ቴምር አሳምነው ፅጌ

ቴምር አሳምነው ፅጌ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቴምር አሳምነው ፅጌ, Photographer, Addis Ababa.

01/11/2025

ከአማራነትም ወርዳችሁ በወሎ ቤተ ዐማራ እና በቀጠናችን ላይ ያለውን ትግል ስሜቱን ለማደብዘዝ እዚህም እዛም የምትሉ ፀረ አሳምነው ግለሰቦች እና ቡድኖች ከእኩይ ድርጊታችሁ ታቀቡ እንላለን!!

ወሎ የማይሸጥ የማይለወጥ የአማራ እምብርት ነው።
በትግላችን ውስጥ በቆሞ ቀርነት ፣ በሗላቀርነት ከፍ ሲልም በአካባቢያዊነት የተጠቃችሁ የብልፅግና ሰራጊ አካላት በቀጠናችን ያለውን ትግል እርባና ቢስ እና የጠላት አጀንዳ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ከቁጥቋጦው ስር ጉባኤ ጀምሮ የምታደርጉትን ሁለንተናዊ ሴራ በሚገባ እናውቃለን!!

ስለሆነም ራሱን በአማራ ህዝብ እና በፋኖ ትግል አታጋይነት ስም መንደር ለመንደር ሲንከላወስ የነበረው ቡድን የምኒልክ ዕዝን ውስጣዊ አንድነት ለማናጋት 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ በፈጀው የተላላኪነት ጊዜው ሃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ ተልከስካሹ ቡድን የክፋት ሴራው ራሱን ጠልፎ እየበላው ይገኛል።

የወሎ ቤተ ዐማራን ትግል በተለያዩ ስልቶች ለማጥቃት የሞከረ ቢሆንም በተለይም ከውጭ እና ከውስጥ የሚዲያ አካላት እና ሃይማኖታዊ አጀንዳ ያላቸው ሃይሎችን በመጠቀም ሀሰተኛ ፍረጃ፣ ስም መስጠት፣ለማሰይጠንና እና መሪዎቹን ጭምሮ ለማጠልሸት በብዙ ርቀት ሄዶ ሲሰራ የነበረው ቡድን ሙሉ ለመሉ ፍላጎቱ ሰይሳካለት ቀርቷል።ስለሆነም ተልከስካሹ ቡድኑ ተንኮታኩቶ አጀንዳውም ድርጊቱም መሬት ለመሬት በመንከላወስ እግር እግራቸውን እየተከተለም ራሳቸውን እየጎተታቸው ይገኛል።

ስለዚህ ከውስጣዊ አንድነታችን ጥንካሬ አልፎ የብዙ ፓለቲከኞችን የስርገት አጀንዳ በማክሸፍ ረገድ ምኒልክ ዕዝ የተዋጣለት የፓለቲካ ስራዎችን ሰርቶ አሳይቷል።
ከእንግድህ ወሎ ቤተ ዐማራ በልጆቹ ታሪክ ራሱን እየገነባ፣እያደራጀ እና ጠንካራ አማራዊ ስነ ልቦናን በመፍጠር ሂደት ታሪካዊ ድርሻውንና ሚናውን እየተወጣ አማራዊ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል!!

በጀግናው የወሎ ቤተ ዐማራ ህዝብ ስም አሮጌ ትርክት እያንጠለጠሉ መሳደብ ከእዚህ በሗላ ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠላትም ወዳጅም ጠንቅቆ ያውቀዋል።
ትርክትን የቀየረ አማራዊ ስነ ልቦናውን እና የማድረግ ብቃቱ የተመሰከረለት ሰራዊት እና ህዝብም መፍጠር ችለናል።
አድስ ማንነት ለመፍጠር ከጠላት ጎን አብሮ የሚንገዳገደው ቡድን ሁሉ ይጠረጋል!!

ወሎ ቤተ ዐማራን ሰሜን ኦሮሚያ፣ወሎ ክልል፣ኦነግ ራደፓ፣አክራሪ የሃይማኖት አጀንዳ፣የብልፅግና ሃይሎች እና ሌሎችም ከውጭ እና ከውስጥ ሆነው የወሎ ቤተ ዐማራን ታሪካዊ ማንነት ለመቀማት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን ጭምር እየታገለ የሚገኘውን ምኒልክ ዕዝን ከውስጥ ሆኖ ለጠላት ጠጠር የሚወረውሩ አካላትን በተደጋጋሚ ከመሰል አሻጥራቸው እንዲያቆሙ ስንል አሁንም አበክረን እንጠይቃለን!!

በሌላ መልኩ በትግላችን ውስጥ ውስጣዊ አንድነት እና ጥንካሬያችንን የማይፈልጉ አካላት ከአማራነትም ወርደው በፀረ ወሎየነት ሚናቸውን ለመወጣት ከውዳቂ ቡድኑ ጋር አጀንዳ ለመስጠት ስትሞክሩ ታዝበናል።

ስለሆነም በየሰፈሩ እየተንከላወሱ ፀረ- ድርጅት እና የመንደር- ሹመኛ ሆኖ መቀጠል የሚቻልበት ዘመን አልፏል።
ተጠያቂነት እና ድርጅታዊነትን በደማችን እናሰፍናለን!!
ደም የገበርንበት ተግል በተልከስካሾችንና በመንጋ አዝማቾችም አይደናቀፍም!! ትግላችንና አማራነት ሊስፍን የሚችለው በተግባር መፈተንን፣ፀንቶ ማለፍን፣በርትቶ መስራትን፣ለዓላማ መፅናትን እና ድርጅታዊ ዕሳቤን ማስረፅ ከቻለ ብቻ ነው።

በሃሰት ፍረጃ፣ስም በመስጠት እና የጠላት ተባባሪ በመሆን የምናሳካው ድል እና የምናሸንፈው ትግል የለም!!

ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ጥቅምት 22-02-2018

04/10/2025
28/09/2025

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ነፃ ባጣቸው የሰሜን እና የደቡብ ወሎ ዞን እና ወረዳ ከተሞች ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶች በማድረግ የከረፋውን የብአዴን መዋቀር እየናደ የራሱን መዋቀር እየዘረጋ ይገኛል፡፡

ዛሬ በቀን 18/01/2016 ዓም በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ ከነዋሪው ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

በውይይቱ የተነሱ ኮር ሃሳቦች

1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?
* ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ
* ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ
* የትግሉ ተግዳሮቶች
* የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ

2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ
* በወታደራዊ ቁመና
* በፖለቲካ ተቀባይነት
* የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም

3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ
* የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ማና
* የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት
* ከጠላት ጋር በጥቅምም ሆነ በፆታዊ ግኑኝነት እያደረጉ ባሉ ሰዎች ጉዳይ

4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ?

በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተመኩሯል፡፡

በውይይቱም ህዝቡ ደስተኛ እንደነበር እና እስከዛሬም ዘግይታችሃል በማለት ቁጭቱን በአደባባይ ገልፆል፡፡

በቀጣይም ሰፊ ውይይቶች እንዲደረግ እየጠየቁ ቀጠናውን እናንተ በመያዛችሁ ሰላም አግኝተናል ከመሳቀቅ ድነናል ሲሉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ምክትል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ፡ የጨነቀው የአብይ ብሮፓጋንድስት የውሸት ቀደዳውን ቀጥሏል ፍኖ አሸናኝ ላለማለት ሻቢያ ማረኩ ወያኔ ማረኩ ይላል ይሄ የፈሳም የውሽታም ስብስብ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251945700818

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቴምር አሳምነው ፅጌ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቴምር አሳምነው ፅጌ:

Share

Category