Afla fikir/አፍላ ፍቅር

Afla fikir/አፍላ ፍቅር አፍላ ፍቅር

09/06/2026

ይድረስ ለመከላክያ ሰራዊት

08/06/2026

አባታችን እርስዎ ምን ያድርጉ በተኩላ ተከበው እግዚአብሔር መፍትሄውን ያምጣልን

08/06/2026

Fifa world cup 2026 new Rule

08/06/2026

ጨርሳችሁ ሱሙት

የኢራቅ ኦርቶዶክሳዊያን መከላከያ ሠራዊት።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።እነ አይኤስ አልቃኢዳን ተደራጅተው የሚከላከሉ የኢራቅ ክርስቲያኖች።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።...
08/06/2026

የኢራቅ ኦርቶዶክሳዊያን መከላከያ ሠራዊት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

እነ አይኤስ አልቃኢዳን
ተደራጅተው የሚከላከሉ የኢራቅ ክርስቲያኖች።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

፦የኢራቅ ኦርቶዶክሳዊያን የሚጠብቃቸው መንግስት ቢያጡ ራሳቸውን አደራጅተው መታገል ጀመሩ።

፦በኢራቅ ዛሬ ኦርቶዶክሳዊያኑ ቤተክርስቲያናቸውን፣ምዕመኑን፣ከተማቸውን የሚጠብቁት ባደራጁት ጠንካራ ሠራዊታቸው ነው።

፦ይፀልያሉ፣በአገልግሎት ይሳተፋሉ፣ያስቀድሳሉ፣ይቆርባሉ፣ያስተምራሉ፣ይከላከላሉ፣ዘብ ይሆናሉ።

፦ደካማ በሆነ መንግስት ብቸኛው አማራጭ ራስን አደራጅቶ መከላከል ነው።

፦በነብር ዘመን ፍየል መሆን መጨረሻው መበላት ነው።

፦ግራህን ቢመቱህ ቀኝን ስጥ የሚለው ቃል እምነትህን ለሚያስለውጥ፣ለሚገልህ ጨካኝ አረመኔ አይደለም።

፦ጥቂት ቢሆኑም ጠንካራ ናቸው፣ጥንታዊ ህዝቦች ናቸው በእምነታቸው አይደራደሩም፣ፈፅሞ ማተባቸውን የሚበጥስ ሲመጣ ቆራጥ ናቸው።

፦ሁለት ሺህ ዓመታት ያህል በክርስትና ኖረዋል ከሁለት ሚሊየን ይበልጣሉ ቁጥራቸው በመከራና በስቃይ ውስጥ ነጥረው የወጡ የክርስቶስ ምርጥ ዘሮች ናቸው።

፦መንግስት ቢኖራቸውም ደካማና ሊከላከልላቸው የሚችል አይደለም ስለዚህ ተሰባሰቡ፣ተደራጁ፣ተናበቡ ራሳቸውን ከገዳዬቻቸውና ከአጥፊያቸው ለመከላከል የጦር መሣሪያ አነሱ ገዳዩንና ጨካኙን አልቃኢዳንና መሰሎቹን መከቷቸው እምነታቸውን ጠበቁ፣ምዕመናኖቻቸውን ታደጉ አሁን ማንም የማይደፍራቸው ፅኑዓን ወታደሮች ሆነው ቤተክርስቲያኖቻቸውንና ምዕመናኖቻቸውን የሚጠብቁ የክርስቶስ ወታደሮች ሆነዋል።

ዛሬ በኢራቅ የሚኖሩትን ኦርቶዶክሳዊያን የሚገድላቸው የለም ራሳቸውን አደራጅተዋልና።

08/06/2026

ቤተክርስቲያን ስደትላይ ነች

08/06/2026

የሰንደቅ ዓላማ ፕሮቶኮል

በአንድ ሀገር ለንጉሡም ለሕዝቡም ያስቸገረ ሌባ ነበር። ንጉሡ ሕዝቡን ሰብስቦ ሌባውን መዘው እንዲሰጡት ቢያባብልም ሌባውን የሚያውቅ በመጥፋቱ ሊሆን አልቻለም፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ንጉ...
07/06/2026

