Mykey's Journey

Mykey's Journey Photographer & Storyteller 🇪🇹
• Passionate about people and meaningful Stories • • Passionate about people and all things story•

‘’ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ : ዲያብሎስን አሰረው : አዳምን ነጻ አወጣው : ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ’’📍 በቦሌ ደብረሳሌም መድኃኔዓለም፤ መጥምቁ ...
12/04/2026

‘’ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ : ዲያብሎስን አሰረው : አዳምን ነጻ አወጣው : ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ’’

📍 በቦሌ ደብረሳሌም መድኃኔዓለም፤ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ሚያዚያ ፳፻፲፰ ዓ.ም - April 2026
Addis Ababa, Ethiopia

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእንጨት መስቀል ላይ እንዴት እጅህን ዘረጋህ? በችንካርስ እንዴት ተቸነከርክ? ለትሕትናህ አንክሮ ይገባል። ጌታዬ እየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዴት አወረዱህ? ለሞት እ...
10/04/2026

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእንጨት መስቀል ላይ እንዴት እጅህን ዘረጋህ? በችንካርስ እንዴት ተቸነከርክ? ለትሕትናህ አንክሮ ይገባል።

ጌታዬ እየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዴት አወረዱህ? ለሞት እስክትደርስ ድረስ አዳምን ልታድነው እንዴት ወደደህ? አንደበት ካላቸው ሰዎች ለክብርህ ምስጋናን ያቀርብልህ ዘንድ የሚቻለው ማነው?

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አዳኝ የሆነ መስቀልህን አቅፈው ዘንድ ከእርሱም የመዳን እና የህይወት መዓዛ አሸት ዘንድ አድለኝ።

ንጽሕ ደምህ በኅሊናዬ ይውረድ። አንተ የህይወት መንፈስ ነህ። በመስቀል ላይ መጸጻና ሐሞት የጠጣህ ጌታይ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ንጽሕ ፍቅርን አጠጣኝ። ከመራራ ሞትም አድነኝ።

የስምዖን አምዳዊ ጸሎት (የአርብ)
ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ሚያዚያ ፳፻፲፰ ዓ.ም - April 2026
Addis Ababa, Ethiopia

21/03/2026

Mule + Kal

📍 ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን(አዲሱ ሚካኤል)
Background Mezmur -

16/03/2026

When I was a child, I used to go to the Serek Gubae with my mother. As soon as it ended, she would tell me to put the chairs back in their place and return to her immediately.

07/03/2026

Matias + Winta

For booking and information ☎️ +251916565758

ለረጅም ጊዜ የራሴ የሆነ፣ ስራዎቼን በትክክል የሚገልጽ ዌብሳይት እንዲኖረኝ እመኝ ነበር። ነገር ግን የፈለኩትን ያህል ጥራት ያለው ስራ የሚሰራልኝ ባለሙያ ማጣትና የፍላጎቶቼ መብዛት ነገሩን ...
18/02/2026

ለረጅም ጊዜ የራሴ የሆነ፣ ስራዎቼን በትክክል የሚገልጽ ዌብሳይት እንዲኖረኝ እመኝ ነበር። ነገር ግን የፈለኩትን ያህል ጥራት ያለው ስራ የሚሰራልኝ ባለሙያ ማጣትና የፍላጎቶቼ መብዛት ነገሩን አዘግይቶት ቆይቷል። እርግጥ ነው፣ ሁሉም ትልቅ ነገር የራሱ የሆነ ታሪክ እና ድካም አለው!

ይህ ዌብሳይት ከፎቶግራፎቼ ባሻገር፣ አሳቦቼን የምታነቡበትና ስራዎቼን በቀጥታ የምትገዙበት ዲጂታል መሥሪያ ነው።

ምን አዲስ ነገር አለው?
1. (Online Store) - ያነሳኋቸውን ፎቶዎች (Photography Prints) በቀጥታ ከዌብሳይቱ ላይ መግዛት ትችላላችሁ።

2. ቀላል ክፍያ ከ Chapa ጋር በተደረገ ትብብር፤ በቴሌብር፣ በሲቢኢ ብር፣ በኤም-ፔሳ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ካርዶች በደህንነት መክፈል ይቻላል።

3. (Online Booking) - ለፎቶግራፍ አገልግሎቶች (ለሰርግ፣ ለግል ፎቶዎች ወይም ለድርጅታዊ ስራዎች) ካሉበት ሆነው በቀላሉ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ።

