ ሀገር ያሉ ከፍተኛ ቦታዎች ናቸው። ትግራይ በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሃብቶች የታደለ ሀገር ነው።የሓ ጥንታዊ ቤተ መቅደስ፣ የአክሱም ጥንታዊ ሃውልቶች፣ከ4ኛው እስከ 15ኛው ክ/ዘመን እንደተሰሩ የሚታወቀው ከ120 በላይ የሚሆኑ ከኣለት ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ውቅር ኣብያተክርስትያናትና ገዳማት እንዲሁም ሌሌች በርካታ ታሪካዊና ኣርኪኦሎጂካዊ ስፍራዎች የሚገኙበት ሀገር ነው። ትግራይን በባህልና በታሪካዊ ኣመጣጥ ከኤርትራ ነጥሎ ማየት ኣይቻለም። የዳኣማትና የአክሱም ግእዛዊ ስልጣኔ ባለቤት ናት። ዓድዋ

ግብፅ ከአባይ ወንዝ በተሰበሰቡ የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች የአለማችንን ትልቁን የቆሻሻ ፒራሚድ ሰራች።ይህ የተዘጋጀው በቅርቡ በአገሪቱ የሚከናወነውን የአለም የከባቢ አየር ጉባኤ በማስመልከት ነው...
04/11/2022

ግብፅ ከአባይ ወንዝ በተሰበሰቡ የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች የአለማችንን ትልቁን የቆሻሻ ፒራሚድ ሰራች።
ይህ የተዘጋጀው በቅርቡ በአገሪቱ የሚከናወነውን የአለም የከባቢ አየር ጉባኤ በማስመልከት ነው። የፒራሚዱ ቁመት 10 ሜትር ሲሆን የጎን ስፋቱ ደግሞ 12 ሜትር ነው።

ሥንሡል  | "በውስጡ የሰማይና የምድር ካርታን በመያዙ ከኹሉም ሕዋሳት የሰው ጣት ይገርመኛል። የጠቢባን ጣቶች ጥበብን ያስቀምጡበታል። የጠበኛ ጣቶች ግን የክፋት ድንጋይን ለወንድማቸው ይጨብጡ...
03/11/2022

ሥንሡል

| "በውስጡ የሰማይና የምድር ካርታን በመያዙ ከኹሉም ሕዋሳት የሰው ጣት ይገርመኛል።

የጠቢባን ጣቶች ጥበብን ያስቀምጡበታል።

የጠበኛ ጣቶች ግን የክፋት ድንጋይን ለወንድማቸው ይጨብጡበታል፤ በጽሑፉቸውም ሰውን ይረግሙበታል፣ ይሰድቡበታል"

👉 "አዋቂ ስትኾን ተፈጥሮን ትሰማለህ። ጠቢብ ስትኾን ግን ተፈጥሮ እራሷ አንተን ትሰማሃለች።

ዐዋቂዎች በዩንቨርስ ውስጥ እንዳሉ ያውቃሉ። ጠቢባን ግን ዩኒቨርስ በእነርሱ ውስጥም እንዳለች ይረዳሉ"

👉 የዋዘኞች ጆሮ ሐሜትን፣ ስድብን፣ የሰውን ውድቀት መስማት ቀለቧ ነው። የዐዋቂዎች ጆሮ ግን እውነትን፣ ጥበብን፣ የሰዎችን ትንሣኤ መስማት ያስደስታታልና ብቻዋን ለትንሣኤ መድረስን ፈጣሪዋ ያድላታል"

(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
💥ኢትዮጵያ ካሏት ከብራና፣ ከጥቅል በመቀጠል የሚታወቀው ብዙዎች ነገራት በአንድ ላይ አካትቶ ከያዘው "ሥንሡል" ጋር💥

photo credited: Haymanot

እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።                        ትንቢተ ኢሳ ፶፫፣...
22/04/2022

እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
ትንቢተ ኢሳ ፶፫፣፭
ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።
ዮሐ ፻፭፣፻፫

ኪሪያ ላይሶን! ጌታ ሆይ ይቅር በል!
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ!
አቤቱ በመንግስትህ አስበን!

15/02/2022
06/02/2022

Address

Bahir Dar

Telephone

+251919107160

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የካሜራ እይታ - camera veiw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share