በአንድ ሀገር ለንጉሡም ለሕዝቡም ያስቸገረ ሌባ ነበር። ንጉሡ ሕዝቡን ሰብስቦ ሌባውን መዘው እንዲሰጡት ቢያባብልም ሌባውን የሚያውቅ በመጥፋቱ ሊሆን አልቻለም፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ንጉሡ በሀገሩ ካለ ሰፊ ሜዳ ላይ ሕዝቡ ሁሉ እንዲኮለኮል አደረገ፡፡ እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ሕዝቡ ሌባውን እንዲያ ጋልጥና እንዲሰጠው ተናገረ፡፡ ግን ምንም ፍንጭ የለም። በዚህ ጊዜ በአካባቢው ካለ አንድ ጨለማ ቤት ውስጥ አንድ አህያ እንዲታሰር አደረገና ለሕዝቡ የሚከተለውን መመሪያ አስተላለፈ እንዲህ ሲል «እዚያች ትንሽ ቤት ውስጥ አንድ አህያ ታስሯል፡፡ ሁላችሁም በተራ ወደዚያች ክፍል እየዘለቃችሁ የአህያውን ጭራ ትጨብጣላችሁ፡፡ በዚህ ጊዜ አህያው ሌባው ሲነካው ያናፋል ያኔ ሌባውን እናው ቀዋለን፡፡» ይላል፡፡ በሌባው ምክንያት ሊታወክ የሰነበተው ሕዝብ ደስ አለውና ሒደቱ ቀጠለ፡፡ ሕዝቡም ሁሉ በየተራ እየገባ የአህ ያዋን ጭራ እየጨበጠ ይወጣ ጀመር፡፡ ኹኔታው ቀጥሎ የሌባው ተራ ይደርስና ወደጨለማው ቤት ይዘልቃል ከቤቱ ውስጥ ከአህያዋ በስተቀር ምንም የለም፡፡ ሌባው ግራና ቀኙን ዐይቶ ተመልካች ስለሌለው የአህያውን ጭራ ቢነካ ያጋልጠኛል ብሎም ስላሰበ አንተ አህያ ሞኝህን ፈልግ ይልና ጭራውን ሳይጨብጥ እንዲሁ ይወጣል፡፡ በልቡም ሠራሁለት ይኽ ጅል ንጉሥ ይላል። ሕዝቡ ሁሉ ድርጊቱን ፈጽሞ ሲያበቃ ንጉሡ ዙሪያውን ካስከበበ በኋላ እያን ዳንዱን ሰው ወደዙፋኑ እንዲቀርብ እያደረገ የሁሉንም እጅ እጃቸውን ማሽተት ይጀምራል፡፡ ይህንን ያደረገው ያለምክንያት አልነበረም:: የአህያውን ጭራ ውድና ልዩ የሆነ ሽቱ ቀብቶት ስለነበር እንጂ፡፡ ሌባው ሆዬ ሀገር ሰላም ብሎ መዳፉን ለንጉሡ ይሰጥና ሲሸተት ባዶ ሆኖ ይገኛል...ከዚያማ ያው እርምጃ ይወስ ድበትና ሀገሪቷ በንጉሡ ብልኀት ከመታወክ ዳነች ይባላል፡፡
***
አበው ሲናገሩ «እውነተኛ ፍርድ እውነተኛ ዳኛ እስኪገኝ ይዘገያል» ይላሉ፡፡ በዚህ ታሪክ በኃይል መጠቀምን በጥበብ ማስተዳደር ሲለቀውም እናያለን፡፡ ሁልጊዜ አጭበርባሪ እንደሆኑ አይዘልቅምና ራሳችንን ወቅሰን ንስሐ መግባቱ ብልህነት ነው፡፡