ይህ ዌብሳይት የመጨረሻው ውጤት አይደለም፤ የእናንተ አስተያየት ታክሎበት ይበልጥ እንዲያምር እንፈልጋለን። ይህን ራዕዬን ወደ እውነታ ለቀየሩልኝ ለ ትልቅ ምስጋና ይድረሳቸው።

ሙሉ ጉዞውን ዶክመንት ለማድረግ ስለሞከርን በቅርቡ ከሚኖረን የStorytelling ቪዲዮ ላይ ትመለከቱታቹ።

እስቲ ዌብሳይቱን ጎብኙትና ያላችሁን አስተያየት በኮመንት አጋሩኝ!
www.mikiyasliyew.com

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
የካቲት ፳፻፲፰ ዓ.ም - February 2026
Addis Ababa, Ethiopia

አንዳንዴ ንጋት ላይ ከእንቅልፌ ስነቃ ራሴን የምጠይቀው አንድ ጥያቄ አለ፤ “ለመሆኑ ምን ዓይነት ድንቅ አምላክ ነው ያለን?” የእግዚአብሔርን ረቂቅ መንገድና እርሱ በሰው ልጅ ድካም ውስጥ የሚ...
27/01/2026

አንዳንዴ ንጋት ላይ ከእንቅልፌ ስነቃ ራሴን የምጠይቀው አንድ ጥያቄ አለ፤ “ለመሆኑ ምን ዓይነት ድንቅ አምላክ ነው ያለን?” የእግዚአብሔርን ረቂቅ መንገድና እርሱ በሰው ልጅ ድካም ውስጥ የሚተክለውን ጽናት ሳስበው ይገርመኛል። ከኖርኩበትና ካለፍኩበት ሕይወት የተረዳሁት አንድ ትልቅ እውነት አለ፤ መኖር ማለት ወዲያ ወዲህ ማለት ስለቻልን ብቻ እዚያም እዚህም ማለት አይደለም። መኖር አንዳንዴም በቆሙበት ስፍራ ጸንቶ መታየትም ጭምር ነው። ወንጌላዊው “በመጽናትችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ” (ሉቃስ 21፥19) የሚለን ለዚህ ሳይሆን አይቀርም።

“አንድ ቦታ መቆም ብቻ እንዴት መጽናት ይሆናል?” ካላችሁኝ፤ በባዕታቸው ተወስነው፣ ከዓለም ጫጫታ ርቀው በአንዲት ስፍራ የሚኖሩትን መነኮሳት ተመልከቱ። እግዚአብሔር ምንም አልነሳቸውም፤ ይልቁንም በገዳም ሕይወታቸው ጸንተው ዓለምን በመናቃቸው እግዚአብሔር በረከትና ጸጋውን አትረፍርፎላቸዋል።
ሕይወት አንዳንዴ ፍጥነታችንን እንድንቀንስ፣ ሩጫችንን እንድናቆም በድንገት ታስገድደናለች። በዚያ የጸጥታ ጊዜ ውስጥ ግን ከቃላት በላይ የሆነ ትልቅ ምስክርነት ይወለዳል። በአንዳንድ የቅርብ ሰዎች ላይ የማየው የአካልን መድከም ሳይሆን፣ የማይሰበር የነፍስ ጽናትን ነው። ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን በአንድ ትምህርታቸው እንዲህ ብለው ነበር፦

“እግዚአብሔር አንዳንዴ በዝምታ ያስተምራል፤ እግርህ ሲቆም ልብህ እንዲራመድ፣ ዓይንህ ሲጨልም የውስጥ ብርሃንህ እንዲበራ ያደርጋል። ” ይህ ምስጢር ዛሬ ከረፈደ እየገባኝ ነው። ያለማማረር መኖር፣ በፈተና መካከል ሳይሳቀቁ ፈገግ ማለት፣ እና በእያንዳንዱ እስትንፋስ ውስጥ የፈጣሪን ቸርነት መፈለግን ስመለከት ትልቁን የሕይወት ትምህርት እየተማርኩ እንደሆነ ይሰማኛል።

