17/09/2025
ከዚህ በኋላ ማንም ከሩሲያ ዘይት እንዳይገዛ !
/ትራምፕ/
የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አውሮፓውያን የሩስያ ዘይት ግዢን በአስቸኳይ እንዲያቆም ከባድ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ተሰማ ።
ትራምፕ በዩናይትድ ኪንግደም ሊያደርጉት ከሚችለው ጉብኝት ቀደም ብሎ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እየቀጠለ ያለውን ግጭት ለማስቆም “ስምምነት ሊያደርጉ ይገባል” ብለዋል።
ትራምፕ ለዩክሬን ከፍተኛ ድጋፍ ቢሰጡም የሩስያን ሃይል መግዛታቸውን በመቀጠላቸው በአውሮፓ ሀገራት ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል ።
"ፑቲን የገቢ ምንጮቹን በሙሉ ስናደርቅበት ሄዶ ከዘለንስኪን ጋር ስምምነት ማድረጉ አይቀርም ሞስኮ በዩክሬን ውስጥ ለምታደርገው ግጭት የገንዘብ ምንጩ ዘይት ስለሆነ መላዉ አውሮፓም ከሩሲያ ዘይት መግዛቷን ማቆም አለባቸው ። ዛሬ ነገ ሳይሉ አሁኑኑ ከሩሲያ ዘይት መግዛት ማቆም አለባቸው" ብለዋል ትራምፕ።
እነዚህን ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን እንዲያቆሙ በአውሮፓ እና በኔቶ ሀገራት ላይ ጫና እያሳደረ እንደሆነ ሲጠየቁ ትራምፕ ያለምንም ማቅማማት አቋማቸውን አረጋግጠዋል።
" ችግሩ የኔቶ አባላት ናቸዉ ዛሬም አዉሮፓዉያኑ የሩስያ ዘይት እየገዙ ነው. ከዚህ በኋላ ዘይት እንዲገዙ አልፈልግም, እና በአስቸኳይ ማቆም አለባቸው. ለኛ ፍትሃዊ አይደለም "ብለዋል.
ትራምፕ የሩስያ እና የዩክሬን ግጭት "መቼም ሊሆን የማይገባው ጦርነት" ሲሉ ገልፀው በግጭቱ ውስጥ በተሳተፉት የሁለቱም ሀገራት መሪዎች መካከል ያለው ስር የሰደደ ጥላቻ ነው። ብለዋል ።
"አገሪቱ ችግር ላይ ነች። ግን እንዲቆም አደርገዋለሁ። በስምንት ወራት ውስጥ ሰባት ጦርነቶችን አቁሜያለሁ። በጣም ቀላል ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር፣ ግን አይደለም፣ በዜለንስኪ እና ፑቲን መካከል ከፍተኛ ጥላቻ አለ። እኛ ግን ልንፈታዉ ነው" ሲል አስረግጦ ተናግሯል።
ትራምፕ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ "እነሱ ስራውን እየሰሩ አይደለም፣ ኔቶ መሰባሰብ አለበት፣ አውሮፓ መሰባሰብ አለባት። አውሮፓ ወዳጄ ናት፣ አውሮፓ ግን ከሩሲያ ነዳጅ እየገዛች ነው። ነዳጅ እንዲገዙ አልፈልግም። እና እየጣሉ ያሉት ማዕቀብ በቂ አይደለም፣ እና ማዕቀብ ለመፈጸም ፍቃደኛ ነኝ፣ ነገር ግን የእነርሱን ጥቃት የሚያባብሱትን እርምጃዎች በጥብቅ መከተል አለባቸው" ብለዋል።
በቅርቡ ትራምፕ “ሁሉም የኔቶ አገሮች ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ሲስማሙ እና ሲጀምሩ እና ሁሉም የኔቶ ሀገራት ከሩሲያ ዘይት መግዛት ሲያቆሙ በሩሲያ ላይ ትልቅ ማዕቀብ ለመጣል ዝግጁ ነኝ” በማለት ለኔቶ ሀገራት ደብዳቤ መፃፋቸው ይታወሳል ሲል የዘገበው ሞስኮ ታይምስ ነዉ ።