ለአሥር ዓመታት ያህል ኪርክ አሌክሳንደር የተባለ ግለሰብ በሳሌም፣ ኦሪገን ከሚገኘው ዶሚኖስ ፒዛ ቤት በየምሽቱ ማለት ይቻላል ምግብ ያዝዝ ነበር። ፒዛ፣ ሰላጣ፣ የዶሮ ስጋ — ምን እንደሚያዝ ...
07/06/2026

ለአሥር ዓመታት ያህል ኪርክ አሌክሳንደር የተባለ ግለሰብ በሳሌም፣ ኦሪገን ከሚገኘው ዶሚኖስ ፒዛ ቤት በየምሽቱ ማለት ይቻላል ምግብ ያዝዝ ነበር። ፒዛ፣ ሰላጣ፣ የዶሮ ስጋ — ምን እንደሚያዝ ጉዳዩ አልነበረም ዝም ብሎ በየቀኑ ግን ያዝ ነበር። አስፈላጊው ነገር ስሙ በዚያ የደንበኞች ገጽ ላይ አለ ሁሌም ሌሊት ፣ ከምሽቱ 5ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት ባለው ጊዜ ውስጥ ያዝ ነበር።

ከዚያ አንድ ቀን አቆመ።

ሠራተኞቹ አስተዋሉ። ዳታቤዝ ተመለከቱ። አሥራ አንድ ቀናት ሆኖታል። ኪርክ በአሥራ አንድ ቀናት ውስጥ አላዘዘም፣ እናም ይህን ቦታ እንደ ሁለተኛ ኩሽናው ለሚጠቀም ሰው ይህ የማይታሰብ ነገር ነበር።

አስተዳዳሪዋ ሳራ ፉለር አንድ ሹፌር በሌሊት 7 ሰዓት ላይ ወደ ቤቱ ላከች — ምግብ ሳይሆን፣ አሳቢነቷን ይዛ የደንበኛዋ ነገር አልሆንልህ ቢላት የሰላም ይሆን? በሚል። ቤቱ ሲደረስ መብራቶቹ በርተው ነበሩ። ቴሌቪዥኑ ጮክ ብሎ ይሰማ ነበር። ሾፌሩ በሩን ያንኳኳል ግን መልስ አላገኘም። ስልኩ በቀጥታ ወደ ድምጽ መልእክት ይሄድ ነበር።

911 ደወለች።

ፖሊሶች በሩን ሰብረው ሲገቡ፣ ኪርክን መንቀሳቀስ ወይም እርዳታ ለመጥራት በማይችል ሁኔታ ወለሉ ላይ ተኝቶ አገኙት። ዶክተሮች ሌላ 24 ሰዓት ቢቆይ በሕይወት እንደማይኖር ተናገሩ።
አስገራሚው ክስተት እሱን ያዳነው ዶክተር አልነበረም። ያዳነው በአጋጣሚ ያስተዋለ ጎረቤት አልነበረም። ያዳነው የፒዛ ማድረሻ ሠራተኞች ቡድን ለደንበኛቸው ልማድ በቅርበት ትኩረት ሰጥተው፣ አንድ ነገር እንደተሳሳተ ስለተሰማቸው ነበር።

ኪርክ አሌክሳንደር በሕይወት ያለው በዶሚኖስ ውስጥ አንድ ሰው — «ያ እሱን አይመስለውም» ብሎ በማሰቡ ነው።

ከሳምንታት በኋላ፣ ሠራተኞቹ አበባና ካርድ ይዘው በሆስፒታል ጎበኙት። ኪርክ በማወቅ ፈገግታ ተቀበላቸው። እሱ ቀድሞውኑ ያውቅ ነበር።

አንዳንድ ጊዜ እርዳታ የምታገኘው ከምትጠብቀው ሰው አይሆንም።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afla fikir/አፍላ ፍቅር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category