የሚገርመው ደግሞ እግዚአብሔር የልብን ቅንነት አይቶ የሚሰጠው በረከት እጄን በአፌ ላይ ያስጭነኛል። ለዛለ ማንነት ምርኩዝ የሚሆን፣ በፍቅር የሚያቅፍ፣ በምክንያት የተሰጠ “ረዳትን” አብሮ ሲያድል ሳይ የእግዚአብሔር ምህረት ይበልጥ ይገለጥልኛል። ጠቢቡ ሰሎሞን “ሁለት መሆን ከአንድ ይሻላል... ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሳዋልና” (መክብብ 4፥9-10) ያለው ቃል፤ በብረት ላይ ሳይሆን በፍቅር ክንድ ላይ ስንደገፍ እውነትነቱ ይበልጥ ይበራልናል።
እኛ የምንኖረው በራሳችን ጉልበት ሳይሆን፣ እርሱ በላከልን ደግ ሰውና በሚሰጠን ጸጋ ነው። ዛሬም ነገም የምናየው ብርሃን፣ በሂደት ላይ የምናገኘው የሕይወት ዕረፍት ሁሉ “እግዚአብሔር ቸር ነው!” ያስብለናል።

ወዳጄ ሆይ! ሕይወት በቆምንበት ስፍራ ሁሉ ውበት አላት። መጓዝ የሚቻለው መሬቱን ስለረገጥን ብቻ ሳይሆን፣ ተስፋን ስላቀፍን ነው። በእርግጥም መኖር ይቀጥላል።

In Frame መቅደስ ደጀኔ -

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ጥር ፳፻፲፰ ዓ.ም - January 2026
Addis Ababa, Ethiopia

F A C E O F T I M K E T ሚከያስ ልየው | Mikiyas Liyew ጥር ፳፻፲፰ ዓ.ም - January 2026Addis Ababa, Ethiopia
19/01/2026

F A C E O F T I M K E T

ሚከያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ጥር ፳፻፲፰ ዓ.ም - January 2026
Addis Ababa, Ethiopia

እኔ ናታኔም፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ። ነብስ አውቄ የጥምቀት በዓልን ማክበር ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ የማስታውሰው ትልቁ ትዕይንት፤ የሰፈር ወጣቶች በከባድ ድካም ውስጥ የሚያሳዩትን ያን...
18/01/2026

እኔ ናታኔም፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ። ነብስ አውቄ የጥምቀት በዓልን ማክበር ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ የማስታውሰው ትልቁ ትዕይንት፤ የሰፈር ወጣቶች በከባድ ድካም ውስጥ የሚያሳዩትን ያንን የማይጠፋ ሰማያዊ ፈገግታ ነው።

ጥምቀት ሲመጣ የከተማዋ የነተቡ ገፅታዎች ቀለም ይቀባሉ፣ ሰንደቅ ዓላማዎች በየመንገዱ ይውለበለባሉ፤ የጥምቀተ ባሕሩ ዳርቻ በመብራት አጊጦ ሌሊቱን እንደ ቀን ያበራል። ነገር ግን ከቀለሙና ከመብራቱ ጀርባ ሌላ ትልቅ እውነት አለ። ወጣቶች የሰፈራቸውን ታቦት ለማጀብ የሚከፍሉት መስዋዕትነት! ገንዘብ ያዋጣሉ፤ ያንንም የተዋጣች ብር በአግባቡ ተጠቅመው ለታቦቱ ማረፊያና ለሰረገላው ውበት ያውሉታል። ገንዘብ ማዋጣትና ማስተባበር ይቻል ይሆናል፤ ፈታኙና ትልቁ ነገር ግን በበዓሉ ዕለት ያንን ረጅም ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ምንጣፍ መሸከምና መዘርጋት ነው።

እነዚያ ወጣቶች ጎንበስ ብለው ምንጣፉን ሲዘረጉ፣ ላባቸው እንደ ዶፍ ሲወርድ፣ “አረፍ በሉ” የሚላቸው ሳይኖር የሚጋደሉት ለምንድነው?

ዛሬ ትኩር ብዬ ሳየው አንድ እውነት የገባኝ መሰለኝ። የሚነጠፈው ምንጣፍ ብቻ አይደለም፤ ዓመቱን ሙሉ የበደልነውን፣ ያስቀየምነውንና የራቅነውን አምላክ በአደባባይ ስናገኘው “ልባችንን አንጥፈን” የምንቀበልበት ንስሐ እንጂ።

በእርግጥም፣ እስኪያልበን የሠራነውን ኃጢአት፣ እስኪምረን ድረስ በዚህኛው ላብ የምንተካው ይመስለኛል። ያንኑ የጥፋት ላብ፣ በዚህኛው የቅድስና ላብ የምናጥብበት የነፍስ ትግል ነው።

ታቦታቱ በምንጣፉ ላይ ሲያልፉ፣ እኛ ደግሞ በጸጸትና በፍቅር የተዘረጋውን ልባችንን እያስባረክን ነው። ወጣቶቹ ምንጣፉን ሲጠቀልሉ፣ የቆሸሸ ማንነታቸውን አብረው ጠቅልለው የሚጥሉ ይመስለኛል። በዚህ በዓል ላይ ዛሬ የገባኝ ጥበብ ይሄው ነው።

ምንጣፍ ሳይሆን ልብን ማንጠፍ!

ሚከያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ጥር ፳፻፲፰ ዓ.ም - January 2026
Addis Ababa, Ethiopia

ለአንድ ወዳጃችን ልደት “እንኳን ተወለድክ” ለማለት ቃላት ይቸግሩናል። አንዳች አዲስ የፍቅር መግለጫ ፍለጋ ማኅበራዊ ገጾችን እናስሳለን፤ ከልባችን ስሜት ይልቅ በጥሩ ለዛ የቀረቡ ቃላትን እን...
07/01/2026

ለአንድ ወዳጃችን ልደት “እንኳን ተወለድክ” ለማለት ቃላት ይቸግሩናል። አንዳች አዲስ የፍቅር መግለጫ ፍለጋ ማኅበራዊ ገጾችን እናስሳለን፤ ከልባችን ስሜት ይልቅ በጥሩ ለዛ የቀረቡ ቃላትን እንመርጣለን። ዛሬ ግን የፍቅር ሁሉ ምንጭ፣ የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆነው የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነው!

ለዚህ ድንቅ ዕለት ምዕመናን ሁሉ እንደ ሰባሰገል በብርሃን ተመርተው፣ በየአቅጣጫው ለምስጋና ተሰባስበዋል። “ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ” እያሉ ለማዜም፤ ገሚሱ ወደ ቅዱስ ላሊበላ አቅንቷል፣ ገሚሱ ደግሞ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በ”አእላፋት ዝማሬ” ተገኝቷል። በኋላም በየአብያተ ክርስቲያናቱ በማኅሌትና በቅዳሴ ተሳታፊ በመሆን፣ የክርስቶስን ልደት ባለቤቱ በሚወደውና በሚከብርበት መንገድ አክብረናል።

አንድን ሰው “እንኳን ተወለድክ” ስንለው ትንሹ የምስጋናችን መግለጫ የሚወደውን ነገር ማድረግ ነው። ለመሆኑ ለእግዚአብሔር ልደት ምን እናድርግለት ይሆን? እርሱስ በምን ደስ ይለው ይሆን? ትልቁ ስጦታችን በበጎ ምግባር የታጀበ የፍቅር ልብ ነው፤ እርሱ የቤተክርስቲያን አምባሳደሮች እንድንሆን ይሻል።

ይህ በየቦታው መገኘታችን መለያየት ሳይሆን የምስጋና ስፋት (ስፋተ-ስብሐት) ነው። በዚያች የቤተልሔም ምሽት መላእክት በሰማይ ሲዘምሩ፣ እረኞች በምድር ድምፃቸውን ሲያስተጋቡ የሰማዩ ዜማ የምድሩን ድምቀት አልሸፈነውም፤ ይልቁንም ሰማይና ምድር በአንድ ዜማ የልደቱን ብርሃን አበሰሩ እንጂ። ዛሬም በላሊበላ የሚወርደው ማኅሌትና በአደባባይ የሚሰማው ዝማሬ ምንጩ አንድ ነው— እርሱም ምስጋና ለእግዚአብሔር!

እኛም የዓለምን ግርግር ትተን ከመላእክቱ ጋር እንዲህ እንላለን፦

ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ” (ሉቃስ 2:14)
ስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ሰላምም ለሰው

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ።



ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ | Addis Ababa,Ethiopia
ታኅሣሥ ፳፱-፳፻፲፰ ዓ.ም

Address

Addis Ababa

Telephone

+251916565758

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mykey's Journey posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mykey's Journey:

Share

Category